Telegram Web Link
ከአንድ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ክልል ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ርቀው እንደሚገኙ ተገለፀ።

በትግራይ ክልል ከ1.24 ሚሊዮን በላይ ትምህርት ቤት መግባት የነበረባቸው  ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ሪፖርት ጠቆመ።

የቢሮው ሪፖርት እንደሚያሳየው በተያዘው የትምህርት ዓመት ይመዘገባሉ ተብለው ከተጠበቁ 2.48 ሚሊዮን ተማሪዎች፣ ትምህርት ቤት የሄዱት 48 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የትምህርት ቢሮ ተዘግተው ከቆዩ 2,492 ትምህርት ቤቶች 2,105 ያህል መልሶ መክፈቱንና የተቀሩትን 387 ትምህርት ቤቶች በፀጥታ ችግሮች፣ በትምህርት ግብዓትና በመምህራን እጥረት፣ እንዲሁም ለመልሶ ግንባታ አቅም በመታጣቱ ምክንያት መክፈት እንዳልቻለ ተገልጿል። 

የትግራይ ክልል ከአማራ ክልል ጋር በይገባኛል በሚከራከርባቸው የምዕራብ፣ የደቡብና የምሥራቅ ዞኖች ያለው ተለዋዋጭ የፀጥታ ሁኔታ ተማሪዎች በገቡባቸው ትምህርት ቤቶች የተረጋጋ የትምህርት ሒደት ለማስኬድ ፈታኝ እንዲሆን ማድረጉም ተጠቅሷል።

በተጨማሪም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች በጊዜያዊ ድንኳን መጠለያዎች ውስጥ እየተማሩ መሆናቸውም ተነግሯል።

በክልሉ ያለው ኢኮኖሚያዊ ጫናና ረሃብ ብዙ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ከመላክ ይልቅ፣ ለመኖር የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ጉዳዩችን ማሟላት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እያስገደዳቸው መሆኑን የቢሮው መረጃ ያሳያል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኢዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና መገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 Advanced Graphics + Video Editing + Motion Graphics + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️    0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#InfinixEthiopia

የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት፣ የኢንፊኒክስ ስማርት ቲቪ፣ የኢንፊኒክስ ላፕቶፕ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን የኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች የሆኑትን ሆት 40፣ ኖት 40፣ ዜሮ 40  እና  የኢንፊኒክስ ስማርት TVን ሲገበያዩ ኩፖን በመውሰድ አብርዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር በመረጡት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ በመጠቀም እና ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፍ ማሸነፍ ይችላሉ። ይፍጠኑ የዚህ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም አካል ይሁኑ፡፡

መመሪያ

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገጽ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡
3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ
ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia
ለ Instagram @infinixethiopia
ለ TikTok @Infinixet
ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ከሚተላለፉ ያልተረጋገጡ፣ አሳሳች እና ሐሰተኛ የጤና መረጃዎች ይጠንቀቁ፡፡

ሰሞኑም ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሰዓታት ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ከእውነት የራቀና አሳሳች መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

"የህክምና ሙያ ሳይኖራቸውና ለሚሠጡት አገልግሎት ህጋዊ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው በማኅበራዊ ሚዲያ ማህበረሰቡን የሚጎዱ፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት መበራከታቸውን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡ "ይህ ተግባር ማህበረሰቡን በእጅጉ እየጎዳና ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ከመዳረግ አልፎ ፈውስ ፈላጊ ዜጎቻችን ላይ ከፍተኛና የተወሳሰበ የጤና ችግር እየፈጠረ ይገኛል" ብሏል፡፡

በነዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አካላት ተግባራቸው በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተገንዝበው ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ማኅበረሰቡም ምንጫቸው ካልተረጋገጠ አካላት የሚላኩ መልዕክቶችን እንዲመረምር፣ አገልግሎቶችንም ከመጠቀማቸው በፊት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ አስፋላጊ ሆኖ ሲገኝም በ"[email protected]" ላይ ጥቆማ እንዲሰጡ ሚኒስቴሩ ጠይቋል፡፡

@tikvahuniversity
#MondayMotivation

ወጣቱ የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪ

በፈጠራ ሥራዎቹ 14 የተለያዩ ሽልማቶችን ማግኘት ችሏል፤ የፈጠራ ባለሙያና የድርጅት ባለቤት ወጣት ኢዘዲን ካሚል፡፡

ወጣት ኢዘዲን ካሚል የመጀመሪያውን ሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር ካሸነፈ በኋላ በርካታ ዕድሎች እንዳገኘ ይናገራል፡፡

በ2010 እና 2011 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የሳይንስና ምህንድስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር አሸናፊ እንደነበር የሚገልጸው ወጣት ኢዘዲን፣ የፈጠራ ሥራዎቹ የተሻለ ሀብት፣ የሥራ እድል ለመፍጠርና የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ያስቻለው መሆኑን ይናገራል፡፡

ወጣቱ የፈጠራ ሥራዎቹን ተግባራዊ ወደ ማድረግ መግባቱን በመግለፅ፣ አሁን ላይ የቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ድርጅት ባለቤት ነው። ለ18 ሠራተኞችም የስራ ዕድል ፈጥሯል።

ከ400 በላይ ተቋማት በሱ ድርጅት የበለፀጉ የሶፍትዌር ውጤቶች እየተጠቀሙ እንደሚገኙ የሚገልጸው ወጣቱ፣ በሥራዎቹ 14 ሽልማቶች ማግኘት መቻሉን ያስረዳል፡፡ #ኢፕድ

@tikvahuniversity
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም የተመደቡለትን አዲስ ገቢ እና በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም የተከታተሉ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች ተቋሙ ወደፊት ጥሪ አደርጋለሁ ማለቱ አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሐግብር መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ለህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
ራያ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሐግብር መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ለህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ የ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሐግብር መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ለህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
2024/11/18 15:47:59
Back to Top
HTML Embed Code: