Telegram Web Link
የመምህራን ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ የተመራ የሱፐርቪዥን ቡድን በዩኒቨርሲው በመገኘት የስልጠናውን አሰጣጥ ተመልክቷል።

በዩኒቨርሲቲው እየተሰጠ ባለው የክረምት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከ 2 ሺህ በላይ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

"ሰልጣኞች ከአበል ክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን እንዳቀረቡና ስልጠናውም ተቋርጦ እንደነበር" የሚያሳዩ መረጃዎች ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወሩ ነበር፡፡

"በስልጠናው ተሳታፊዎች እንደ ችግር የሚነሱና አስተዳደራዊ ምላሽ የሚሹ ጉዳዮችን በቅርበት በመከታተል መፍትሔ እንዲያገኙ ይደረጋል" ብለዋል በዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ጉብኝት ያደረጉት ሚኒስትር ዴኤታዋ።

ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናው በ28 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሥራቸውን ለማስቀጠል የሚያስችላቸውን ፈቃድ ለማግኘት እስከ ታኅሳስ 30/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደገና ምዝገባ ማከናወን እንዳለባቸው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል። ዳግም ምዝገባው ያስፈለገው እንደ  ሀገር ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል። በዚህም በመንግሥት እና በግል ተቋማት…
#ETA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በፌደራል ደረጃ ፈቃድ የተሰጣቸው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ባወጣው የዳግም ምዝገባ መምሪያ መሰረት እስከ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ድረስ ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

በዚህም ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቋም፣ በካምፓስ እና በፕሮግራም ደረጃ ያሉ መረጃዎችን በሀርድ ኮፒ እና ሶፍት ኮፒ መረጃዎችን በማደራጀት በአካል እንዲያቀርቡ ባለሥልጣኑ አስረድቷል።

(የባለሥልጣኑ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የተማሪዎችድምጽ

° “ ሳንመረቅ አመታት ተቆጠሩ፡፡ ዩኒቨርሲቲው መቼ እንደሚጠራን ያሳውቀን ” - ተመራቂ ተማሪዎች

° “ መስከረም 2017 ዓ/ም መጀመሪያ አካባቢ ይጠራሉ ” - መቐለ ዩኒቨርሲቲ


ትግራይ ውስጥ በነበረው ጦርነት ሳቢያ ጭምር የመመረቂያ ጊዜያቸው የተራዘመባቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመመረቅና ድግሪ ለመያዝ አመታትን እንደጠበቁ ፣ አሁንም ዩኒቨርሲቲው እንዳልጠራቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ምን አሉ ?

- ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ስለጉዳዩ ዩኒቨርሲቲውን ጠይቀን ነበር። የመውጫ ፈተና እንደምንፈተን እና ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ላይ እንደምንመረቅ ነበር ስኬጁል የወጣው።

- የመውጫ ፈተናውን ብንወስድም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲውን ለቀን ወጥተናል። ከዚያ ነሐሴ 2016 ዓ/ም ትጠራላችሁ ተባልን፡፡ አሁን የክረምት ተማሪዎችም ተጠርተዋል፡፡ እስካሁን የኛ ግን ምንም ነገር የለም። ዝም ጭጭ ብለዋል።

- የፌደራል መንግስትም በጦርነነቱ ጊዜ የነበሩ ተማሪዎች በዓመት 3 ሴሚስተር ማካካሻ ጊዜ ፈቅዶልን ነበር፡፡ ያኔ የተፈቀደልንን ማካካሻ በአግባቡ ያስተናግዱን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ የጠየቀው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ፤ “ ተማሪዎቹ እያነሱት ያለው ቅሬታ ትክክል ነው ” ብሏል።

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚደንት ተከስተ ብርሃን (ዶ/ር) ምን አሉ ?

በተለያዩ ምክንያቶች በተለይ ትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ጦርነት ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎች አሉን።

ክረምቱን እንዲማሩ ነበር በዩኒቨርሲቲው ማኔጀመንት የወሰነው። ነገር ግን በአገር ደረጃ በተሰጠው ዳይሬክሽን መሠረት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲፈተኑ መደበኛ ተማሪዎቹ ማስወጣት የግድ ነበር።

በኮረና እና በነበረውም ጦርነት ትምህርታቸውን ያቋረጡ የክረምት ተማሪዎች ነበሩ። እነርሱንም ተቀበልን፡፡ ለመምህራን የሚሰጥ ስልጠና አለ፡፡ እነርሱንም ተቀብለን እያሰለጠንን ነው።

በእነዚህ ምክንያቶች መደበኛ ተማሪዎቻችንን መጥራት አልቻልንም።

አሁን እንደ አቅጣጫ የያዝነው መስከረም 2017 ዓ/ም መጀመሪያ አካባቢ ጠርተን ማካካሽ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ባለፉት ዓመታት ሊመረቁ ለነበሩ ተማሪዎች ብቻ ካላንደር አዘጋጅተን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዲመረቁ ነው።

መስከረም ስንት ቀን ይጠራሉ ? ቁርጥ ያለውስ ቀን መቼ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ተከሰተ (ዶ/ር)፣ " የክረምት ተማሪዎቹ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ/ም እንዲያጠናቅቁ ብለናል፡፡ ስለዚህ ካላንደሩ ገና አልጸደቀም መስከረም መጀመሪያ አካባቢ ይጠራሉ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

#TIkvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የተማሪዎችድምጽ

ዛሬ በርካታ የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኢንተርን ሀኪሞች ወደ ቲክቫህ መልዕክት እያደረሱ ናቸው።

በዚህም አሉ ያሏቸውን ችግሮች እንዲታወቁና መላሽ እንዲሰጥባቸው ጠይቀዋል።

ኢንተርን ሃኪሞቹ ምን አሉ ?

- የ6ኛ ዓመት የሕክምና ተማሪዎች ከሐምሌ 15/11/2016  ዓ.ም ጀምሮ ወደ  ኢንተርንሺፕ የገባን ተለማማጅ ሀኪሞች (Medical Interns) ነን።

- በኢትዮጵያ ባሉ ሁሉም የህክምና ዩኒቨርቲዎች የምግብ አገልግሎት ወይም cost sharing (ወጭ መጋራት) የሚያገኙ ሲሆን የኛ ዩኒቨርስቲ ግን ከዚ በተለየ መልኩ " ከዛሬ ጀምሮ ምንም አይነት የምግብ አገልግሎት አታገኙም "  በማለቱ ያለምግብ ሆስፒታል ገብተን ስራ መስራት ስለማንችል መፍትሔ ይሰጠን ብለን ጥያቄ ስናቀርብ ቆይተናል።

-  ይሁን እንጂ " አድማ እያደረጋቹ ነዉ " በማለት " ባጭር ጊዜ ወደ ሆስፒታል ስራችሁ ግቡ ይህ ካልሆነ ግን ከዩኒቨርስቲው ትባረራላችሁ " ተብለናል።

- በ2010 ዓ.ም ጀምሮ ዩኒቨርሲቲውን የተቀላቀልን ቢሆንም በሀገራችን እነዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በተከሰቱ ሁነቶች እስካሁን 2 ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ሳይካካስ ባክኖብናል።

- ያሳለፍነው ጠባሳ ሳያንስ አሁን ደግሞ ከግቢ ትወጣላቹ የሚለው ማስፈራሪያ አሳዝኖናል።

- ከሀምሌ 18/11/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ በመመለስና ያለው ከሌለው በመረዳዳት ክፍያ እስኪጀመርልን ለመቀጠል በመወሰን በስራ ገበታ ላይ እንገኛለን።

- ከዚህ በተጨማሪ በትምህርት ሚኒስትር በወጣ መመሪያ በ cost share ወይም ወጭ መጋራት በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለመደበኛ ተማሪዎች የነፃ ህክምና እየተሰጠ ባለበት ሰዓት የባህር ዳር የኒቨርሲቲ የኢንተርን ሀኪሞች አገልግሎቱን ተከልክለናል።

- ከሀምሌ 18 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምንም መፍትሔ ከዩኒቨርሲቲው ስላላገኘን ስራችንን  ለመቀጠል በጣም አስቸጋሪ አድርጎብናል።

- አብዛኞቻችን ረሀብን እንድንጋፈጥ ተፈርዶብናል ስለዚህ ፈጣን መፍትሄ እንፈልጋለን።

- ጉዳዩ በትምህርት ሚኒስትር እስኪፈታልን ሰላማዊ ጥያቄያችን እንቀጥላለን።

- የኢተርን ሀኪሞች የትርፍ ሰዓትን ጨምሮ ያለ እንቅልፍ ለተከታታይ 36 ሰዓታት የምንሰራ ሲሆን ያለ ምግብ እና ህክምና አገልግሎት መቀጠል ስለሚከብድ የሚመለከተው አካል በዋናነት ትምህርት ሚኒስትር አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን በታላቅ አፅንኦት እንጠይቃለን ።

ቲክቫህ በዚህ ጉዳይ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት ሚኒስቴርን ያነጋግራል።

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ለሚጀምረው የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም በአራት የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል፡፡

በዚህም በማስተርስ እና ፒኤችዲ ለሚሰጡ ተከታዮቹ ፕሮግራሞች ማመልከት ይቻላል ተብሏል፦

► Astronomy and Astrophysics
► Remote Sensing
► Space Science
► Geodesy

አመልካቾች የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለማስተርስ ዲግሪ ለማመልከት የመጀመሪያ ዲግሪ CGPA 3.00 እንዲሁም ለፒኤችዲ ፕሮግራም ለማመልከት የማስተርስ ዲግሪ CGPA 3.00 እና የመመረቂያ ፅሁፍ 'በጣም ጥሩ' ሊኖራችሁ ይገባል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የድኅረ ምረቃ ቢሮ 2ኛ ፍሉር በመገኘት ወይም የትምህርት ሰነዶችን በPDF ፎርማት በማዘጋጀት በ [email protected] የኢ-ሜይል አድራሻ ማመልከት ይቻላል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
መስከረም 6/2017 ዓ.ም
የመግቢያ ቀን፦
መስከረም 14/2017 ዓ.ም

(የኢንስቲትዩቱ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ምን እየጠበቅን ነው? ቲክቶክ ላይ የሙዚቃ ችሎታችንን እያሳየን እስከ 400,000 ብር እንሸለም እንጂ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፦
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት!
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትን ከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳትረሱ!
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ  እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#ይመዝገቡ

በ2017 የትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከተጀመረ አንድ ሳምንት አልፏል።

ምዝገባው ሊጠናቀቅ አምስት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እስከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም ብቻ ይመዝገቡ።

ለመመዝገብ 👇
https://NGAT.ethernet.edu.et

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የተማሪዎችድምጽ

° " ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " - የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንትርን ሀኪሞች

° " ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " - ዩኒቨርሲቲው

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች፣ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የምግብ አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን ምግብ መከልከላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ቅሬታቸውን ለተማሪዎች አገልግሎት ቢያቀርቡም መፍትሄ በማግኘት ፋንታ " እናባርራችኋለን " የሚል ዛቻ እንደደረሰባቸው አስረድተው፣ "  ብዙ ልጆች ተቸግረዋል፡፡ የምግብ አገልግሎት ተከልክለናል " ነው ያሉት።

ዩኒቨርሲቲውን የተቀላቀሉት 2010 ዓ.ም እንደሆነ ፤ በተለያዩ ችግሮች ሁለት ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ እንደባከነባቸውና እንዳልተካካሰላቸው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ተማሪዎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ ሆኖ ሳለ እነርሱ ህክምና መከልካላቸውን አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ የተማሪዎቹን ቅሬታ ይዞ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚደንት ዶክተር መንገሻ አየነን አናግሯል።

ዶክተር እሳቸው ጋር ምንም አይነት የቀረበላቸው ቅሬታ እንደሌለ ገልጸው፣ ለማን ቅሬታ እንዳቀረቡ ኢንተርን ሀኪሞቹ በድጋሚ እንዲጠየቁ አሳስበዋል፡፡

እሽ በማለት ቅሬታ አቅራቢዎቹን ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት አሳውቃችሁ ነበር ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽም፣ " ለዶክተር መንገሻ አልደረሰም፡፡ ለተማሪዎች አገልግሎት አቅርበናል " ብለዋል።

ለምን ለዩኒቨርቲው ከፍተኛ አካላት እንዳላቀረቡ ሲያስረዱም፣ " የተማሪዎች አገልግሎት 'ይሄ ጉዳይ ከእኔ አልፎ ወደ ላይ ቢሄድ አውቶማቲካሊ ሴኔት ሰብስብቤ ፈርሜ አባራችኋለሁ' አለን " ብለዋል፡፡

" ቅሬታችንን ለዶክተር መንገሻም አላሳወቁትም ከታች ነው ያስቀሩት " ሲሉም አክለዋል፡፡

ቅሬታው ደርሷቸዋል የተባሉት አካላት ለጊዜ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲሆን፣ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቅሬታ ያቀረቡበትን ክፍል በመግለጽ በድጋሚ ስለጉዳዩ ጠይቀናቸዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ መንገሻ (ዶ/ር)፣ የኢንተርን ሀኪሞቹ ቅሬታ ዩኒቨርሲቲው ያላወቀው ቅሬታ እንደሆነ አስረድተው፣ ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

" ፕሮፌሰር የሺጌታ የሚባል ሲኢድ አለን ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ሙሉውን የሚመራ የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ነው እዚያ ግቢ " ያሉት መንገሻ (ዶ/ር)፣ ' ፕሮፌሰሩን ይጠይቁ፡፡ እሱ ካልፈታላቸው ወደ እኔ ይመጣሉ ወይም ደብዳቤ ካላቸው ያምጡ " ብለዋል፡፡

" ጥያቄያቸው ይቅረብና ፍትሃዊ ከሆነ እናያለን፡፡ የሚመለከተው አካል ለምን እንዳላስተናገደም የምቀጣ ይሆናል " ሲሉ አክለዋል፡፡

(ጉዳዩ ከምን እንደደረሰ ተከታትለን መረጃ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

የPhD ትምህርት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመሆን ለ2ዐ17 ዓ.ም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የትምህርት መስክ የPhD ፕሮግራም በመደበኛ መርሐግብር አመልካቾችን ተቀብለው ማስተማር ይፈልጋሉ፡፡

የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦

► የሁለተኛ ዲግሪ በተያያዥ የትምህርት ዘርፍ ከታወቀ የትምህርት ተቋም፣
► በሁለተኛ ዲግሪ CGPA ለሴቶች 3.00 ፤ ለወንዶች 3.25፣
► የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና ያለፉ፣
► የሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ፅሁፍ ውጤት 'ጥሩ' የሆነ፣
► ከ10 ገጽ ያልበለጠ 'Synopsis'ማዘጋጀት ይጠበቅባችኋል፣
► ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

የማመልከቻ ጊዜ፦
ከዛሬ ነሐሴ 1/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 06/2017 ዓ.ም (በኦንላይን)

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#ይመዝገቡ በ2017 የትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከተጀመረ አንድ ሳምንት አልፏል። ምዝገባው ሊጠናቀቅ አምስት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እስከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም ብቻ ይመዝገቡ። ለመመዝገብ 👇 https://NGAT.ethernet.edu.et @tikvahuniversity
ሀገራዊ_የድህረ_ምረቃ_መግቢያ_ፈተና_አሰጣጥና_አስተዳደር_ማኑዋል_መጋቢት_2016_ዓም_GAT_Manual.pdf
6.1 MB
የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና አሰጣጥና አስተዳደር ማንዋል

አገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በመስከረም እና በህዳር 2016 ዓ.ም በሁለት ዙር የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ 3ኛው ዙር የ NGAT ፈተና በዚህ ወር እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

(ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉት የሚጠበቀው “አገራዊ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና አሰጣጥና አስተዳደር ማንዋል" ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የምርምር ዩኒቨርሲቲ የሆነው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለድኅረ ምረቃ እና ለምርምር ሥራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለድኅረምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች፦
- የዶርም አገልግሎት፣
- የቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣
- የዲጂታል ቤተመጻሕፍትና ኮምፒውተር ማዕከላት እና
- የ24 ሰዓት የኢንተርኔት አገልግሎት ያቀርባል፡፡

ተቋሙ ለፒ.ኤች.ዲ. ምርምር አወዳድሮ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚሰጥም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አሥራት አፀደወይን (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

(ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች በ11 ኮሌጆች ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምርባቸው የትምህርት መስኮች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

@tikvahuniversity
2024/10/02 20:36:15
Back to Top
HTML Embed Code: