Telegram Web Link
"ዘንድሮ በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና ጎን ለጎን ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መንግሥት በሚያዘጋጃቸው ኮምፒውተሮች ይከናወናል፡፡" - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት እንዲሁም በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች የራሳቸውን ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ ተወስኗሉ የሚሉ መረጃዎች ሲዘዋወሩ ታይቷል፡፡

"ይህንን በተመለከተ ለትምህርት ቤቶች የተላለፈ መልዕክት አለመኖሩንና ወላጆች ኮምፒውተር እንዲያዘጋጁ መጠየቃቸውም ተገቢ አለመሆኑን" የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

"ፈተናው መንግሥት በሚያዘጋጀው የኮምፒውተር አቅርቦት ይከናወናል" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ "ተማሪዎች አንብበውና በቂ ዝግጅት አድርገው የተመዘገቡበትን መታወቂያ ብቻ ይዘው መምጣት ነው የሚጠበቅባቸው" ብለዋል፡፡ "ሆኖም ትምህርት ቤቶችም ሆኑ ተማሪዎች የግል ኮምፒውተሮቻቸውን ለፈተናው መጠቀም ከፈለጉ እንደማይከለከሉ" ተናግረዋል፡፡

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በልምምድ ላይ እንደሚገኙ ያነሱት ኃላፊው፤ 156 የኮምፒውተር ባለሙያዎች ሰልጥነው በክልሎች ስልጠና እንዲሰጡ መሰማራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዘንድሮው ፈተና ልምዶችን በመያዝ፤ በሚቀጥሉት ከ3 እስከ 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የመስጠት ዕቅድ መኖሩን ገልፀዋል፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

@tikvahuniversity
የዶክትሬት ዲግሪ በ17 ዓመቷ

ዶሮቴ ዢን ቲልማን ትባላለች፡፡ በ17 ዓመቷ የዶክትሬት ዲግሪዋን በመያዝ በዓለማችን በልጅነቷ የሦስተኛ ዲግሪ የያዘች ሆናለች።

ከህጻንነቷ ጀምሮ በትምህርቷ አስደናቂ የነበረችው ታዳጊዋ፤ ገና በሰባት ዓመቷ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቷን በመከታተል ላይ ነበረች፡፡ 

ጥቂት መረጃዎች ስለዚች አስደናቂ ተማሪ

በ10 ዓመቷ በስነ-ልቦና ትምህርት የአሶሼት ዲግሪዋን ከኢሊኖዩ ሌክ ካውንቲ ኮሌጅ አጊኝታለች።

በ12 ዓመቷ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በስነ-ሰብ ትምህርት ከኒውዮርኩ ኤክሰልስዮ ኮሌጅ ወስዳለች።

በ14 ዓመቷ በሜን ግዛት ከሚገኘው ዩኒቲ ኮሌጅ በስነ-ሰብ ትምህርት የማስተርስ ዲግሪዋን ተቀብላለች።

በ17 ዓመቷ ደግሞ የዶክትሬት ዲግሪዋን በተቀናጀ የባህሪ ጤና መስክ ከአሪዞና ስቴት የጤና ሶሉሽንስ ኮሌጅ በመውሰድ አስደናቂ ታሪክ ፅፋለች።

ለዶክትሬት ዲግሪዋ በሠራችው የመመረቂያ ጥናት፥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአዕምሮ ህክምና ለማግኘት የሚገጥማቸውን መገለል ለመቀነስ የሚያስችል ፕሮግራም ላይ ምርምር አድርጋለች።

እቺ አስደናቂ ታዳጊ ገና ምርጫ እንኳን ለመምረጥ በምትችልበት እድሜ ላይ ሳትደርስ በትምህርቷ አስገራሚ ነገሮችን ማሳካቷ በርካቶችን እያነጋገረ ነው፡፡

(ዋቢ፦ CNN and The New York Times)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለወጣቶች በቤት አያያዝ ሙያ (Domestic Work) የአጭር ጊዜ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

ስልጠናውን መከታተል የምትፈልጉ ወጣቶች ከግንቦት 18 እስከ 23/2016 ዓ.ም ድረስ በኢንስቲትዩቱ ግቢ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 3 በሥራ ሰዓት በመገኘት መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል።

ስልጠናው ሰኔ 1/2016 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

የምዝገባ መስፈርቶች፦

➧እድሜ ከ 18 እስከ 35 ዓመት
➧ስምንተኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች
➧ለ21 ቀናት ሳያቆራርጡ መሰልጠን የሚችሉ
➧የብቃት ምዘና ለመመዘንና ለመመዝገቢያ 100 ብር ያስፈልጋል።

@tikvahuniversity
ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች

በኢትዮጵያ በፀጥታ ችግር ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው፡፡ በ2016 ዓ.ም 8.8 ሚሊዮን ተማሪዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት 8,977 ትምህርት ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 6,483 ሙሉ በሙሉ ዝግ እንደሆኑ ሚኒስቴሩ ይገልፃል፡፤

በግጭት ውስጥ በሚገኘው አማራ ክልል ብቻ ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ 2.6 ሚሊዮን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መሔድ እንዳልቻሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ዛሬ ባጋራው መረጃ ደግሞ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ውስጥ 33 በመቶ የሚሆኑት ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የተዘጋጀ "ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ" ፕሮግራም (National Cyber Talent Challenge Program)

በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

የታለንት መስኮች፦

➧ Cyber Security
➧ Cyber Development
➧ Embedded Systems
➧ Aerospace

የመመዝገቢያ ጊዜ፦
ከግንቦት 15-30/2016 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ፦
0904311833
0943579970
0904311837


ለመመዝገብ፦ https://talent.insa.gov.et
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ 9ኛ ዓመታዊ የምርምር ጉባኤውን ማካሔድ ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው "ተግባር ተኮር ምርምር እና የፈጠራ ሥራ ለዘላቂ ልማት" በሚል ጭብጥ ላይ ጉባኤውን እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ ከትምህርትና ሥልጠና በተጓዳኝ የህብረተሰቡን ችግር ለሚፈቱ የምርምር ሥራዎች ትኩረት ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከማል አብዱራሂም (ዶ/ር) ተናግረዋል። ከምርምሮቹ መካከል የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጡ ሥራዎች ዋነኞቹ እንደሆኑ ገልፀዋል።

የምርምር ኮንፍረንሱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይካሔዳል።

@tikvahuniversity
የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀው የተማሪዎች የሳይንስ ፈጠራ አውድ ርዕይ በወዳጅነት አደባባይ ተከፍቷል፡፡

በከተማዋ ከሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ ተማሪዎች እና መምህራን የተሠሩ የፈጠራ ውጤቶች በአውደ ርዕዩ ላይ ቀርበዋል፡፡

አውደ ርዕዩ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

@tikvahuniversity
ተቋማት ዛሬ መላክ ይጠበቅባቸዋል!

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎቻቸውን መረጃ ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እንዲልኩ የተሰጣቸው ጊዜ ዛሬ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም ያበቃል፡፡

ተቋማቱ የተፈታኞቻቸውን መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ቴምፕሌት በመጠቀም መላክ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ መግለፁ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚያሳትመው የአፍሪካ ኢኮኖሚክስ እና ቢዝነስ ሪሰርች ጆርናል በአፍሪካ ጆርናሎች ኦንላይን ድረ-ገጽ ላይ ተካቷል።

ዩኒቨርሲቲው የሚያሳትመው ጆርናል (African Journal of Economics and Business Research) በአፍሪካ ጆርናሎች ኦንላይን (AJOL) ድረ-ገጽ ላይ መካተት ችሏል።

ጆርናሉ በፋይናንስ፣ ቢዝነስ፣ ኢኮኖሚክስ እና ልማት መስኮች ላይ ትኩረት ያደረጉ የፖሊሲ እና ችግር ፈቺ ምርምሮች የሚቀርቡበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ጆርናል በአፍሪካ ጆርናሎች ኦንላይን (AJOL) ድረ-ገጽ ላይ መካተቱ ተደራሽነቱንና ተነባቢነቱን የበለጠ እንደሚጨምረው ዩኒቨርሲቲው ግልጿል፡፡

African Journals Online (AJOL) ለማግኘት፦ https://www.ajol.info/index.php/ajebr

@tikvahuniversity
2024/09/29 23:22:27
Back to Top
HTML Embed Code: