Telegram Web Link
#Update

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኦንላይን ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆኗል፡፡


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ብቻ ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

በመሆኑም ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ የበይነ መረብ ተፈታኞች ባሉበት ሆነው ልምምድ ማድረግ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል/ከተማ አስተዳደር የተላከውን የይለፍ ቃል እና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡

በዚሁ መሠረት መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች ከተደለደሉበት ክላስተር ውጪ ሲስትሙን መጠቀም #እንደማይችሉ አገልግሎቱ አሳስቧል።

(ፈተናው የሚሰጥበት አድራሻ እና ተፈታኞቹ የሚገኙበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የተገነባ የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ተመርቋል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነባ ሲሆን፤ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ግንባታው መከናወኑ ተገልጿል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ከ300 በላይ አይነ ስውራን ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተማር አቅም አለው ተብሏል።

ለአይነ ስውራን ምቹ የሆኑ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መፃሕፍት እና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን መያዙ ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳሪ ትምህርት ቤቱን መረከቡ ታውቋል።

@tikvahuniversity
በሳምንቱ መጨረሻ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበር ተቋሙ አሳውቋል።

በዩኒቨርሲቲው ብሎክ አራት 4ኛ ፎቅ አንድ ዶርም ላይ "ተከስቶ የነበረው መጠነኛ የእሳት አደጋ የከፋ አደጋ ሳያደርስ ወዲያው በቁጥጥር ስር መዋሉን ተቋሙ ገልጿል።

@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን ለሚወስዱ የተዘጋጀ መለማመጃ

በተቀመጠው መመሪያ መሠረት የኦንላይን ፈተናውን ይለማመዱ።

@tikvahuniversity
ሰላም ሚኒስቴር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አምባሳደሮች 10ኛ ዙር ስልጠና መርሐግብር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስጀምሯል፡፡

ሚኒስቴሩ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሚሰጠው ስልጠና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 2,000 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አምባሳደሮች ለ33 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል፡፡

ሚኒስቴሩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በዘጠኝ ዙሮች ከ47 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ አምባሳደሮችን አሰልጥኖ ማስመረቁ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#ጥቆማ ጤና ሚኒስቴር የሚያስተዳድራቸውን አዲስ የህክምና ትምህርት ኢንሼቲቭ (NMEI) ትምህርት ቤቶች መቀላቀል የምትፈልጉ ዕጩዎች ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ ሚኒስቴሩ በNMEΙ ስርዓተ ትምህርት የቅበላ ፖሊሲ መሰረት፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ አዲሱን የህክምና ትምህርት ኢንሼቲቭ (NMEI) ለመቀላቀል ፍላጎት ያላቸውን ዕጩዎች እንዲመለምል፣ የመግቢያ ፈተና እንዲሰጥ እና ውጤት እንዲያሳውቅ…
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለጤና ሚኒስቴር አዲስ የህክምና ትምህርት ኢንሼቲቭ (NIMEI) 2016 ዕጩ ተወዳዳሪዎች በቅርቡ ሰጥቶት የነበረውን የፅሁፍ ፈተና ውጤት በሙሉ ሰርዟል፡፡

ስለተፈጠው ነገር ኮሌጁ ምን አለ?

በፈተናው ውጤት ላይ ቅሬታ ካቀረቡ አስር ተፈታኞች ውስጥ ስምንቱ የቃል ፈተና ላይ ሊካተቱ ችለዋል፡፡ በአንፃሩ አንድ ተፈታኝ ለቃል ፈተናዉ ያላለፈ፣ ነገር ግን ቅሬታ አቅርቦ በእጅ በሚታረምበት ወቅት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ ቃል ፈተናዉ ተካቶ ነበር፡፡

ተፈታኞች የተሳሳተ የኮድ አጠቋቆር በመጠቀማቸው ፈተናው የራሱ ባልሆነ ኮድ መታረሙ ኮሌጁ ገልጿል፡፡ አንዳንድ ተፈታኞች ከተሰጠው ቦታ ውጪ በማጥቆራቸውና ሌሎች ደግሞ በደንብ ባለማጥቆራቸው በዕርማት ወቅት የኮምፒውተር ስህተት ማስከተሉ ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ በእጅ ሲታረም ግን ትክክል ሆኖ መገኘቱን ኮሌጁ ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም "የሁሉንም ተፈታኞች መብት ለማስጠበቅና የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረም" የሁሉም የመልስ መስጫ ወረቀቶች በእጅ እንዲታረሙ መደረጉን ኮሌጁ ገልጿል፡፡ በዚህም ሁሉም የተለጠፉ የፈተና ውጤቶች መሰረዛቸውን ኮሌጁ አረጋግጧል፡፡ ለግንቦት 11/2016 ዓ.ም ተይዞ የነበረው የቃል ፈተናም መሰረዙን ገልጿል፡፡

ሁሉም የፈተና ውጤት በእጅ ከታረመ በኃላ ለቃል ፈተናው ብቁ የሆኑትን የስም ዝርዝር በድጋሚ በድረ-ገጽ እንደሚለጠፍ ኮሌጁ አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ዕጩ የቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር #ሞዴል የመውጫ ፈተና መስጠት ጀምሯል፡፡

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይወቃል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለዕጩ የቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎቻቸው #ሞዴል የመውጫ ፈተና እንዲሰጡ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ያስገድዳል፡፡

@tikvahuniversity
2024/09/29 19:31:40
Back to Top
HTML Embed Code: