Telegram Web Link
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

የነባር የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 2 እና 3/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

አዲስ የPGDT ኮርስ ተመዝጋቢዎች ምዝገባ ከሰኔ 25-30/2016 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

የክረምት ትምህርት ከሐምሌ 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል።

የፈተናው ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ በርካታ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን አድርሰውናል።

የፈተናው ውጤት መቼ ይገለፃል ስንል የጠየቅናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "በቅርቡ፥ ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት" ሲሉ መልሰውልናል።

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 3-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትናንት የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተና ለወሰዱ ተፈታኞች ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ከሰዓት እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡

በዚህም ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ላይ እንደሚሰጥ ተፈታኞች እና ፈታኞች እንዲያውቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ እና የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ዛሬ ከሰዓት ፈተናውን እንደሚወስዱ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#MekelleUniversity

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትናንት የተሰጡት የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ እና የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተናዎች ከተዘጋጀው ብሉ ሪንት ውጪ በመሆናቸው ፈተናዎቹ በድጋሜ እንዲሰጡ ተፈታኞቹ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ተወካይ በጉዳዩ ላይ ከተቋሙ አመራሮች ጋር የተወያየ ሲሆን፤ ፈተናዎቹ ከብሉ ፕሪንት ውጪ እንደተዘጋጁ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል፡፡ ይሁን እንጂ ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ከሰዓት እንደሚሰጥ ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በተመሳሳይ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም የተሰጠው የ Management የመውጫ ፈተና በተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት መሰረት የተዘጋጀ እንዳልነበር በርካታ ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
#AddisAbabaUniversity

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 29/2016 ዓ.ም በሚሌኒየም አዳራሽ ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
#EducationDiplomacy

መንግሥት የትምህርት ዲፕሎማሲን በማጠናከር
በ2016 ዓ.ም ለ865 የጎረቤት አገራት ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጥቷል።

እነዚህ ተማሪዎች በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

ነጻ የትምህርት ዕድል ካገኙት መካከል የደቡብ ሱዳን፣ የሶማሊላንድ እና የጅቡቲ ተማሪዎች ይገኙበታል።

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
#ዳሽን_ከፍታ: በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው "ዳሽን ከፍታ" የሥራ ፈጠራ ውድድር ሦስተኛ ምዕራፍ ሊጀመር ነው፡፡

በዳሸን ከፍታ የመጀመሪያው እና ሁለተኛው ዙር የሥራ ፈጠራ ውድድሮች ተሳትፈው አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሸልማትና የፋይናስ ድጋፍ አግኝተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ስኬታማ በመሆን ለሌሎችም የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ነዎት?

ዳሽን ከፍታ የሥራ ፈጠራ ውድድር በምዕራፍ ሦስት የቅድመ ውድድር ጅማሬ ስልጠና ለመስጠት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ይንቀሳቀሳል!

የስልጠና ቦታዎች፦ አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ አዳማ፣ መቐለ፣ ድሬዳዋ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታ፣ ጅማ እና ደሴ

ምዝገባ እስከ #ሰኔ_22/2016 ዓ.ም. ድረስ በሁሉም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች የሚካሔድ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ ወደ 6333 ይደውሉ ወይም የባንኩን የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይጎብኙ፡፡

ዳሸን ባንክ ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ!
አምቦ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በዕለቱ የህክምና ዶክተሮች፣ የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ እንዲሁም የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች እንደሚመረቁ ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር እስከ ነሐሴ ወር ድረስ 18.8 ሚሊዮን የመማሪያ መጻሕፍት ወደ አገር ውስጥ በማስገባት፣ ለመጪው የትምህርት ዘመን ለክልሎች ለማሠራጨት ዕቅድ መያዙን አስታወቀ፡፡

እስካሁን 20.7 ሚሊዮን የሁለተኛ ደረጃ የመማሪያ መጻሕፍት ታትመው አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ለክልሎች መሠራጨታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር የመማር ማስተማር ቁጥጥርና ሥርጭት ባለሙያ ዘሪሁን አሰግድ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተከሰተውን የመማሪያ መጻሕፍት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ወጥቶ የነበረውን ጨረታ ባሸነፈው የጃፓን ኩባንያ አማካይነት ኅትመቱ እየተከናወነ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በገጠመው የበጀት ችግር ምክንያት የመማሪያ መጻሕፍት ኅትመት በሁለት ዙሮች መደረጉንና እስከ መጪው ነሐሴ ወር ድረስ ቀሪ 18.8 ሚሊዮን የመማሪያ መጻሕፍት እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከዚህ በፊት ለሦስት ተማሪ አንድ መጻሕፍት ይዳረስ የነበረውን አሠራር፣ ለአንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ እንዲዳረስ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በሀረሪ ክልል ሲሰጥ የነበረው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ተጠናቋል።

5 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል።

ክልል አቀፍ ፈተናው በ29 የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰጥቶ በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሙያ ፍቃድና ምዘና ዳይሬክተር ዙኸራ ሙክታር ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
#TopTrainingInstitute

በሁለቱም ቅርንጫፎቻችን (ሜክሲኮ እና መገናኛ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ሁሉም ስልጠናዎች ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል!

አሁኑኑ ይመዝገቡ! ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ያለው!

የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Interior Design
🎯 Digital Marketing
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Website Design
🎯 Programming Language
🎯 Video Editing
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares (Peachtree,...)
🎯 Engineering Softwares
(Autocad, Etabs, Civil 3d, Reviet, ...)
🎯 SPSS and STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign and Local Languages

አድራሻ፦
1. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419

☎️ 0910317675 / 0991929303

Telegram: www.tg-me.com/topinstitutes
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በዕለቱ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች እንደሚመረቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#ExitExam

ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የመውጫ ፈተናው በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች በ51 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል።

ለፈተናው ከተመዘገቡት 169,790 ተማሪዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈተኑ 117,192 ተማሪዎች እንዲሁም 52,598 ተማሪዎች ደግሞ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት የጥራትና ብቃት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ገልፀዋል።

የመውጫ ፈተና ውጤት በቅርቡ እንደሚለቀቅ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ?

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተናቸውን ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ማጠናቀቃቸው ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ትናንት ሰኔ 19/2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡

የፈተናዎቹ ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ኃላፊው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
2024/07/01 00:22:14
Back to Top
HTML Embed Code: