Telegram Web Link
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሐግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል።

እነማን ይመዘገባሉ?
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች

ምዝገባ የሚያበቃው፦
ግንቦት 7/2016 ዓ.ም


ስልጠናው መቼ ይጀምራል?
ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም
(ለሁለት ወራት) (በሳምንት ለአራት ቀናት)

ስልጠናው ትኩረት የሚያደርግባቸው፦

➭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣
➭ ሮቦቲክስ፣
➭ ፕሮግራሚንግ፣
➭ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም።

ምዝገባ የማድረጊያ አማራጮች፦

👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/

@tikvahuniversity
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ተሹሞለታል።

ኤርሚያስ ሞሊቶ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸው በዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ብርሃኑ መገርሳ (ዶ/ር) ተፈርሞ የወጣ የሹመት ደብዳቤ ያሳያል።

@tikvahuniversity
ትምህርት ሚኒስቴር ለስድስት ተጨማሪ የምርምር ጆርናሎች ዕውቅና ሰጥቷል።

ሚኒስቴሩ በ2012 ዓ.ም ለሦስት ዓመት የሚቆይ ዕውቅና የተሰጣቸው ጆርናሎችን እንዲሁም ሌሎች ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና ለማግኘት ያመለከቱ በድምሩ 35 የአገር ውስጥ ጆርናሎች ላይ ፍተሻ ሲያካሒድ መቆየቱን አስታውሷል።

በዚህም በ2012 ዓ.ም ዕውቅና አግኝተው ከነበሩ ጆርናሎች መካከል አስራ አንድ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በ2015 ዓ.ም ካመለከቱ ጆርናሎች መካከል ስድስት (ከታች ከቁጥር 12-17 የተገለፁት) በድምሩ አስራ ሰባት የምርምር ጆርናሎች መስፈርት ማሟላታቸው ተገልጿል።

ለጆርናሎቹ የተሰጠው ዕውቅና ከሚያዝያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ዓመት የሚቆይ ነው ተብሏል።

1. Bahir Dar Joumal of Education
2. East African Journal of Sciences
3. East African Journal of Social Sciences and Humanities
4. Ethiopian Journal of Agriculture Sciences
5. Ethiopian Journal of Education
6. Ethiopian Journal of Social Sciences and Language Studies
7. Ethiopian Journal of the Social Sciences and Humanities
8. Haramaya Law Review
9. Jimma University Law Journal
10. Journal of Ethiopian Studies
11. Oromia Law Journal
12. Ethiopian Association of Civil Engineers Journal
13. Ethiopian Journal of Business and Economics
14. Ethiopian Journal of Business Management and Economics
15. Ethiopian Journal of Development Research
16. Ethiopian Journal of Higher Education
17. Journal of Indigenous Knowledge and Development Studies

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ነገ ግንቦት 1/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

የሙያ ብቃት ምዘና ፈተናውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ እንደሚሰጡት ተገልጿል።

ምዘናው በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18,591 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ነገ ሐሙስ ግንቦት 1/2016 ዓ.ም በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች ይሰጣል።

ተመዛኞች ስልክና የትኛውም አይነት የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ይዘው ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት አይችሉም።

ተመዛኞች የታደሠ መታወቂያ በመያዝ ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት (2:30) አንድ ሰዓት ቀደም ብለው በምዘና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት ይኖርባቸዋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስጠት ሊጀምር ነው።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃ እና በድኅረ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም ለሚገቡ ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት መዘጋጀቱን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ጀሉ ዑመር (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው ከመጪው መስከረም ጀምሮ መሰጠት የሚጀመር ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚከናወን ም/ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው በሁሉም ዘርፎች ይሰጣል የተባለ ሲሆን ፕሮግራሙ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል፡፡

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ በሥራ ገበያ ያሉ ሰራተኞች እና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም ፕሮፌሽናል ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል። #ENA

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "የኢትዮጵያ አብዮት ከ50 ዓመት በኋላ፡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ትሩፋቶችና የተሸጋገሩ ዕዳዎች" በሚል ጭብጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ልዩ ሴሚናር አዘጋጅቷል።

አንጋፋዎቹ ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ፣ አምባሳደር ታደለች ኃይለሚካኤል፣ አቶ ዘገዬ አስፋው፣ ዲማ ነገዎ (ዶ/ር)፣ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) በመድረኩ ተወያዮች መሆናቸው ተገልጿል።

ሴሚናሩ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ራስ መኮንን አዳራሽ ነገ ግንቦት 1/2016 ዓ.ም ጠዋት 2:00 መካሔድ ይጀምራል።

@tikvahuniversity
ነጻ የትምህርት ዕድል!

የደቡባዊ ትብብር ድርጅት (OSC) የድህረ ምረቃ ነጻ የትምህርት ዕድሎች ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ!

ድርጅቱ 400 የድህረ ምረቃ ነጻ የትምህርት ዕድሎች ለአባል አገራት ተማሪዎች ያመቻቸ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ድርጅቱ የስኮላርሺፕ ዕድሎቹን ከብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍ ትብብር ቡድን ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

መቀመጫውን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ያደረገው የደቡባዊ ትብብር ድርጅት (OSC), ከአራት ዓመታት በፊት የተመሰረተና አባል አገራትን ከአፍሪካ፣ ኤስያ ፓስፊክ፣ ላቲን አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የያዘ ድርጅት ነው፡፡

ተጨማሪ ለማንበብና ለማመልከት 👇
https://osc.int/scholarships/

የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው 👇
ሰኔ 10/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት የጽሁፍ ምዘና ተሰጠ፡፡

የሙያ ብቃት የጽሁፍ ምዘናው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 18,591 መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በ15 የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

ምዘናው በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች በ36 የትምህርት አይነቶች የተሰጠ ሲሆን፤ በምዘና ሒደቱ ከአንድ ሺህ በላይ ፈታኞች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና አስተባባሪዎች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

የመምህራኑን ፍቃደኝነት መሰረት በማድረግ የተሰጠው የጽሁፍ ምዘናው፤ የመምህራንን የሙያ ብቃት በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የጽሁፍ ምዘናው ከ80 በመቶ የሚያዝና ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ የማህደረ ተግባር ምዘናን መሰረት እንደሚያደርግ ምዘናውን በጋራ የሰጡት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
23 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በዩናይትድ ስቴትስ እየተካሔደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የሮቦፌስት ውድድር ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

አብርሆት ቤተ-መፃሕፍት ከአቦጊዳ የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ማዕከል ጋር በመተባበር እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ በውድድሩ እየተሳተፉ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ሚችጋን ላውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ በሚገኘው ውድድር 23 ታዳጊዎች ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ ዘርፎች እየተሳተፉ እንደሆነ ታውቋል።

ግንቦት 5/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ በሚጠበቀው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር፤ ኢትዮጵያውያኑ ታዳጊዎቹ የሚያሸንፉ ከሆነ በሚችጋን ላውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ለመቀጠል የሚያስችላቸውን ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚያገኙ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በአምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ ተከናውኗል፡፡

መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ

ስቱዲዮቹ በትምህርት ሚኒስቴር፣ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ አሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ሻያሾኔ ኩባንያ ትብብር በተተገበረ e-SHE የተባለ ፕሮግራም አማካኝነት የተገነቡ ናቸው።

ስቱዲዮቹ በ'ሪሶርስ ማዕከልነት' የሚያገለግሉ ሲሆን የዲጂታል ትምህርትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል።

ስቱዲዮቹ በየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኛሉ?

ስቱዲዮቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መቋቋማቸው ተገልጿል።

እነዚህ ስቱዲዮች የከፍተኛ ትምህርት ሽግግርን በአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በቅርብ ርቀት በሚገኙ አስር ክላስተር ዩኒቨርሲቲዎች ለማምጣት እንደሚያስችሉ ይጠበቃል።

የስቱዲዮቹ ሌሎች ጠቀሜታዎች

መምህራን ስቱዲዮቹን በመጠቀም ለe-learning የሚጠቀሟቸውን ኮርሶች ማዘጋጀት ይችላሉ። እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የተዘጋጁትን ኮርሶች ለመደበኛ እና የርቀት ትምህርት ፕሮግራሞች መጠቀም ይችላሉ።

ስለ e-SHE ፕሮግራም

e-SHE 'ኢ-ለርኒግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት' የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት ግብ ያደረገ ነው።

በፕሮጀክቱ የአምስት ዓመት ቆይታ 35 ሺህ መምህራን እና 800 ሺህ ተማሪዎች የዲጂታል ትምህርት አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
#Update

2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡

መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች፤ ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

(መርሐግብሩ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
2024/09/30 17:20:11
Back to Top
HTML Embed Code: