Telegram Web Link
#NATIONAL_EXAM

ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች ከትናንት ጀምሮ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከማክሰኞ ሐምሌ 9/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን ይሰጣል።

በትግራይ ክልል ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሐምሌ 9-12/2016 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የነባር የሁለተኛ ዲግሪ የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለነባር የክረምት ተማሪዎች እና ለአዲስ ሰልጣኝ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ጥሪ አድርጓል።

በዚህም በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐግብር የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የነበራችሁ እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተመደባቹ አዲስ ሰልጣኝ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ምዝገባ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
ከጥቂት ቀናት በፊት አጋሮ እና ጅማ ከተሞች አካባቢ 'ከሰማይ ወደቁ ስለተባሉት ድንጋይ/አለት' ጥናት የሚያደርግ የባለሙያዎች ቡድን ማቋቋሙን ጅማ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል፡፡

በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወሩ የታዩት ምስሎች የወደቁት ነገሮች የአስትሮይድ ወይም ሚቲዮራይት ስብርባሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ ይሁን እንጂ ተገቢው ምርምር እና የላቦራቶሪ ፍተሻ መደረግ እንዳለበት ገልጿል፡፡

በመሆኑም የጅማ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች፣ ኬሚስቶች እና የማቴርያል ሳይንቲስቶችን ያቀፈ የባለሙያዎች ቡድን አቋቁሟል፡፡

ቡድኑ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

የወደቁትን ቁሶች ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ላቦራቶሪ ለመውሰድ ከአካባቢው አመራሮች ጋር ንግግር መጀመሩን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
#NATIONAL_EXAM

ለሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ዛሬ ዩኒቨርሲቲዎች አጠቃላይ ገለፃ ይሰጣሉ፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ሐምሌ 9/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ተፈታኞች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ የገቡ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት በፈተናው ዲሲፕሊን ዙሪያ አጠቃላይ ገለፃ እየተደረገላቸው ነው፡፡

ምስል፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በክረምት መርሐግብር ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነባራችሁ ሁሉም ነባር የክረምት የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 16 እና 17/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በቅጣት ለመመዝገብ፦ ሐምሌ 18 እና 19/2016 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦ በደሴ እና በኮምቦልቻ ግቢዎች

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ከዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የገባችው የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ብስራት ጌታነው ሴት ልጅ ተገላግላለች።

ተፈታኟ ሐምሌ 07/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ በወልድያ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሴት ልጅ ወልዳለች፡፡

"እሷም፣ ልጇም በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ" የተናገረችው ተማሪ ብስራት፤ ፈተናዋና ለመውሰድ መዘጋጀቷን ገልጻለች፡፡ ዩኒቨርሲቲውም ፈተናዋን እስክትጨርስ አስፈላጊውን ድጋፍ አደርግላታለሁ ብሏል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በቅርቡ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከነገ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡

በሕጻናት፣ በማህፀንና ጽንስ፣ በአጠቃላይ ቀዶ ጥገና እና በውስጥ ደዌ ተመላላሽ ሕክምና እንዲሁም የተለያዩ የላቦራቶሪ እና ኢሜጂንግ አገልግሎቶች አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከሰባት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው ሆስፒታሉ፤ 600 የህሙማን አልጋዎች እና የተለያዩ ዘመናዊ የህክምና ግብዓቶች የተሟላለት ነው፡፡

@tikvahuniversity
#DebreMarkoUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ የክረምት መርሐግብረ ተማሪዎች የምዝገባ ጌዜን በቀናት አራዝሟል።

የ2016 ዓ.ም ነባር የክረምት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 16 አና 17/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/02 06:24:30
Back to Top
HTML Embed Code: