Telegram Web Link
ስቴምፓወር የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከአውስትራሊያ ኤምባሲ፣ IBM SkillsBuild እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሴቶችን ለማብቃት ያለመ የዲጂታል ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡

ስልጠናው ሴቶች የስራ ቅጥር ዕድላቸውን የሚያሰፉበት የቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ የሚታየውን ፆታዊ ልዩነት ለማጥበብ ስልጠናው ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው የስቴምፓውር የኢትዮጵያ ተወካይ ስሜነው ከሰሰ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Infinix_Note40_Pro_Plus

የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ካሜራ 108 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያለው የካሜራ ቴክኖሎጂ ይዞ የመጣ ሲሆን የ 100 ዋት ፋስት ቻርጀር እና ባለ 20 ዋት ያለገመድ ዋየር ለስ ቻርጅ ማድረግ የሚችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዘመኑ የመጨረሻ ቴክኖሊጂ የሆነውን 5G ኔትወርክን ማስጠቀም የሚያስችል ድንቅ አቅም ያለው ስልክ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
176 ሺህ በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች የትምህርት ዕድል እንደተሰጣቸው መንግሥት ገለፀ።

በናሚቢያ፥ ዊንድሆክ የስደተኞች ትምህርት ጉዳይን አስመልክቶ በተደረገ ውይይት ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ፤ ኢትዮጵያ 850 ሺህ የሚሆኑ ስደተኞችን ተቀብላ እያኖረች ሲሆን ከእነዚህ ስደተኞች ውስጥ 176 ሺህ የሚሆኑትን የትምህርት ዕድል እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።

ስደተኞቹ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የትምህርት ዕድል ማግኘታቸውን ሚኒስትር ዲኤታው ተናግረዋል።

እስከ ሁለተኛ ዲግሪ የዩኒቨርሲቲ የትምህርት ዕድል የተሰጣቸውና ሙሉ ወጪያቸውም በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈንላቸው እንዳሉ ሚኒስትር ድኤታው ጠቁመዋል። #HaramayaUniversity

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ IELTS ፈተና ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) ይሰጣሉ፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገፅ ላይ በመግባት ኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations

ለፈተናው ዝግጅት የሚያስፈልግዎትን ስልጠና እና ምክር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
መቱ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎቹን መስከረም 3 እና 4/2017 ዓ.ም እንደጠራ ተደርጎ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የሚዘዋወረው የጥሪ ማስታወቂያ ሐሰተኛ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

መቱ ዩኒቨርሲቲ በራሱ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች በይፋ ጥሪ እስከሚየደርግ ድረስ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

@tikvahuniversity
📱 ቅመም Itel Proን ዛሬውኑ ገዝተን ለ90 ቀናት የሚቆይ ነፃ የ90GB ቲክቶክ ጥቅል እናግኝ! አሁኑኑ ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች በማቅናት ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር ቅመም Itel Proን እንግዛ!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር መተግባር ይጀምራል።

በትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ኮራ ጡሹኔ በቀን ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተፃፈ ደብዳቤን ትክክለኛነት እንድናረጋግጥ በርካታ ጥያቄዎች ደርሰዋል።

ደብዳቤው ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣ እና ትክክለኛ መሆኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደብዳቤው ከደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አረጋግጧል።

ደብዳቤው ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተግባር እንደሚጀምር ይገልፃል።

በዚህም፦

★ የ1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ፦ መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም

★ የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 9 እና 10/2017 ዓ.ም

★ የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት መስከረም 13/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

(ሙሉው የ2017 ትምህርት ዘመን የአካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ ሳይንቲስት ሔማን በቀለ የታይም መፀሔት የዓመቱ ታዳጊ ተብሏል።

በአሜሪካ ቨርጂንያ ነዋሪ የሆነው ታዳጊ ሔማን፥ የቆዳ ካንሰርን ለማከም የሚያስችልና በአነስተኛ ዋጋ የሚሸጥ ሳሙና በመፍጠር ሽልማቶች ማግኘቱ ይታወቃል።

ታይም መፀሔት ዛሬ ያወጣውን ሰፊ ዳሰሳ ለማንበብ 👇
https://ti.me/3Asbszu

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በታዳጊው ሳይንቲስት ላይ የሰራቸው ዘገባዎችን ለማየት፦

https://www.tg-me.com/TikvahUniversity/9148

https://www.tg-me.com/TikvahUniversity/8852

@tikvahuniversity
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ሸካ ዞኖች ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 50 ተማሪዎች የስቴም ሰልጠና መስጠት ጀምሯል።

ተማሪዎቹ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ትምህርቶች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።

ስልጠናው ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን፤ በዩኒቨርሲቲው ቴፒ ካምፓስ በሚገኘው የስቴም ማዕከል ውስጥ ይሰጣል።

@tikvahuniversity
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የስነ-አዕምሮ ጤና ክፍል ከፍቷል።

ዩኒቨርስቲው የአዕምሮ ጤና ላይ ትኩረት ያደረገ አውደ ጥናት አካሒዷል።

የአዕምሮ ጤና አገልግሎት በኢትዮጵያ፣ የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀምና የአዕምሮ ጤና እንዲሁም የህፃናት የአዕምሮ ጤናን የተመለከቱ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

@tikvahuniversity
#ይመዝገቡ
#ዛሬ_ይጠናቀቃል

በ2017 ዓ.ም በድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ለመማር የአመልካቾች የመግቢያ ፈተና ምዝገባ አድርገዋል?

ለአምስት ቀናት የተራዘመው የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ይመዝገቡ 👉 https://NGAT.ethernet.edu.et

@tikvahuniversity
📯 Professionals Talk | የሙያ ወግ 📯

Topic: Becoming a Professional Tech Product Developer for the 21st Century

📅 August 17, 2024
🕰 1:00 PM-4:00 PM EAT
📍 Vamdas Cinema

🌟 55 Training Full Scholarship
🌟 27+ Internship Offer
🌟 15 Workshop Offer

Join us for an insightful panel discussion on navigating the job market and developing in-demand skills in Tech products developing, innovation and entrepreneurship sponsored by Safaricom.

Hear directly from experts, and impactful youth professionals in the industry as they share their experiences and expert advice. This free event is your chance to get practical guidance and make valuable connections with other professionals and like-minded people in this industry.

🎟 FREE ENTRANCE

Register here 👇
https://forms.gle/rsatstJCDyj1VeMa6

For more Info contact @Stenarcustomerservice

Don't miss this smart, career-boosting opportunity. See you there!
2024/10/03 09:20:20
Back to Top
HTML Embed Code: