Telegram Web Link
#ETA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2015 ዓ.ም እና በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎችን ዝርዝር እንዲልኩ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል።

ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣችሁ ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ ያስመረቋቸውንና ከዚህ በፊት ያልተላኩ የተመረቁ ተማሪዎች መረጃንም እንዲልኩ ተብሏል።

በዚህም መረጃዎቹን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሀርድ ኮፒ እንድትልኩ ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ለፈተና የሚጠቀሙበትን የይለፍ ቃል ከላይ ባሉት ሊንኮች በመግባት መቀየር ይችላሉ።

@tikvahuniversity
#MoH

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፦
- በነርሲንግ፤
- ሜዲስን፤
- ጤና መኮንን፤
- አንስቴዥያ፤
- ፋርማሲ ፤
- ሜዲካል ላቦራቶሪ፤
- ሚድዋይፈሪ፤
- ዴንታል ሜዲስን፤
- ሜዲካል ራዲዮሎጂ፤
- ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ፤
- ፔዲያትሪክ ኤንድ ቻይልድ ሄልዝ፤
- ሳይካትሪ ነርሲንግ፤
- ኢመርጀንሲ ኤንድ ክሪቲካል ኬር ነርሲንግ ፤
- ሰርጅካል ነርሲንግ፤
- ኦፕቶሜትሪ፤
- ፊዚዩቴራፒ እንዲሁም ሂውማን ኒውትሪሽን ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ተመዝግበው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ አዲስ እጩ ምሩቃን የጤና ባለሙያዎች ፈተናው ከትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ጋር በጋራ ሰኔ 19/ 2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

ለዚህም ፈተና ተመዛኞች መዘጋጀት እና በፈተናው ወቅት በጠዋትም በከሰዓትም ክፍለ ጊዜ አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረማቸውን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል።

በተጨማሪም ፦
° በሰርጅካል ነርሲንግ፤
° ኦፕቶሜትሪ፤
° ፊዚዩቴራፒ እንዲሁም ሂውማን ኒውትሪሽን ሙያዎች የሚመረቱ ባለሙያዎች ከሰኔ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሙያ ፈቃድ ለማግኘት የብቃት ምዘና ፈተና የሚጠበቅባቸው መሆኑን
አውቀው ከወዲሁ ከላይ በተጠቀሰው የፈትና ወቅት ዝግጅት አድርገው እንዲቀርቡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahuniversity
በትግራይ ክልል ለሦስት ተከታታይ ቀናት የተሰጠው የ8ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቋል።

122 ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተናውን ወስደዋል።

በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና በ1,129 ትምህርት ቤቶች መሰጠቱን የክልሉ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ታደሰ ካህሳይ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ ፈተናው በሰላም መጠናቀቁን ኃላፊው ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
#ExitExam

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል፡፡

የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ለፈተናው በድጋሜ የሚቀመጡ ተማሪዎች ለሦስተኛ ጊዜ እየተሰጠ የሚገኘውን ፈተና ይወስዳሉ፡፡

ተፈታኞች የማኔጅመንት፣ የጂኦሎጂ እና የሕዝብ አስተዳደርና ዴቨሎፕመንት ማኔጅመንት ፈተናዎችን ዛሬ ሙሉ ቀን የሚወስዱ ይሆናል፡፡

ተሻሽሎ የወጣው የመውጫ ፈተና መርሐግብር፤ ሀገር አቀፍ ፈተናው እስከ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል፡፡

ምስል፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

በተለያየ ምክንያት ዛሬ የተሰጡትን የ Management, Business Administration, Business Management እና Business Management and Entrepreneurship ፈተና ያልወሰዳችሁ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ነገ ቅዳሜ ሰኔ 15 /2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ፈተናው ስለሚሰጥ ወደየተመደባችሁበት ተቋም በመሔድ መፈተን የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሁሉም ተፈታኞች User Name Password በመያዝ ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት የፈተና ጣቢያ መገኘት እንዳለባችሁ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል ላለፉት ሁለት ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ተጠናቋል፡፡

በክልሉ ሰኔ 13 እና 14/2016 ዓ.ም የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መጠናቀቁን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከ170 ሺህ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ከዚህ ቀደም ያሳወቀው ቢሮው፤ ምን ያህሉ ፈተናው እንደወሰዱ አልገለፀም።

በክልሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ለፈተናው ምዝገባ አለማድረጋቸው ይታወቃል።

@tikvahuniversity
አዲስ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ወደ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ።

አዋጁ የአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርትን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በፍትሐዊነት ለማዳረስ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር እና የትምህርትን ጥራት፣ ተደራሽነት እና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

አዋጁ የትምህርት አግባብነትን፣ ስርዓተ ትምህርትን፣ የትምህርት ተቋማት አደረጃጀትን እና መምህራንን የሚመለከቱ ሙያዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የያዘ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የትምህርት ተቋማት ደረጃ ማውጣትን እና ከመንግሥት ውጭ ባሉ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚደረግ ቁጥጥርን በተመለከተ ድንጋጌዎችን አካቶ የቀረበ የሕግ ማዕቀፍ መሆኑ የሚኒስትሮች ም/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ምክር ቤቱ በቀረበው አዋጅ ላይ የተወያየ ሲሆን ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።

@tikvahuniversity
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 5ኛ አመት ተመራቂ ተማሪዎች " ከሁለት አመት በፊት Add አድርገን መጨረስ የምንችላቸውን ኮርሶች በዩኒቨርሲቲው ምክንያት ባለመውሰዳችን የመውጫ ፈተና ላይም መቀመጥም ሆነ የመመረቂያ አዳራሽ ውስጥ እንዳንገኝ ዩኒቨርሲቲው ወስኖብናል " በማለት ቅሬታቸውን ለቲክቫህ አቅርበዋል።

" ከሁለት አመት በፊት ከ በግዜው በኮቪድ ምክንያት በክረምት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከነበሩ ተማሪዎች ጋር አድ አድርገን መጨረስ እንችል ነበር " ያሉት ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ከመደበኛ ተማሪዎቹ ጋር መማር አትችሉም የሚል ህግ አውጥቶ እንዳይማሩ እንዳገዳቸው አሳውቀዋል።

በክረምት መማር አትችሉም የተባሉት ተማሪዎች በቀጣዩ አመት ነገሮች እንዲመቻች ይደረግላችሁኋል በማለት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕ/ት ቃል ገብተውላቸው እንደነበር አስረድተዋል።

ከዛ በኋላ መስከረም ላይ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕ/ት ሂዱና የትምህርት ክፍላችሁን አናግሩ በማለት መፍትሄ እንዳልሰጧቸው እና በድጋሚ የቀሩትን ኮርሶች በቀጣዩ ክረምት ትወስዳላችሁ ተብሎ ቃል ቢገባላቸውም ቃሉ እንዳልተጠበቀላቸው ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎም ኮርሶቹን ባለመጨረሳቸው ለመውጫ ፈተናም መቀመጥ እንዳይችሉ እንደተደረጉ የገለፁት ተማሪዎቹ በተጨማሪም የምረቃ ስነስርዓት ላይ እንዳይገኙ እንደተወሰነ ጠቁመዋል።

ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መፈተን እንዳይችሉ ከመደረጋቸው ባሻገር "ቤተሰብ ይመረቃሉ ብሎ ቢጠብቀንም መመረቂያ አዳራሽ ውስጥ እንኳን እንዳንገባ ወስነውብናል" የሚል ቅሬታቸውን በማቅረብ ዩኒቨርሲቲው ይህንን እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ጉዳዩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባ በሚገኙ 183 የመፈተኛ ጣቢያዎች ከሰኔ 12-14/2016 ዓ.ም ለተከታታይ ሦስት ቀናት የተሰጠው ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ፈተናውን መውሰድ ካልቻሉ ጥቂት ተማሪዎች በስተቀር አብዛኞቹ ተማሪዎች መፈተናቸውን በቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ገልፀዋል፡፡

በአማርኛ ስርዓተ ትምህርት ለሚማሩ ተማሪዎች በአምስት እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናውን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity
#ማስታወሻ

ትናንት የተሰጡትን የ Management, Business Administration, Business Management እና Business Management and Entrepreneurship የመውጫ ፈተና በተለያየ ምክንያት ያልወሰዳችሁ ተፈታኞች ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 15 /2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ፈተናው ስለሚሰጥ ወደየተመደባችሁበት ተቋም በመሔድ መፈተን የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ተፈታኞች User Name Password በመያዝ ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት የፈተና ጣቢያ መገኘት አለባችሁ ተብሏል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ማሰልጠኛ ማዕከል የመጀመሪያ ዙር 60 ሰልጣኞችን መቀበል ጀምሯል።

ምዝገባው የሚያበቃው፦
ሰኔ 19/2016 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦
CSSH ህንጻ 1ኛ ፍሉር R-10

ለተጨማሪ መረጃ፦

0977945129 / 0916159720
Email: [email protected]

@tikvahuniversity
#ExitExam

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የሁለተኛ ቀን ፈተናዎች እየተሰጡ ነው፡፡

የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እና በድጋሜ ተፈታኞች ለሦስተኛ ጊዜ እየተሰጠ የሚገኘውን ፈተና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

የአካውንቲንግ እና ሕግ ፈተናዎችን ጨምሮ የሰባት ትምህርት አይነት ፈተናዎች ዛሬ ሙሉ ቀን እየተሰጡ ነው፡፡ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተናው እስከ ሰኔ 19/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ምስል፦ ቦረና፣ አዲግራት እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
2024/09/29 21:28:01
Back to Top
HTML Embed Code: