Telegram Web Link
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ለአስር የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች ዕውቅና ሰጥቷል፡፡

በ2016 ዓ.ም ዕውቅና ለማግኘት ካመለክቱ የአገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች መካከል መስፈርቱን ላሟሉ አስር (10) የምርምር ጆርናሎች ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚቆይ ዕውቅና መስጠቱን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

ዕውቅና የተሰጣቸው ጆርናሎች፦

1. Berhan International Research Journal of Sciences and Humanities
2. Choke Journal of Science and Technology
3. Ethiopian Journal of Applied Sciences and Technology
4. Ethiopian Journal of Biological Sciences
5. Science, Technology and Arts Research Journal
6. Ethiopian Journal of Business and Social Science
7. Ethiopian Journal of Economics
8. Ethiopian Journal of Language, Culture and Communication
9. Ethiopian Journal of Sport Science
10. RADA Multidisciplinary Research

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ኀዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➭ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➭ የስፖርት ትጥቅ

@tikvahuniversity
#RayaUniversity

በ2017 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የማጠናከሪያ ትምህርት (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ህዳር 9/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
2024/11/05 11:40:03
Back to Top
HTML Embed Code: