Telegram Web Link
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን የመጀመርያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነገ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ለ5ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች በውጪ ፈታኞች የብቃት ምዘና ሰጥቷል።

በህክምና ትምህርት ቤት ስር የሚገኙ 35 የህክምና ተማሪዎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የፌደራል ሆስፒታሎች በመጡ ሲኒየር ሀኪሞች የብቃት ፈተናውን ወስደዋል።

በውጪ ፈታኞች (External Examiners) ከተፈተኑ 35 ተማሪዎች መካከል 29ኙ በተሻለ ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ሲሆን ቀሪዎች ለሦስት ወራት ያክል የጎደላቸውን በመሙላት ቀጣዩን ዙር እንደሚቀላቀሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተማሪዎች ሞዴል ፈተና እየተሰጠ ነው።

ሞዴል ፈተናው በክልሉ በሚገኙ አምስት ማዕከላት ማለትም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዋና ጊቢና ዱራሜ ካምፓስ፣ በወራቤ እና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም  ሆሳዕና ሊች ጎጎ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተሰጠ ነው።

በክልሉ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሚወስዱ ከ 47 ሺህ በላይ ተማሪዎች ውስጥ 1,401 ተማሪዎች በበይነ መረብ ይፈተናሉ ተብሏል።

ሞዴል ፈተናው እስከ ሰኔ 28/2016 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 96 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ።

@tikvahuniversity
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 1,700 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 20 በሦስተኛ ዲግሪ፣ 253 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ከ 1,400 በላይ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
#AssosaUniversity

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከ 1,500 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በክረምት መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 1,538 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 140 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረቁ ናቸው፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#JimmaUniversity ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 1,700 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 20 በሦስተኛ ዲግሪ፣ 253 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ከ 1,400 በላይ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው። @tikvahuniversity
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ውጤት የተመረቁት መንትዮቹ

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል መንትዮቹ ዮሴፍ ሞላወርቅ እና ሰለሞን ሞላወርቅ ይገኙበታል።

መንትዮቹ ከመዋለ ህጻናት ጀምሮ በአንድ ክፍል የተማሩ ሲሆን፤ በጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባዮ-ሜዲካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ትምህርታቸውን ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ተመሳሳይ የአጠቃላይ ውጤት (CGPA) እና ተቀራራቢ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ውጤት (71 እና 73) በማምጣት ተመርቀዋል።

@tikvahuniversity
#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ 42 የትምህርት መስኮች በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ተማሪዎቹ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በእረፍት ቀናት መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁና አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በኦንላይን ለሚወስዱ ተፈታኞች #ሞዴል_ፈተና ዛሬ ተሰጥቷል።

የሙከራ ፈተናው አብርሆት ቤተ-መፃሕፍትን ጨምሮ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የኦንላይን መፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠቱን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን አገር አቀፍ ፈተና፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስኬት ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ቢሮው ጠቁሟል።

ቢሮው ከኢትዮ ቴልኮም እና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 93.3 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 544 ተማሪዎች አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው 11ኛ ዙር ተመራቂዎች፣ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ተመራቂዎቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከ92 በመቶ በላይ በማምጣት ለምረቃ መብቃታቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ/ር) ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 2,300 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነቀምቴ ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 2,335 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ስልጠናቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
2024/09/30 09:23:58
Back to Top
HTML Embed Code: