Telegram Web Link
Tikvah-University
ዛሬ ያበቃል! በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የተዘጋጀ "ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ" ፕሮግራም (National Cyber Talent Challenge Program) የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡ በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በቻሌንጁ ላይ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፤ Cyber Security, Cyber Development,…
ለ3ኛ ዙር ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ፕሮግራም የተመዝግባችሁና ለፈተና ያለፋችሁ ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ የሆናችሁ፤ ፈተናው ከሐምሌ 9-12/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) አሳውቋል፡፡

ወደ 3ኛ ዙር ፈተና ያለፋችሁ ስም ዝርዝር በአስተዳደሩ የሳይበር ታለንት ማዕከል የቴሌግራም አድራሻ https://www.tg-me.com/cteinsa በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፈተናው ፕሮግራም እንደሚከተለው ይሆናል፦

- ስማችሁ በ 'A' የሚጀምር ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጠዋት 3፡00
- ስማችሁ በ 'B', 'C' እና 'D' የሚጀምር ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ከሰዓት 7፡30
- ስማችሁ በ 'E', 'F', 'G', እና 'H' የሚጀምር ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ጠዋት 3፡00
- ስማችሁ በ 'I', 'J', 'K', እና 'L' የሚጀምር ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ከሰዓት 7፡30
- ስማችሁ በ 'M' እና 'N' የሚጀምር ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም ጠዋት 3፡00
- ስማችሁ በ 'O', 'P', 'Q', ‘R’, ‘S’ እና 'T' የሚጀምር ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም ከሰዓት 7፡30
- ስማችሁ በ 'U', 'V', 'W', ‘X’, ‘Y’ እና 'Z' የሚጀምር ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ጠዋት 3፡00

የፈተና ቦታ፦ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የ INSA ዋና ቢሮ

ለፈተና ስትሔዱ መታወቂያ መያዝን እንዲሁም ፕሮጀክት የምታቀርቡበት ላፕቶፕ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

ወደ 3ኛ ዙር ያለፋችሁ #የክልል ተፈታኞች ከ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቅ በኋላ በየአካባቢያችሁ እንደምትፈተኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
የቅኔ መምህሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ

የቅኔ መምህሩ ዲበኩሉ ሽፈራዉ ከመቄት ወረዳ በረከዛ ኢየሱስ አካባቢ ወደ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸውን ወስደዋል፡፡

መምህር ዲበኩሉ የማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስክ ፈተናቸውን ከወሰዱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት "በዚህ ዕድሜዬ የምማረው ለወጣቶች አርአያ ለመሆንና ትምህርት ስለማይጠገብ ነው" ብለዋል፡፡

ውጤት ከመጣላቸው መማራቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡ ከተማሩ በኋላ ግን መስራት የሚፈልጉት በቅኔ መምህርነት መቀጠል እንደሆነ ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
አራስነት የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመውሰድ ያልገደባቸው እናቶች

14 አራስ እናቶች በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደዋል።

እነዚህ ብርቱ እናቶች ከ1 ወር እስከ 9 ወር ዕድሜ ያላቸውን ህጻናት ይዘው በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ፈተናቸውን ወስደዋል፡፡

ተፈታኝ ተማሪ እናቶቹ አስፈላጊው እንክብካቤ ተደርጎላቸው የ12ኛ ክፍል ፈተናቸውን በስኬት አጠናቀው በዛሬው ዕለት ወደየመጡበት አካባቢ ተሸኝተዋል።

@tikvahuniversity
#NATIONAL_EXAM

ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ዛሬ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል።

ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሐምሌ 9-11/ 2016 ዓ.ም በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በዚህም ተፈታኞች ሐምሌ 6 እና 7/2016 ዓ.ም ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል።

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመደቡለትን ተፈታኞች በዛሬው ዕለት መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ለተፈታኞቹ አጠቃላይ ገለፃ ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

በተያያዘ መረጃ፣ በትግራይ ክልል ሁለኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 9-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
ሀምዳ አህመድ ሁሴን ትባላለች። ነፍሰጡር መሆኗ የ12ኛ ክፍል ፈተናዋን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከመውሰድ አልገደባትም።

ነፍሰጡር ብትሆንም ብዙ የደከመችበትን የ12ኛ ክፍል ፈተና እንዲያመልጣት አልፈለገችም።

በፈተና ተቆጣጣሪዎች መልካም ፈቃድ፣ ተማሪ ሀምዳ ፈተናዋን ከሆስፒታል ሆና መውሰድ ችላለች።

ተማሪ ሀምዳ ህልማቸውን መኖር ለሚጥሩ ጥሩ የጥንካሬ ምሳሌ ናት።

@tikvahuniversity
በሰዎች ለሰዎች ድርጅት የሐረር አግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን 104 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል።

ምሩቃኑ ለአምስት ዓመታት በማኑፋክቸሪንግ፣ በኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ እንዲሁም በአውቶሞቲቭና አግሮ ኢኮሎጂ ቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች ስልጠናቸውን ተከታትለው ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#NATIONAL_EXAM

ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ዛሬ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል።

ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሐምሌ 9-11/ 2016 ዓ.ም በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ለተፈታኞቹ አጠቃላይ ገለፃ ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

በተያያዘ መረጃ፣ በትግራይ ክልል ሁለኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 9-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/06 09:19:46
Back to Top
HTML Embed Code: