Telegram Web Link
#ጥቆማ

ለ Fulbright African Research Scholars Program (FARSP) ያመልክቱ!

የዩኒቨርሲቲ መምህር ነዎት? ምርምርዎትን በዩናይትድ ስቴትስ ማከናወን ይሻሉ?

ዓመታዊው የፉልብራይት አፍሪካ የምርምር ምሁራን ፕሮግራም (FARSP) 2025/26 ለአመልካቾች ክፍት ሆኗል፡፡

የማመልከቻ ጊዜው እስከ ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

ለማመልከት 👇
https://apply.iie.org/fvsp2025

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ተከታዩ አድራሻ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲን ያናግሩ፦ [email protected]

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አርጀንቲናውያን መንግሥት ለሕዝብ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው ድጎማ ላይ ጭማሪ እንዲያደርግ ለመጠየቅ በሀገሪቱ መዲና ቦነስ አይረስ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ወደ ስልጣን የመጡት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሐብየር ሚሌይ የመንግሥትን ወጪ መቀነስ ላይ ትኩረት በማድረግ ይታወቃሉ፡፡

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሶሻሊስት ርዕዩተ ዓለም አስተሳሰብ መጠመቂያ ማዕከላት በመሆናቸው የበጀት ቅነሳ እንደተደረገባቸው ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በሀገሪቱ ምርጥ የሚባሉ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የበጀት እጥረት ፈተና እንደሆነባቸው ይገልጻሉ፡፡ ምርጥ ከሚባሉ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የሆነው ቦነስ አይረስ ዩኒቨርሲቲ፤ የበጀት ድጎማ ጭማሪ ካልተደረገለት በበጀት እጥረት ምክንያት በሦስት ወራት ውስጥ ሊዘጋ እንደሚችል ይፋ አድርጓል፡፡

ዛሬ በሀገሪቱ መዲና ቦነስ አይረስ የተደረጉ ሰልፎች ለዩኒቨርሲቲዎቹ የሚደረግ የበጀት ድጎማ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ #BBC

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
#የፈተና_ጥሪ

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እና በቴክኒካል አሲስታንት የሥራ መደቦች ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር በቅርቡ ላወጣው ማስታወቂያ ላመለከቱ የፈተና ጥሪ አድርጓል።

ለፈተና የተመረጡ ባለሙያዎች በተቋሙ የቴሌግራም ገፅ በመግባት መመረጣቸውን ይመልከቱ 👇
https://www.tg-me.com/dkulatestnews/74

ለፈተና የተመረጣችሁ ሚያዝያ 21/2016 ዓ.ም የተጠየቀውን መስፈርት አሟልታችሁ በዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ እንድትቀርቡ ተብሏል።

@tikvahuniversity
#YHMC

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲግሪ መርሐግብር ማስተማር ጀመረ።

ኮሌጁ በዛሬው ዕለት 79 ተማሪዎችን በመቀበል በዲግሪ መርሐግብር ትምህርት መስጠት መጀመሩ ተሰምቷል።

ኮሌጁ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ማስተማር የጀመረባቸው መስኮች፦

➤ በድንገተኛ ሕክምና ነርስነት (Emergency and Critical Nursing)

➤ በጨቅላ ሕጻናት ነርስነት (Neonatal Nursing)

➤ በአጠቃላይ ነርስነት (Comprehensive Nursing)

➤ በላቦራቶሪ ባለሙያ (Medical Lab)

@tikvahuniversity
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተመድበውለታል፡፡

ካሳሁን አህመድ (ዶ/ር) የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፣ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመድበዋል፡፡

ማርየ በለጠ (ዶ/ር) የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው በትምህርት ሚኒስቴር እና በቦርድ አፅዳቂነት ተመድበዋል፡፡

አዲስ የተሾሙት አመራሮች ከተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሥራ መደቦች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 19
➤ የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ እና 2ኛ ዲግሪ
➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመትና ከዚያ በላይ
➤ የሥራ ቦታ፦ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት
➤ የምዝገባ ቦታ፦ አዲስ አበባ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ቢሮ ወይም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. B-4

ለተጨማሪ መረጃ፦ አ.አ. 0111-26-01-24 ፖ.ሳ.ቁ. 1362

@tikvahuniversity
#ይጠንቀቁ

"ሰርተፊኬት የሚያሰጡ ነጻ የኦንላይን ስልጠና " የሚሉ ማስታወቂያዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወሩ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ ማስታወቂያዎቹ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴርን ስም ይጠቅሳሉ፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ማስታወቂያዎች ሐሰተኛ መሆናቸውን ዩኒቨርሲዎቹ አረጋግጠዋል፡፡

"የተቋሜን ስም በመጠቀም የሚፈፀም የማጭበርበር ተግባር ሰለሆነ የሚመለከተው ሁሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስባለው" ብሏል መቐለ ዩኒቨርሲቲ፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ከጥቂት ሳምንታት በፊት አውጥቶ እንደደነበር አይዘነጋም፡፡

"በተለያዩ ድረ-ገጾች እና ማኅበራዊ ሚዲያዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ስም እና አርማ በመጠቀም ከሚተላለፉ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲጠነቀቁ" ብሏል ዩኒቨርሲቲው፡፡

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

#MoE

@tikvahethiopia
#HawassaUniversity👏

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ማዕከል የፊታችን ሰኞ የጨረር ህክምና መስጠት ይጀምራል።

ማዕከሉ ለመጀመሪያ ዙር ፈቃደኛ ሆነው በተገኙ 30 ታካሚዎች ነው የጨረር ህክምና አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው። #ኢፕድ

@tikvahethiopia
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 154 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የሰለጠኑ 110 እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ 44 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል107ቱ በጤና ሳይንስ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በ Ethiopian Capital Market (ካፒታል ገበያ) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ይሳተፉ!

መቼ?
ነገ ሰኞ ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም ጠዋት 2:30

የት?
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ

ስልጠናውን ማን ይሰጠዋል?
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለሙያዎች

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሐግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል።

እነማን ይመዘገባሉ?
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች

የምዝገባ ጊዜ፦
ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም

ስልጠናው መቼ ይጀምራል?
ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም
(ለሁለት ወራት) (በሳምንት ለአራት ቀናት)

ስልጠናው ትኩረት የሚያደርግባቸው፦

➭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣
➭ ሮቦቲክስ፣
➭ ፕሮግራሚንግ፣
➭ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም።

ምዝገባ የማድረጊያ አማራጮች፦

👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/

@tikvahuniversity
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙና ዘንድሮ የመልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በበጎ ፍቃደኛ መምህራን በመታገዝ በተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሐግብር አከናውኗል፡፡

በጉዲኦ ዞን ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አምስት ትምህርት ቤቶች ላለፉት ሦስት ዓመታት አንድም ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ አለማሳለፋቸውን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ተቋም ያደረገው ጥናት ያሳያል፡፡

በመሆኑም የማጠናከሪያ ትምህርቱ በጌዴኦ ዞን የሚታየውን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ማነስን ለማሻሻል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለአንድ ወር ከአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን፤ በተመረጡት ትምህርት ቤቶች አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
"ትምህርት ለትውልድ" በተባለውና የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት መሰብሰቡን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ባለፈው ዓመት መጨረሻ በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አሰተዳደሮች ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መሰብሰቡን በሚኒስቴሩ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል።

በ2016 ዓ.ም ብቻ በትምህርት ለትውልድ መርሐግብር ከ4 ሺህ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ሥራ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 05:28:54
Back to Top
HTML Embed Code: