Telegram Web Link
#GondarUniversity

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተመደቡ አዲስ ገቢ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመደበኛ እና በ2016 የትምህት ዘመን አቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ሲከታተሉ ቆይተው የማለፊያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ህዳር 12 እና 13 2017 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ አንደኛ ዓመት እና በ2016 ዓ.ም በመደበኛ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ህዳር 18 እና 19/2017 ዓ.ም መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በቅጣት ምዝገባ፦ ህዳር 20/2017 ዓ.ም

ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፦ ህዳር 20/2017 ዓ.ም

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

@tikvahuniversity
#BuleHoraUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደተቋም የመግቢያ ጊዜ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
- ስምንት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

@tikvahuniversity
🔊 🌟 ገቡ ገቡ ገቡ! የሳፋሪኮም #1ወደፊት የዲጂታል ሙዚቃ ውድድር ምርጥ 10 ኮከቦቻችን ወደ ሙዚቃ ስልጠናው ገብተዋል! በቆይታቸውም የሚኖራቸውን ጊዜ ተከታተሉን!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether
#DigitalMusicChallenge
#DebreTaborUniversity

በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥታችሁ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ምዝገባ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
- ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም እንድትከታተሉ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሌላ ማስታዎቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
2ኛው አገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ፕሮግራም ነገ ህዳር 4/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እና የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ፕሮግራሙን በጋራ አዘጋጅተውታል።

መርሐግብሩ በአገር አቀፍ ደረጃ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ ክህሎታቸውን በማሳደግ ከውጪ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን የሚተኩ፣ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን እንዲፈጥሩ የሚያስችል ነው።

@tikvahuniversity
#AssosaUniversity

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
- የስፖርት ትጥቅ።

@tikvahuniversity
#JinkaUniversity

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፍያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በፍሬሽማን ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 11 እና 12/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#RayaUniversity ራያ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለህዳር 2 እና 3/2017 ዓ.ም አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል። @tikvahuniversity
#RayaUniversity

ለ2017 የትምህርት ዘመን ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
ይሄኔ እኮ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይህን አልሰሙም፤ የሀገር ውስጥ በረራችንን በM-PESA ስናደርግ 5% ተመላሽ አለን። ይህን አጋጣሚማ እፍስ ነው እንጂ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
#ጥቆማ

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች መካከል በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግእዝ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ከሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉና ፍላጎቱ ያላችሁ አመልካቾች ከ8ኛ-12ኛ ክፍል ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ይዛችሁ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በአካል በመቅረብ እስከ ህዳር 7/2017 ዓ.ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ወደ ፍሬሽማን ፕሮግራም ያለፋችሁ ተማሪዎች የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ ተብሏል።

@tikvahuniversity
#MaddaWalabuUniversity

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ እና በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርታችሁን በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማሰረጃ ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ8ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።

የትምህርት ማመልከቻ እና ምዝገባ የሚከናወነው በኦንላይን http://estudent.mwu.edu.et/auth/login ሊንክ በመጠቀም ስለሆነ በተጠቀሱት ቀናት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሮቤ ካምፓስ በአካል በመገኘት በኦንላይን ምዝገባ አድርጉ ተብሏል፡፡

በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ትምህርት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
#InjibaraUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ወደ አንደኛ ዓመት (Freshman Program) መግቢያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2017 ዓ.ም በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (Remedial) አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደፊት የሚገለፅ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ለተመደቡ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ነቀምት ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ አቀባበል ማድረግ ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ህዳር 4 እና 5/2017 ዓ.ም ሪፖርት እንዲያደርጉ የጥሪ ማስታወቂ ማውጣቱ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መስጠት ጀምሯል፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚሰጠው ፈተና፤ ተማሪዎቹ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ጀማሪ መርሐግብር (Freshman) ለመግባት የሚያስችላቸውን ውጤት የሚለይበት ነው፡፡

በማኅበራዊ ሳይንስ (378) እና በተፈጥሮ ሳይንስ (950) በድምሩ 1,328 ተማሪዎች ፈተናውን በዩኒቨርሲቲው ሦስት ግቢዎች ማለትም በፖሊ፣ ፔዳ እና ሰላም ግቢዎች መውሰድ ጀምረዋል።

@tikvahuniversity
2024/11/18 14:40:03
Back to Top
HTML Embed Code: