Telegram Web Link
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የአክሰስ ሚኒ-ስኮላርሺፕ ፕሮግራም ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተማሪዎቹ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እና በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ላለፉት ሁለት ዓመታት የተሰጠውን ትምህርት ተከታትለው አጠናቀዋል።

50 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠናቸውን አጠናቀው ሰርተፊኬት እነደተበረከተላቸው ተገልጿል።

@tikvahuniveristy
#TVTI

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የስቴም ስልጠና ማዕከል አስመርቋል።

STEMpower በኢትዮጵያ 61ኛ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ የስልጠና ማዕከሉን በፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ውስጥ አስመርቋል።

STEMpower በኢትዮጵያ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ማዕከላት ያሉት ሲሆን፤ በቴክኒክና ሙያ ተቋም የመጀመሪያ የሆነውን ማዕከል ሥራ ማስጀመሩ ተገልጿል።

ድርጅቱ በኢንስቲትዩቱ ውስጥ ባስመረቀው ማዕከል እስከ ሁለት ዓመት ስልጠናዎችን እየሰጠ አንዳንድ ወጪዎችንም ድጋፍ እያደረገ የሚቆይ መሆኑ ተጠቁሟል።

@tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ይፋ አድርጓል።

በንቅናቄው ተፈታኝ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መርሐግብር በትምህርት ቤቶች ይሰጣል።

በማጠናከሪያ ትምህርቱ የተማሪዎችን የመማር ብቃትና የሥነ-ልቦና ዝግጅት ለማሳደግ እንደሚሠራ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል።

ይህን ሥራ አንዳንድ ክልሎች ቀደም ብለው መጀመራቸው የሚያበረታታ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል።

ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የተቋማት ባለሙያዎች፣ ወዘተ በማሳተፉ እንዲሠሩ ጥሪ አድርገዋል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
23 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በዩናይትድ ስቴትስ እየተካሔደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የሮቦፌስት ውድድር ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡ አብርሆት ቤተ-መፃሕፍት ከአቦጊዳ የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ማዕከል ጋር በመተባበር እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ በውድድሩ እየተሳተፉ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ ሚችጋን ላውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ በሚገኘው ውድድር 23 ታዳጊዎች ኢትዮጵያን ወክለው…
በዩናይትድ ስቴትስ በተካሔደ ዓለም አቀፍ የሮቦፌስት ውድድር ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያውያን የሮቦቲክስ ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሆነዋል።

በውድድሩ 23 ታዳጊ ኢትዮጵያውያን በተለያዮ ዘርፎች የተሳተፉ ሲሆን ከ10 ዓመት በታች በሮቦፓሬድ ምድብ የተወዳደረው ታዳጊ ማሸነፉ ተሠምቷል።

ሌላኛው ታዳጊ ተወዳዳሪ ከ 14-16 ዓመት ምድብ ተሳትፎ ስፔሻል አዋርድ ሽልማትን ማግኘት ችሏል።

በየውድድሩ ከ 1-3 ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

@tikvahuniversity
"የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል" የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውናል፡፡

የሪሚዲያል ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ብቻ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል፡፡

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ማጣራት የሪሚዲያል ፈተና ከሰኔ 1-7/2016 ዓ.ም ወይም ከሰኔ 8-14/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ዘንድሮ ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ትምህርታቸውን ከታህሳስ ወር ጀምሮ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም፡፡ ተማሪዎቹ ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተዘዋውረው የሚማሩበት ዕድል እንዲሁም አማራጭ የፈተና ጊዜ የሚዘጋጅላቸው ስለመሆኑ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የተባለ ነገር የለም፡፡

@tikvahuniversity
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ እና የሥራ አውደ-ርዕይ ተከፍቷል።

አውደ ርዕዩ ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተለያዩ መምህራን እና ተማሪዎች የተሠሩ የምርምር ውጤቶች ይቀርባሉ ተብሏል።

አውደ ርዕዩ ተመራቂዎችን ወደፊት ከሚቀጥሯቸው ተቋማት ጋር የሚያገናኝ መድረክ እንደሚሆንም ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ አምስት ዓመታት ተግባራዊ በሚያደርገው ስትራቴጂክ ዕቅድ ለምርምርና ቴክኖሎጂ ልማት ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን የተቋሙ ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት አምስት ዓመታት በጤና መረጃ ስርዓት ላይ ባከናወናቸው ሥራዎች የጤና ሚኒስቴር የላቀ አፈጻጸም ተሸላሚ ሆኗል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ ሞዴል ከሆኑት ሰባት ወረዳዎች በሁለቱ ማለትም በሸበዲኖ እና በሳንኩራ ወረዳዎች በሠራው ሥራና ባከናወናቸው ምርምሮች ሽልማቱ ተበርክቶለታል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ 9ኛ ብሔራዊ የምርምር ጉባኤውን ግንቦት 14 እና 15/2016 ዓ.ም ያካሒዳል፡፡

ጉባኤው "የፐብሊክ ሴክተር ሽግግር እና ልማት" በሚል ጭብጥ ላይ ይመክራል፡፡

@tikvahuniversity
"በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2017 በጀት ዓመት አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም።" - መንግሥት

ይህ የተገለፀው የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የስምንት የምርምር እና የ14 የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድን በገንዘብ ሚኒስቴር በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በተቋማቱ በሚቀጥለው ዓመት ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ ጠቅሰዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የበጀት ዕቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሠረት አስተካክለው በጥቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡

@tikvahuniversity
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ Social and Behavior Change (SBC) ትምህርት በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ደረጃ መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው የፕሮግራሙን ማስጀመሪያ መርሐግብር አከናውኗል፡፡ በፕሮግራሙ ስርዓተ ትምህርት ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡

ፕሮግራሙ ተማሪዎች የማኅበራዊ እና ባህሪ ለውጥ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ ለመተግበር የሚያስችላቸውን ዕውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡

ፕሮግራሙ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና በዓለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ትብበር የተጀመረ ሲሆን የ SBC የልህቀት ማዕከል በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መቋቋሙም ታውቋል፡፡

@tikvahuniversity
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አመራረጥ አዲስ መመሪያ በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሃብት ብክነት እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደገለፁት፤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በመላክ ዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉባቸውን ችግሮች መጠናቱን ገልፀዋል፡፡

"ዩኒቨርሲቲዎች የብዙ ደሃ ሕዝብ ሃብት የሚፈስባቸው ቦታዎች ናቸው" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ስለዚህ ተቋማቱ በሙስናና ብልሹ አሰራር የተጨመላለቀ አስተዳደር ሊኖራቸው አይገባም ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በዋናነት የተማረ የሰው ኃይል ከማምረት ይልቅ፣ ህንጻ ማምረት ላይ የተሰማሩ ተቋማት እንደነበሩ ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ "ዩኒቨርሲቲዎች የሚታለቡ የጥገት ላሞች ናቸው" የሚለው የአንዳንድ ግለሰቦች አባባል አሁን ላይ አይሠራም ብለዋል፡፡

ሦስት ጊዜ መጥፎ የኦዲት ግኝት ያለበት ዩኒቨርሲቲን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የሚያዝ የገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ ኃላፊዎቹም በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩንም አክለዋል፡፡ ይህንን አሰራር በመከተል "ሦስት ጊዜ መጥፎ የኦዲት ግኝት ያለበት ዩኒቨርሲቲን የሚመሩ አመራሮችን በሙሉ እንቀይራለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፎረም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ይካሔዳል፡፡

ፎረሙ በትምህርት ሚኒስቴር እና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን ለሁለት ቀናት ግንቦት 8 እና 9/ 2016 ዓ.ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ይከናወናል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
ትምህርት ሚኒስቴር ለስድስት ተጨማሪ የምርምር ጆርናሎች ዕውቅና ሰጥቷል። ሚኒስቴሩ በ2012 ዓ.ም ለሦስት ዓመት የሚቆይ ዕውቅና የተሰጣቸው ጆርናሎችን እንዲሁም ሌሎች ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና ለማግኘት ያመለከቱ በድምሩ 35 የአገር ውስጥ ጆርናሎች ላይ ፍተሻ ሲያካሒድ መቆየቱን አስታውሷል። በዚህም በ2012 ዓ.ም ዕውቅና አግኝተው ከነበሩ ጆርናሎች መካከል አስራ አንድ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በ2015…
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚያሳትመው አራተኛ የምርምር ጆርናሉ በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና አግኝቷል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የሚታተመው Ethiopian Journal of Business Management and Economics (EJBME) የምርምር ጆርናል በ2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና ከተሰጣቸው 17 የምርምር ጆርናሎች መካከል ይገኝበታል።

ከዚህ ቀደም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሚያሳትማቸው የምርምር ጆርናሎች ውስጥ ሦስቱ ማለትም Ethiopian Renaissance Journal of Social Science and Humanities (ERJSSH), International Journal of Ethiopian Legal Studies (IJELS) እና Ethiopian Journal of Health and Biomedical Sciences (EJHBS) በትምህርት ሚኒስቴር ለሦስት ዓመት የሚቆይ ዕውቅና ያገኙ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም በቅርቡ ዕውቅና የተሰጠውን ጨምሮ በትምህርት ሚኒስቴር ዕውቅና ያገኙ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጆርናሎች አራት ደርሰዋል።

@tikvahuniversity
የከፍተኛ ትምህርት፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪዎች ብሔራዊ የትስስር ም/ቤት ተመሰረተ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የትስስር ም/ቤቱ ሰብሳቢ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

ም/ቤቱ ከተለያዩ ማኅበራት፣ የልማት ድርጅቶችና ሌሎች የመንግሥት ተቋማት የተውጣጡ 22 አባላት እንዲኖሩት ተወስኗል።

(የም/ቤቱ ምስረታን በማስመልከት በትምህርት ሚኒስቴር የወጣ መግለጫ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
2024/09/29 23:22:37
Back to Top
HTML Embed Code: