Telegram Web Link
ተፈታኝ ተማሪዎች ወደቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ነው።

ላለፉት ሦስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያው ዙር አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ከሰዓት በተሰጠው የኢኮኖሚክስ ፈተና ፍፃሜውን አጊኝቷል።

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከረቡዕ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በወረቀት እና በኦንላይን በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተመረጡ የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
በአዲስ አበባ ከተማ ላለፉት ሦስት ቀናት የተሰጠው የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ የማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና ተጠናቋል፡፡

ፈተናው በወረቀት እና በበይነ መረብ በመዲናዋ በተለዩ 10 የፈተና ማዕከላት ሲሰጥ ቆይቷል።

የፈተናውን መጠናቀቅ ተከትሎ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል።

ሁለተኛው ዙር ፈተና ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
የ59 ዓመቱ አባት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናቸውን በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል።

አቶ አሊ ሁሴን ሀመዱ በአፋር ክልል ዞን አምስት በሚገኘው 'ደዌ ወረዳ' መሀመድ ቦዳያ ትምህርት ቤት ነው የተማሩት።

የ59 ዓመት ብርቱ አባት፤ ዕድሜያቸው እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸው ሳይበግራቸው ትምህርታቸውን አጠናቀው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸውን ወስደዋል።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪው አቶ አሊ፤ ለሌሎችም አርአያ በመሆን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን በ59 ዓመታቸው ተፈትነዋል።

@tikvahuniversity
ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ በርካታ ጎልማሳ እና የዕድሜ ባለፀጎች ይገኙበታል።

የ78 ዓመቱ አዛውንት ኢብራሂም ጎዳና፣ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ፈተናቸውን የልጅ ልጆቻቸው ከሚሆኑ ተማሪዎች ጋር ወስደዋል።

ትምህርታቸውን ለመማር እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ለመውሰድ ዕድሜ እንዳልገደባቸው አሳይተዋል።

@tikvahuniversity
ከሁለት ልጆቻቸው ጋር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱት እናት

ወ/ሮ መይረም እስማኤል አሊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸውን በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል። ወ/ሮ መይረም ብቻቸውን አልነበረም ፈተናውን የወሰዱት።

ሴት ልጃቸው ጦይባ አብደላ መሀመድ እና ወንድ ልጃቸው ኢብራሂም አህመድ ሀሰን አብረዋቸው ነበሩ። በክልሉ ከሚገኘው ዳሎል መሰናዶ ትምህርት ቤት የመጡት ሁለቱ ልጆቻቸውም በማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸውን ወስደዋል።

ለመማር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩት ወ/ሮ መይረም፤ የ12ኛ መልቀቂያ ፈተናውን በስኬት በማጠናቀቅ ለሌሎች እናቶችም አርአያ ሆነዋል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
ዛሬ ያበቃል! በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የተዘጋጀ "ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ" ፕሮግራም (National Cyber Talent Challenge Program) የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡ በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በቻሌንጁ ላይ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፤ Cyber Security, Cyber Development,…
ለ3ኛ ዙር ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ፕሮግራም የተመዝግባችሁና ለፈተና ያለፋችሁ ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ የሆናችሁ፤ ፈተናው ከሐምሌ 9-12/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) አሳውቋል፡፡

ወደ 3ኛ ዙር ፈተና ያለፋችሁ ስም ዝርዝር በአስተዳደሩ የሳይበር ታለንት ማዕከል የቴሌግራም አድራሻ https://www.tg-me.com/cteinsa በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፈተናው ፕሮግራም እንደሚከተለው ይሆናል፦

- ስማችሁ በ 'A' የሚጀምር ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጠዋት 3፡00
- ስማችሁ በ 'B', 'C' እና 'D' የሚጀምር ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ከሰዓት 7፡30
- ስማችሁ በ 'E', 'F', 'G', እና 'H' የሚጀምር ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ጠዋት 3፡00
- ስማችሁ በ 'I', 'J', 'K', እና 'L' የሚጀምር ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ከሰዓት 7፡30
- ስማችሁ በ 'M' እና 'N' የሚጀምር ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም ጠዋት 3፡00
- ስማችሁ በ 'O', 'P', 'Q', ‘R’, ‘S’ እና 'T' የሚጀምር ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም ከሰዓት 7፡30
- ስማችሁ በ 'U', 'V', 'W', ‘X’, ‘Y’ እና 'Z' የሚጀምር ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ጠዋት 3፡00

የፈተና ቦታ፦ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የ INSA ዋና ቢሮ

ለፈተና ስትሔዱ መታወቂያ መያዝን እንዲሁም ፕሮጀክት የምታቀርቡበት ላፕቶፕ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

ወደ 3ኛ ዙር ያለፋችሁ #የክልል ተፈታኞች ከ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቅ በኋላ በየአካባቢያችሁ እንደምትፈተኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/05 13:21:54
Back to Top
HTML Embed Code: