Telegram Web Link
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ዋና መግቢያ በር ተመርቋል፡፡

የግብርና ውጤቶችን የሚያመርተው ዩኒቨርሲቲው፤ በተቋሙ የውስጥ ገቢ የተገነባን የምርት መሸጫ ማዕከልም አስመርቋል፡፡

በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲው በ21 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባው የአረጋውያን ማዕከል አስመርቋል፡፡

104 ደጋፊ የሌላቸው አረጋውያንን መያዝ የሚችለው ማዕከሉ፤ ከዳያስፖራዎች፣ የግንባታ ተቋራጮች፣ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና ከውስጥ ገቢ በተገኘ ገንዘብ የተገነባ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahuniversity
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሊመረቅ ነው።

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በግንባታና ግብዓት በማሟላት ሒደት ላይ የቆየው ሆስፒታሉ፤ ሰኔ 01/2016 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መሥጠት ይጀምራል፡፡

ተቋሙ "አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል" በሚል ስያሜ እንዲጠራ መወሰኑም ታውቋል፡፡

ሆስፒታሉ 600 የህሙማን አልጋዎች እና የተለያዩ ዘመናዊ የህክምና ግብዓቶች ይኖሩታል የተባለ ሲሆን ከሰባት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የአርባ ምንጭ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
በኢትዮጵያ 61ኛው የስቴም ማዕከል

STEMpower በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ተቋም የመጀመሪያ የሆነውን የስቴም ማዕከል ባሳለፍነው ሳምንት በፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሥራ ማስጀመሩ ይታወቃል።

ማዕከሉ ኤሌክትሮኒክ ላብራቶሪ እንዲሁም 3D ማተሚያ የተገጠመለት ስማርት ኮምፒዩትር ላብ እንዳለው ተገልጿል፡፡

STEMpower በኢትዮጵያ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የስቴም ማዕከላት አሉት፡፡

@tikvahuniversity
የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፎረም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ መካሔድ ጀምሯል፡፡

ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሔደው ፎረሙ፤ በትምህርት ሚኒስቴር እና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የተዘጋጀ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ-ገዝ ለመሆን የሚያከናውኗቸው ተግባራት፣ ልየታ እና ሪፎርም፣ የምርምር ፕሮጀክቶች እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲጂታል ሽግግር ፎረሙ ከሚመክርባቸው ጉዳዮች ይጠቀሳሉ፡፡

@tikvahuniversity
#Update

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ገለፀ።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው "ሰላም ሰፈር" ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ረቡዕ ከጠዋቱ 2:45 አካባቢ እንደሆነ ፖሊስ አመልክቷል።

"በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት፣ ተጠርጣሪው ሟችን ጀርባዋ ላይ በጩቤ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል" ሲል ፖሊስ ገልጿል። የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጭ እንደሆነም ተግልጿል፡፡

ተጠርጣሪው የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልሆነና ከአዲስ አበባ ዱከም ከተማ አቋርጦ ወደ አሶሳ ከተማ ለሥራ ጉዳይ በመምጣት የወንጀል ድርጊቱን እንደፈፀመ ፖሊስ ገልጿል።

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች "ድርጊቱ የተፈጸመው በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ነው" በሚል የተሰራጨው እና ከብሔር ጋር የተያያዘ ግድያ ለማስመሰል የሚደረገው ሙከራ ፍጹም ከእውነት የራቀ እና ሁለቱም የአንድ ብሔር ተወላጅ እንዲሁም በጓደኝነት አብረው የነበሩ መሆኑን የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል IELTS የፈተና ማዕከል የIELTS ፈተና ግንቦት 17/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል።

የብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገፅ ላይ በመግባት ኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations

ለፈተናው ዝግጅት የሚያስፈልግዎትን ስልጠና እና ምክር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
#MoE

የዩኒቨርሲቲዎችን አፈጻጸም ለመለካት የሚረዱ ቁልፍ የውጤት መለኪያ አመላካቾች (KPIs) መዘጋጀታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከተሰጣቸው ተልዕኮና ቁልፍ የለውጥ አጀንዳዎች አንፃር በውጤት እየተለኩ የሚሔዱበት የአሰራር ስርዓት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ እንደሚዘረጋ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ ገልፀዋል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ሥራ ፈጣሪ እና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ የሰው ኃይል ማፍራት እንዲችሉ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ተልኳቸውን በሚገባ እንዲወጡ ቁልፍ የለውጥ አጀንዳዎች ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎች እድገት እና ውጤት ለመለካት የሚረዱ ቁልፍ የውጤት መለኪያ አመላካች መስፈርቶች መዘጋጀታቸውን አቶ ኮራ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ባለው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፎረም ላይ አንስተዋል።

በተዘጋጁት ቁልፍ የውጤት መለኪያ አመላካች መስፈርቶች (KPIs) ላይ ውይይት በማድረግ ከስምምነት ከተደረሰ በኋላ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ፕሬዝዳንቶቹ ውል እንሚገቡ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያልጀመራችሁ የክረምት ተማሪዎች፣ ትምህርታችሁን መቀጠል እንድትችሉ ምዝገባ አድርጉ ተብሏል፡፡

በዚህም እስከ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ለመመዝገብ፦ http://196.190.28.50/StudentRegistration.aspx

ኦንከላይን ምዝገባ ያላከናወነ #የክረምት ተማሪ በጀት የማይያዝለት በመሆኑ #የማይስተናገድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታችሁን የቀጠላችሁ የክረምት ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪው አይመለከታችሁም ተብሏል፡፡

(ለበለጠ መረጃ ከላይ የተያያዘውን የዩኒቨርሲቲውን የጥሪ መልክት ይመልከቱ፡፡)

@tikvahuniversity
#MoH

በተለያዩ የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ግንቦት 15 እና 16/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

በኮምፒውተር የሚሰጠው ፈተና ፕሮግራም እንደሚከተለው ይሆናል፡-

➧ Pharmacy, Public Health, Midwifery, Medical Laboratory
👉 ግንቦት 15/2016 ዓ.ም
➧ Nursing, Medicine, Dental Medicine, Pediatric Nursing, Psychiatric Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Medical Radiology Technology, Anesthesia and Environmental Health
👉 ግንቦት 16/2016 ዓ.ም

ተመዛኞች ግንቦት 14/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ኦረንቴሽን መከታተል፣ የኮምፒውተር ቅድመ-ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራት፣ ወደ ፈተና የሚያስገባውን Username and Password ማወቅ እንዲሁም የመፈተኛ ክፍላችሁን መለየት ይኖርባችኋል ተብሏል።

በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ)፣ የፈተና መስሪያ ግብዓቶች (እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ) እና ስትመዘገቡ ሲስተሙ የሰጣችሁን ስሊፕ ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

የመፈተኛ ጣቢያ ኦንላይን በመረጣችሁት መሰረት ስም ዝርዝራችሁን ተከታዩን ሊንክ በመጫን መመልከት ይኖርባችኃል 👇
https://drive.google.com/drive/folders/1e329fbEYG-P2vT0WJ1uSlw1tVlgtEFg4?usp=sharing)

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁ. 0118275936 እንዲሁም moh.gov.et ላይ EHPLE የሚለው ውስጥ በመግባት ማግኘት ይቻላል፡፡

@tikvahuniversity
በራያ አካባቢ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 850 የሚሆኑ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እንዲያጠናቅቁና ማጠናከሪያ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡

ከራያ አካባቢዎች የተውጣጡት ተማሪዎች ከሐሙስ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መግባት መጀመራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ሰምቷል።

በራያ አካባቢዎች ትምህርት ከተቋረጠ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነ በአማራ ክልል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት ዘንድሮ ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚቀመጡ የአካባቢዎቹ ተማሪዎች “ከዚህ በኋላ ለፈተናው ተዘጋጅቶ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ ላይ እንዳልሆኑ” ከንቲባው ጠቅሰዋል።

ተመሳሳይ ሀሳብ የሚያነሱት የሰሜን ወሎ ዞን የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰጠ ታደሰ፤ “ከዚያው አካባቢ ሆነው የማጠናከሪያ ትምህርትም የቀራቸውን [የትምህርት] ይዘቶች መሸፈን ስለማይቻል ወደዚህ ቀረብ ብለው ይሸፍኑ የማጠናከሪያ ትምህርት ይሰጣቸው የሚለውን አላማ ያደረገ ነው” ሲሉ ተማሪዎቹ ወደ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ በሚኖራቸው ቆይታ በዩኒቨርሲቲው መምህራን የማካካሻ ትምህርት እንደሚያገኙ ተገልጿል። ተማሪዎቹ ነገ በዩኒቨርሲቲው ገለጻ ተደርጎላቸው፣ ሰኞ ዕለት ትምህርት ይጀምራሉ ተብሏል።

ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ሲቆዩ ለሚያገኙት የምግብ አቅርቦት ከአምስት እስከ ስድስት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን የምግብ ወጪያቸው በማን እንደሚሸፈን እስካሁን ድረስ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። #ቢቢሲአማርኛ

@tikvahuniversity
2024/09/29 21:24:11
Back to Top
HTML Embed Code: