Telegram Web Link
#MondayMotivation

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱ ይታወቃል። የማዕረግ እድገቱን ካገኙት መካከል ሁለቱ ሴት ምሁራን ናቸው።

ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወልደአማኑኤል በሜዲካል ማይክሮባዮሎጂ መስክ 30 ጥናታዊ ፅሁፎችን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች በማሳተም የሙሉ ፕሮፌሰርነት የማዕረግ እድገት አጊኝተዋል።

ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት መስክ ዘጠኝ ጥናታዊ ፅሁፎችን በዓለም አቀፍ ተፅዕኖ አሳዳሪ ጆርናሎች በማሳተም የሙሉ ፕሮፌሰርነት የማዕረግ እድገት አጊኝተዋል።

በተጨማሪም ምሁራኑ በማስተማር ውጤታማነት እና በአካዳሚያዊ አገልግሎት ከፍተኛ አበርክቶ ያደረጉ ናቸው።

@tikvahuniversity
#EthiopianAviationUniversity

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የአቪዬሽን የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 800 የሚጠጉ ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በአውሮፕላን አብራሪነት፣ በበረራ መስተንግዶ፣ በማርኬቲንግ እና በአውሮፕላን ጥገና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 787 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከስምንት የአፍሪካ አገራት እና ከአንድ የኤስያ ሀገር የተውጣጡ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ካሴ ይማም ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
#SummerVoluntaryService

20 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ይሳተፋሉ።

የዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ሰላም ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ይካሔዳል።

በንቅናቄው ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ39 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሏል።

በዘንድሮው መርሐግብር በ14 መስኮች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚሰጡ ሲሆን፤ ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ነው የተገለፀው።

የአረንጓዴ አሻራ፣ ትምህርት እና የጤና አገልግሎት ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል ይገኙበታል ተብሏል።

20 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተለያዩ አካባቢዎች በበጎፈቃድ አገልግሎቱ እንደሚሳተፉ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ ተናግረዋል።

ንቅናቄው ረዕቡ ሰኔ 12/2016 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ይጀመራል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ በ2017 የትምህርት ዘመን በተለያዩ ምክንያቶች ምዝገባ እንዳያካሒዱ ዕገዳ የተጣለባቸው 35 ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ በ2017 የትምህርት ዘመን በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸው 41 ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ።

@tikvahuniversity
2024/09/29 17:26:38
Back to Top
HTML Embed Code: