Telegram Web Link
በአዲስ አበባ የሚገኙ 35 ትምህርት ቤቶች ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንዳያካሒዱ ዕገዳ ተጣለባቸው።

በከተማዋ የሚገኙ 35 የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንዳያካሒዱ ማገዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሳውቋል።

ትምህርት ቤቶቹ በዋናነት በትምህርት ፖሊሲ ጥሰት፣ በትምህርት ስታንዳርዱ መሰረት ከ75 በመቶ በታች ያመጡ እንዲሁም የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን በአግባቡ አለመጠቀም የታየባቸው በመሆኑ ዕግዱ እንደተጣለባቸው ባለስልጣኑ ገልጿል።

ዕግዱ ከተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል የጊብሰን ትምህርት ቤቶች፣ የቅዱስ ሚካኤል አምስት ትምህርት ቤቶች እና የካ አፖሎ ትምህርት ቤት እንደሚገኙበት የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዳኛው ገብሩ ተናግረዋል።

ዕገዳ በተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በመኖረያ አቅሪያቢያቸው በሚገኙ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ እንዲስተናግዱ ይደረጋል ብለዋል።

ሌሎች 41 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው መሰረዙን የገለፁት ኃላፊው፤ የ150 ትምህርት ቤቶች ጉዳይ በሒደት ላይ እንደሆነና ወደፊት እንደሚገለፅ ተናግረዋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ተማሪዎችን መዝግበው እንዲያስተምሩ ፈቃድ የተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች 1,332 መሆናቸውን ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity
Schedule of Exit Exam.xls
280.5 KB
#ExitExamSchedule

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

የመውጫ ፈተና ጊዚያዊ መርሐግብር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahuniversity
የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ̔ፕሬዝዳንሻል ሜንተርሽፕ̔ ሰልጣኞች በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ፡፡

የሜንተርሽፕ ፕሮግራሙ በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እና በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች የተለያዩ ክህሎቶች ማሳደጊያ የማማከር ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ከአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየ ዙር ስልጠናውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች የምርቃት እና የፕሮጀክቱ ማጠቃለያ መርሐግብር ተካሄዷል፡፡

በአጠቃላይ በአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥራቸው 500 የሚሆኑ የፕሬዝዳንሻል ሜንተርሺፕ ስልጠና (Presidential Mentorship Program) ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡

ፕሮግራሙ በ Institute of International Education አማካኝነት በአመራር ብቁ የሆኑ ሴቶችን ለማፍራት ከአራት ዓመት በፊት የተጀመረ መርሐግብር ነው፡፡ #AASTU

@tikvahuniveristy
2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል።

የዘንድሮው የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና ከሰኔ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን ሲሰጥ ቆጥቷል።

በዛሬው ዕለት የተፈጥሮ ሳይንስ ሪሚዲያል ተማሪዎች የኬሚስትሪ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ከታህሳስ ጀምሮ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 78 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ለስምንት ቀናት የተሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑ ይታወቃል።

ምስል፦ አምቦ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ "የተማሪዎቹን ደህንነት" በተመለከተ በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች እየተናፈሰ ያለው መረጃ ሐሰት መሆኑን ገለፀ፡፡

ሐሰተኛ መረጃዎቹ "የፆታዊ ጥቃት መከሰታቸውን እንዲሁም የተማሪዎች ህይወት ማለፉን" የሚገልጹ ሲሆን፤ አሉባልታዎቹ ሙሉ በሙሉ ሐሰት መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡

"የተማሪዎቻችንን ደህንነት ማስጠበቅ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው" ያለው ዩኒቨርሲቲው፤ በተቋሙ ውስጥ ምንም አይነት ፆታዊ ጥቃት፣ ጉዳት እና ሞት አልተፈጠረም ብሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የአሉባልታዎቹን ምንጭ አጣርቶ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቋል፡፡ ሐሰተኛ መረጃዎቹን ያሰራጩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች የትኞቹ እንደሆኑ ዩኒቨርሲቲው አልገለፀም፡፡

@tikvahuniveristy
በትግራይ ክልል ከ122 ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።

በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና በ1,129 ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ እንደሚገኝ የክልሉ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ታደሰ ካህሳይ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ይሰጣል፡፡ ምስል፦ @ProfKindeya

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል፡፡

በአዲስ አበባ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና በ183 ጣቢያዎች እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ከተማ አቀፍ ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ቀናት ይሰጣል።

@tikvahuniversity
ይለማመዱ!

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የኦንላይን የመፈተኛ ፕላትፎርም አጠቃቀምን ይለማመዱ!

ፕላትፎርሙን እንዴት መጠቀምና እንዴት ፈተናውን መውሰድ እንደሚቻል ለማሳየት በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተዘጋጀን የአራት ደቂቃ ገላጭ ቪዲዮ በተከታዩ ሊንክ በመግባት ይመልከቱ፡፡ ራስዎን ለፈተናው ያዘጋጁ!

ቪዲዮውን ይመልከቱ 👇
https://www.youtube.com/watch?v=PdAu-FI-Q5M


@tikvahuniversity
EXIT EXAM Schedule - Revised.xls
196.5 KB
#RevisedExitExamSchedule

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከአርብ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

የመውጫ ፈተና የተሻሻለ መርሐግብር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahuniversity
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይመልከቱ ፦ ይህ የመውጫ ፈተና የተመለከተ አጭር ቪድዮ የይለፍ ቃል (Password) እንዴት መቀየር እንደሚቻል ፣ ተፈታኞች በፈተና ወቅት መከተል ስላለባቸው ጉዳዮች ያሳያል።

#MoE

@TikvahUniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ላልሆኑ የተቋሙ ተማሪዎች የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት ከነገ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደማይሰጥ አሳውቋል።

ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ግን አገልግሎቶቹ መሰጠት እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ሰኔ 13/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይሰጣል፡፡

170 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወሳል።

በፀጥታ ችግር ምክንያት 99 ሺህ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና እንደማይቀመጡ የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን ለአሜሪካ ድምፅ ሰሞኑን መናገራቸው አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
አምቦ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ገለፃ ሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከአምቦ ከተማ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ገለፃውን የሰጠ ሲሆን፤ የተማሪዎቹን የስነ-ልቦና ዝግጁነት ለማጎልበት ያስቻለ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በአምቦ ከተማ ከሚገኙ ሰባት የሁለተኛ ደረጃ፣ የመሰናዶ እና የአዳሪ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በመርሐግብሩ ተሳትፈዋል፡፡

@tikvahuniveristy
የአውሮፓ ህብረት ለ48 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የኢራስመስ+ ሁለተኛ ዲግሪ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ገለፀ፡፡

ዕድሉ ተማሪዎቹ በ12 አገራት በሚገኙ ታዋቂ የአውሮጳ ዩኒቨርሲቲዎች የማስተርስ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለሁለት ዓመታት (2024-2025) እንዲከታተሉ የሚያስችላቸው ነው፡፡

ኢትዮጵያ የአውሮጳ ህብረት ኢራስመስ+ ስኮላርሺፕ ፕሮግራም ተጠቃሚ ከሆኑ ቀዳሚ አገራት አንዷ ነች። የአውሮጳ ህብረት ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ከ600 ለሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የኢራስመስ ሁለተኛ ዲግሪ ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጥቷል፡፡

@tikvahuniveristy
መንገሻ አየነ (ዶ/ር) የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመደቡ፡፡

መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ከሰኔ 12/2016 ዓ.ም ጀምሮ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸውን ሰኔ 10/2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ የወጣ የምደባ ደብዳቤ ያሳያል፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ፤ ፕ/ር እሰይ ከበደ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው በመወከል ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

አዲስ የተመደቡት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ፤ ከመስከረም 2014 ዓ.ም ጀምሮ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።

ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሰጠ የሚገኘውን ፈተና፤ ከ170 ሺህ በላይ ተፈታኞች በ4,355 ትምህርት ቤቶች እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

በፀጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ 99 ሺህ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሁለት ቀናት የሚሰጠውን ፈተና እንደማይወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለፁ አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
2024/09/29 19:32:53
Back to Top
HTML Embed Code: