Telegram Web Link
#ጥቆማ

በቅርቡ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየሰጠ ካለው የሕክምና አገልግሎቶች በተጨማሪ ከዛሬ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ የጥርስ፣ የኤም.አር.አይ. እና የስነ-ደዌ/Pathology/ የሕክምናና ምርመራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት እየተሰጠ ያለውን የመምህራን ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተመልክተዋል።

ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ በ28 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የመምህራን ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

ምስል፦ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ በሦስት የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲዎች እና በትምህርት ሚኒስቴር ትብብር ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲሰጥ የቆየው የአመራር እና አስተዳደር (LMG) ፕሮግራም የመዝጊያ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሒዷል፡፡

ከ37 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 50 የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች በፕሮግራሙ የተሳተፉ ሲሆን፤ የከፍተኛ ትምህርት የአመራር እና የአስተዳደር ክህሎታቸውን ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና ተከታትለዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ በዩናይትድ ስቴትስ የሥራ ጉብኝትም አድርገዋል፡፡

ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ በቴክሳስ ቴክ ዩኒቨርሲቲ፣ በኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ በኦክላሆማ ስቴት ዩኒቨርስቲ እና በትምህርት ሚኒስቴር ትብብር ላለፉት ሁለት ዓመታት ተፈጻሚ ሆኗል፡፡

@tikvahuniversity
በሲዳማ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠውን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ75 በመቶ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸው ተገለፀ፡፡ 

996 ትምህርት ቤቶች ለ48,763 ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል ፈተናን የሰጡ ሲሆን፤ 152 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸውን የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሳ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል 69,880 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ 37,845 ወይም 54.1 በመቶ ተማሪዎች 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

792 ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ያስፈተኑ ሲሆን 44 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ማሳለፉፍ መቻላቸው ተገልጿል። 23 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።

አንድ ተማሪ ብቻ ያሳለፉ እና ምንም ተማሪ ባላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ላይ ችግሮችን የመለየትና የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#Sidama የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ የስምንተኛና ስድስተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መለቀቁን በቲክቫህ ገልጿል።

የቢሮዉ ኮሚዩኒኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ ጸጋ ሀጎስ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ተማሪዎች ዉጤታቸዉን በሊንክ ማየት እንደሚችሉ ገልጸዉልናል።

በዚህም መሰረት
ለስድስተኛ ክፍለ
https://sidama6.ministry.et/#/

ለስምንተኛ ክፍል
https://sidama.ministry.et/#/

@tikvahuniversity
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ከዘመኑ ጋር አብሮ የዘመነ ዓለም የደረሰባቸውን ቴክኖሎጂዎች በአንድ ላይ ያጣማረ ለእርሶ የሚገባ ዘመናዊ ስልክ!!

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር ተመስርቷል።

በምስረታ ጉባኤው ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ የቀድሞ ተማሪዎች በአካልና በኦንላይን ተሳትፈዋል፡፡

በማኅበሩ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ፣ የውስጥ ቁጥጥር ኦዲተር እና ሌሎች የቦርድ አባላት ምርጫ ተካሒዷል።

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

ለስፖርት ፀሀፊነት የወጣ የስራ ማስታወቂያ (ቲክቫህ ስፖርት)

የቅጥር ሁኔታ፦ ቋሚ

በዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች ላይ ዜና መስራት የሚፈልግ/የምትፈልግ፣

- ወቅታዊ ዜናዎችን ተከታትሎ በሰዓት በፅሁፍ ማቅረብ የሚችል፣

- ሥራውን ካለበት ሆኖ ማከናወን የሚችል/የምትችል፣

- እንደስፈላጊነቱ በተለያዩ መርሐግብሮች ላይ ሪፖርት ማዘጋጀት የሚችል/የምትችል፣

- አማርኛ ሥርዓቱን ጠብቆ መጻፍ የሚችል። እንዲሁም ዓለም አቀፍ ዜናዎችን ወደ አማርኛ ምልስ ትርጉም ጠንቅቆ ማዘጋጀት የሚችል/የሞትችል፣

- ለሥራው የሚሆን ጥሩ ስልክ ያለው፤ የኢንተርኔት አገልግሎት በአስተማማኝ ሁኔታ ማግኘት የሚችል/የምትችል፣

- ዜናዎችን ተከታትሎ ፈጣን መረጃ ለመስጠት ንቁ (Active) የሆነ/የሆነች፣

- ለሚሰራው ሥራ ታማኝ፣ ፈጣን፣ ስልቹ ያልሆነ እንዲሁም የሚሰጡ አስተያየቶችን ተቀብሎ ለማስተካከል ዝግጁ የሆነ/የሆነች፣

- ለረጅም ጊዜ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች።

ደምወዝ፦ በድርጅቱ ስኬል መሠረት

የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ ሃያ ሁለት

የሥራ ልምድ፦ ስለ ሁሉም አይነት ስፖርት በቂ ዕውቀት ያለው/ያላትና ወቅታዊ ስፖርታዊ መረጃዎችን የሚከታተል/የምትከታተል።

🔴 አመልካቾች ለማመልከት ማስረጃዎችን ሲልኩ ማሳያ የሚሆን ዜናዎችን ቢልኩ ይመረጣል።

🔴 ማመልከቻችሁን ለመላክ፦ @Tikvahsportcv
#Infinix_Note40_Pro_Plus

አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ከፍተኛ ጥራት ያለው 108 ሜጋ ፒክስል ካሜራው በተለያዩ አማራጮች ቁልጭ ያለ ፎቶን ይሰጦታል በተጨማሪም የሱፐር ዙም ቴክኖሎጂው ከርቀት ሆነው ጥራት ያለው ምስልን ማንሳት ያስችላል፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 42.93 ከመቶ ተማሪዎች የማለፊያውን 50 ከመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በክልሉ በ2016 ዓ.ም 45,086 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ 19,355 ተማሪዎች (42.93 በመቶ) የማለፊያ 50 ከመቶ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የቢሮው ኃላፊ አልማው ዘውዴ ተናግረዋል።

ውጤት ለማየት፦ www.sw.ministry

ተማሪዎች ከላይ የተገለፀው አድራሻ ላይ በመግባት View Result የሚለውን በመጫን፣ የመመዝገቢያ ቁጥራችሁንና ስማችሁን በማስገባት ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ። #SouthWestCommunications

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፍ ሆኗል።

በክልሉ የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወሰዱ 132,225 ተማሪዎች መካከል 97,859 (74.1%) ተማሪዎች የማለፊያ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት እንዳስመዝገቡ የክልሉ ትሞህርት ቢሮ አሳውቋል።

በተመሳሳይ የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወሰዱ 150,928 ተማሪዎች መካከል 84,522 (56%) ተማሪዎች የማለፊያ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል።

በክልሉ 82 አይነ ስውር የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ተቀምጠው 80 ተማሪዎች (95.18%) የማለፊያ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን፤ ፈተናውን ከወሰዱ 148 የ8ኛ ክፍል አይነስውር ተማሪዎች  መካከል 105 (70.94%) ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ውጤት ለማየት 👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች፦
https://amhara.ministry.et/#/result

ውጤት ለማየት 👉 ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች፦
https://amhara6.ministry.et/#/result

በተጨማሪ በቴሌግራም ቦት ለማየት፦
@emacs_ministry_result_qmt_bot  

ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ለማቅረብ፦

👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች፦
https://amhara.ministry.et/#/complaint

👉 ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች፦
https://amhara6.ministry.et/#/complaint

@tikvahuniversity
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ ከታዋቂው ዓለም አቀፍ የስፒከር አምራች ኩባንያ ጄቢኤል ጋር በመተባበር አዲሱን ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ ከእጅግ አስገራሚ የድምፅ ጥራት ጋር ይዞ መጥቷል፡፡ ሙዚቃ ለማዳምጥ፣ ጌም ለመጫወት እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያ ለመመልከት በኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ ልዩ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
Tikvah-University
Photo
በአማራ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ትናንት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠውን ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል፥ በደሴ ከተማ ሁለት ተማሪዎች ከፍተኛውን ውጤት አስመዝግበዋል።

በደሴ ከተማ በግል ትምህርት ቤቶች ተማሪ የሆኑት
ሳሚያ የሱፍ እና ሲትረላህ አሊ የአቬሬጅ እና ፐርሰንታል 100 በማምጣት በክልሉ ከፍተኛውን ውጤት አሳክተዋል።

ተማሪዎቹ በደሴ ከተማ በሚገኙት ካቶሊክ ትምህርት ቤት እና አልፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በትምህርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ጥናት በቅርቡ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2ኛ ዙር የ'ትምህርት ለትውልድ' ክልል አቀፍ የንቅናቄ መድረክ በወራቤ ከተማ ተካሒዷል፡፡

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) "በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ጥናት በሚኒስቴሩ እየተከናወነ እንደሚገኝና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትግበራ እንደሚገባ" ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/03 19:21:57
Back to Top
HTML Embed Code: