Telegram Web Link
#ጥቆማ

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተለያዩ የአጭር ጊዜ ስልጠናዎች አዘጋጅቷል፡፡

ስልጠናዎቹ በአራት ፈረቃዎች ማለትም ከ3:00- 5:00 ፣ ከ7፡00- 9፡00 ፣ ከ9:00-12:00 እንዲሁም ማታ ከ12:00-2:00 ሰዓት ይሰጣሉ፡፡ የስልጠና ፈላጊዎችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ቅዳሜ እና እሁድ መርሐግብር ሊሰጥ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

የስልጠና ርዕሶች፦

► Tourism and Hospitality Marketing
► Hospitality leadership Management
► Tour Operation Service
► Culinary Art
► Barista Service
► Bartender Service
► Food Safety Service
► Butchery Service
► Wellness and Spa Service
► Housekeeping and Laundry Service
► Pastry and Bakery
► Food Beverage Service
► Fast Food Preparation
► Food and Beverage Control
► Front Office Service

የምዝገባ ቦታ፦ በገነት ካምፓስ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
የመመዝገቢያ ክፍያ፦ 100 ብር

(የኢንስቲትዩቱ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#YHMC

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ የተመደቡ 'አዲስ የህክምና ትምህርት ኢንሼቲቭ' (NIMEI) ተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 15-17/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

አጠቃላይ ገልፃ ነሐሴ 20 እና 21/2016 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

► ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
► የቅድመ ምረቃ ዲግሪ ዋናውና ኮፒው
► ስቱድንት ኮፒ ዋናውና ኮፒው
► ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ፖ.ሳ.ቁ. 257 ማስላክ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
Vacancy #CBE
=======

Commercial Bank of Ethiopia would like to invite qualified and interested job seekers to apply for the following positions:

1.  IS Trainee (Head Office)
2.  Laboratory Service Officer (Head Office)
3.  Junior Laboratory Service Officer (Head Office)
4.  Graphics Designer and Video Editor (Head Office)
5.  Associate Collateral Valuator –I (Shire Endasilassie District)
6.  Associate Collateral Valuator –II (Shire Endasilassie District)
7.  Collateral Valuator (Shire Endasilassie District)
8.  District Attorney (Shire Endasilassie District)
9.  Associate District Attorney (Shire Endasilassie District)
10.  Bank Trainee (Mekelle and Shire Endasilassie Districts)

Interested and qualified job seekers should apply through CBE career website (https://vacancy.cbe.com.et) from August 12 – 18, 2024
For requirements and other detail information, please use the following link:
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Extrenal_vacancy_09_08_2024_a4840b9198.pdf
CBE Vacancy Site User Guideline.pdf
1.5 MB
CBE Vacancy Site User Guideline

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ማመልከቻ ድረ-ገፅ (https://vacancy.cbe.com.et ) ክፍት የሥራ ቦታዎች ለማመልከት የሚረዳ መመሪያ

(ንግድ ባንክ)

@tikvahuniversity
እንኳን እስከ 400,000 ብር ለሚደርስ ሽልማት በነጻም እኮ ይዘፈናል! አሁኑኑ ወደ TikTok ሄደን ተሰጥዖአችንን እናሳይ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፦

🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትን ከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳትረሱ
📲የ TikTok ደረ-ገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!


#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
#ጥቆማ

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት በ2017 የትምርት ዘመን በተመረጡ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች አመልካቾችን እንደሚቀበል አሳውቋል፡፡

የማስተርስ ፕሮግራሞች፦
1. MSc in Land Administration and Management
2. MSc in Real Property Valuation
3. MSc in Geomatics
4. MSc in Land Use Planning
5. MA in Land Law

የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራም፦
1. PhD in Land Policy and Governance

ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በመፈተን እና አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ገልጿል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦ 0918164647 / 0977907163

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከቡሉምበርግ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ አፍሪካ ጋር በመተባበር የፋይናሻል ጋዜጠኝነት ስልጠና ሊሰጡ ነው፡፡

ስልጠናውን በተመለከተ የፕሮግራም ትውውቅ በዛሬው ዕለት የተካሔደ ሲሆን፤ ስልጠናው በዩኒቨርሲቲዎቹ የጋዜጠኝነት ተማሪዎች እንዲሁም በሥራ ላይ ላሉ ጋዜጠኞች የፋይናሻል ዘገባ ግንዛቤያቸውን የሚያሳድግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ የካፒታል ገበያ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርገው ስልጠናው፤ ፍላጎት ላላቸው ጋዜጠኞች ለተከታታይ ስድስት ወራት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ወንደወሰን ሙሉጌታ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው በተለይ ወቅቱ የሚጠይቀውን የፋይናንሻል ጋዜጠኝነት ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ለማፍራት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

የፋይናሻል ጋዜጠኝነት ቁጥራዊ መረጃን በትክክል መርምሮ ከመዘገብ ባለፈ የኢኮኖሚ መረጃን በግልጽ ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡ #ኢፕድ

@tikvahuniversity
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የስቴም ስልጠና ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞችን ተቀብሏል።

የወጣቶችን እና ተማሪዎችን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ ዕውቀትና ክህሎት ለማጎልበት እንዲሁም የፈጣራ ሃሳብ ለማሳደግ የሚሰራው ማዕከሉ፤ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ ወጣቶችን ዛሬ ተቀብሏል።

ማዕከሉ በኢንስቲትዩቱ አካባቢ ለሚገኙ ወጣቶች ተከታታይ ስልጠና እንደሚሰጥ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ወጣቶቹ አንድ የፈጠራ ሃሳብ ይዘው እንደሚወጡ ያላቸውን ተስፋ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

የኢንስቲትዩቱ የስቴም ስልጠና ማዕከል STEMpower ከተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ጋር በመተባበር ባለፈው ግንቦት ነበር የተመረቀው፡፡

@tikvahuniversity
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ አዲሱን የኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልኩን እጅግ ደማቅ በሆነ የጌሚኒንግ እና የሙዘቃ ዝግጅት በቃና ስቱዲዮ ለተጠቃሚዎች አስተዋውቋል!

በተለይም ለጌመሮች እና ለሙዚቃ አድናቂዎች የተለየ ነገርን ይዞ የመጣው አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም በቃና ስቱዲዮ በአይነቱ ለየት ባለ ዘግጅት አዲሱን ስልኩን አንዲሁም የኢንፊኒክስ ቲቪ፣ ላፕ ቶፕ፣ ስፒከሮች፣ ስማርት ሰዓት እና ኤር ፖዶችን ለተጠቃሚዎች አስተዋውቋል፡፡

አዲሱ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ 108 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያለው የካሜራ ቴክኖሎጂ ይዞ የመጣ ሲሆን 100 ዋት ፋስት ቻርጀር እና 20 ዋት ያለገመድ ዋየርለስ ቻርጅ ማድረግ የሚያስችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዘመኑ የመጨረሻ የኔትወርክ ቴክኖሎጂ የሆነውን 5G ኔትወርክን ማስጠቀም የሚያስችል አቅም ያለው ሲሆን በጌመሮች እና ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ ስራዎችን በስልካቸው በሚከውኑ ስዎች ተመራጭ የሆነውን የ Mediatek Dimesnty 7020 ፕሮሰሰር የተገጠመለት ፈጣን ስልክ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
#ጥቆማ

የአዲስ ቻምበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የተለያዩ አጫጭር የቢዝነስ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ስልጠናዎቹ እስከ መስከረም 9/2017 ዓ.ም እንደሚቆዩ ተገልጿል፡፡

ከሚሰጡ ስልጠናዎች መካከል ካፒታል ማርኬት፣ ዲጂታል ማርኬቲንግ፣ የአመራር ክህሎት፣ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ኦፊስ ኦፐሬሽንስ ማኔጅመንት ይገኙበታል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
0115500934 / 0911194965 / 0911343078 / 0913553393

የኢ-ሜይል አድራሻዎች፦
[email protected] / [email protected] / [email protected]

(የስልጠናዎቹን አይነት፣ የጊዜ ርዝመት እና ክፍያ መጠን የሚያሳይ ከኢንስቲትዩቱ የተገኘ መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ስቴምፓወር የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከአውስትራሊያ ኤምባሲ፣ IBM SkillsBuild እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሴቶችን ለማብቃት ያለመ የዲጂታል ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡

ስልጠናው ሴቶች የስራ ቅጥር ዕድላቸውን የሚያሰፉበት የቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ የሚታየውን ፆታዊ ልዩነት ለማጥበብ ስልጠናው ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው የስቴምፓውር የኢትዮጵያ ተወካይ ስሜነው ከሰሰ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Infinix_Note40_Pro_Plus

የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ካሜራ 108 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያለው የካሜራ ቴክኖሎጂ ይዞ የመጣ ሲሆን የ 100 ዋት ፋስት ቻርጀር እና ባለ 20 ዋት ያለገመድ ዋየር ለስ ቻርጅ ማድረግ የሚችል ነው፡፡ በተጨማሪም የዘመኑ የመጨረሻ ቴክኖሊጂ የሆነውን 5G ኔትወርክን ማስጠቀም የሚያስችል ድንቅ አቅም ያለው ስልክ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
2024/10/03 23:19:41
Back to Top
HTML Embed Code: