Telegram Web Link
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በደህንነት ካሜራ (CCTV) በመታገዝ እየሰጡ ይገኛሉ።

@tikvahuniversity
የተማሪ ወ/ሮ አታለለች ተመሳሌትነት

ተማሪ ወ/ሮ አታለለች አብርሃም የ11 ልጆች እናት ናቸው። ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ እንደሚሆን ይናገራሉ፡፡ 70 የልጅ ልጆችን እንዲሁም 13 የልጅ ልጅ ልጅ አይተዋል፡፡

ከአብራካቸው የተገኙትን 11 ልጆቻቸውን አስተምረው በልዩ ልዩ ሙያዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስመርቀው በስራ ዓለም እንዲሰማሩ አድርገዋል፡፡

ተማሪ ወ/ሮ አታለለች የወለዷቸውን ልጆች ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ድረስ በማስተማር ታላቅ የእናትነት ሚናቸውን ተወጥተዋል።

ተማሪ ወ/ሮ አታለለች ትውልዳቸው በሲዳማ ክልል ምስራቅ ሲዳማ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ ሲሆን በአሁን ወቅት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡

ትምህርታቸውን ካቋረጡ ከበርካታ ዓመታት በኋላ በ2012 ዓ.ም ካቆሙበት በመጀመር ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ በቅተዋል።

ተማሪ ወ/ሮ አታለለች ትናንት የተጀመረውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በመፈተን ላይ ይገኛሉ። #HawassaUniversity

@tikvahuniversity
"በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች ሌላ ዙር ፈተና ይዘጋጃል።" - ትምህርት ሚኒስቴር

በፀጥታ ችግር ምክንያት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች ሌላ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በመገኘት በሰጡት ማብራሪያ እንደገለፁ፥ የማካካሻ ትምህርት በመስጠት ከተቻለ በ2016 ዓ.ም መጨረሻ ካልሆነም በቀጣዩ የትምህርት ዘመን መጀመሪያ ሌላ ዙር ፈተና እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ድብልቅ በሆነ መልኩ በወረቀት እና በኦንላይን እየተሰጠ መሆኑንጨያነሱት ሚኒስትሩ፤ በቀጣይ መሰረተ ልማቶችን በማሟላትና የኢንተርኔት መቆራረጥ ችግርን በመፍታት የኦንላይን ፈተናው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity
#National_Exam

አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሁለተኛ ቀን ፈተናዎች ዛሬ ይሰጣሉ፡፡

በጠዋቱ መርሐግብር የስኮላስቲክ አፕቲትዩድ ፈተና የሚሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት የጂኦግራፊ ትምህርት ፈተና ይሰጣል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና እስከ ነገ ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ምስል፦ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
የ85 ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ

አቶ ታምሬ ጠናሞ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እየወሰዱ ከሚገኙ ተፈታኞች መካከል አንዱ ናቸው።

"ዕድሜ ትምህርትን አይገድብም" የሚሉት አቶ ታምሬ፥ በ72 ዓመታቸው ትምህርት ጀምረው በ85 ዓመታቸው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተፈታኙ አቶ ታምሬ ጠናሞ፥ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን እየወሰዱ ነው። #ASTU

@tikvahuniversity
ዲላ ዩኒቨርሲቲ የክረምት መርሐግብር ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም እንዲሁም የ PGDT ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚካሔደው ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ምዝገባ ለማድረግ በመንግሥት ስፖንሰርነት የምትማሩ የመገጣጠሚያ ደብዳቤ፥ መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ስፖንስርነት እና በግል የምትማሩ ደግሞ አስፈላጊውን የክፍያ ደረሰኝ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች በዋናው ግቢ፥ የማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች በኦዳያኣ ግቢ ሪፖርት አድርጉ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የክረምት መርሐግብር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ነባር ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም የሚካሔድ መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

@tikvahuniversity
💨 ⚡️ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️
  
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የ12ኛ ክፍል ተፈታኟ በፈተና ላይ እያለች ልጅ መውለዷ ተሠማ።

በክልሉ የምዢጋ ወረዳ የምዢጋ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ብሪቱ እምሩ፣ የዛሬ ጠዋት ፈተናዋን ካጠናቀቀች በኋላ ምጧ በመምጣቱ በአሶሳ ሆስፒታል ልጇን በሰላም የተገላገለች ሲሆን፤ የዛሬ ከሰዓት ፈተናዋንም ወስዳ አጠናቃለች።

ተማሪ ብሪቱ ልጇን በሰላም መገላገሏንና ፈተናዋንም መውሰድ በመቻሏ ደስተኛ መሆኗን ገልጻለች። ይህን ላደረገው ፈጣሪም ምስጋና አቅርባለች።

ባለቤቷ ተማሪ አለሙ ታምሩ የ12ኛ ከፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ሲሆን፤ ባለቤቱ ተማሪ ብሪቱ በሰላም በመውለዷ እና ፈተናዋን በማጠናቀቋ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

@tikvahuniversity
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የክረምት መርሐግብር ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም የ PGDT ሰልጣኞ የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አሳውቋል።

በትምህርት ሚኒስቴር ስፖንሰርነት ትምህርታችሁን የምትከታተሉ ሰልጣኞች ከምትሰሩበት መስሪያ ቤት መገጣጠሚያ፥ በተለያዩ ተቋማት ስፖንሰር አድራጊነት ትምህርታችሁን የምትከታተሉ ሰልጣኞች መገጣጠሚያና የክፍያ ደረሰኝ እንዲሁም በግል ትምህርታችሁን የምትከታተሉ ሰልጣኞች አስፈላጊውን የክፍያ ደረሰኝ በመያዝ በአካል በመቅረብ ምዝገባ ለ,ማድረግ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
የ79 ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ

የ12 ልጆች አባት ናቸው፡፡ ተማሪ በዛብህ ጡምዶሎ፡፡ በሀዲያ ዞን በጃቾ መሠናዶ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለው፣ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

እስከ 7ኛ ክፍል ድረስ ተምረው እንደነበርና በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ምክንያት ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን ይጠቅሳሉ። ከዛም በግብርና ሥራ ላይ መሰማራታቸውን ያነሳሉ፡፡

የመማር ፍላጎታቸው ከፍተኛ ስለነበር፣ ያቋረጡትን ትምህርታቸውን ቀጥለው ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

እኚህ አባት የሰው ልጅ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ትምህርት ለመማርና ዕውቀት ለመገብየት ዕድሜ እንደማይገድበው ጥሩ ተምሳሌት ናቸው፡፡ #ዋቸሞዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የክረምት መርሐግብር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ነባር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 18 እና 19/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የቲቶሪያል ትምህርት ከሐምሌ 20/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/01 22:42:42
Back to Top
HTML Embed Code: