Telegram Web Link
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለነባር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ባደረገው ጥሪ መሠረት ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ ይገኛል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ Climate Change and Environmental Management የማስተርስ ፕሮግራም ከፍቷል።

የገበያ ተፈላጊነት ባለው የትምህርት ፕሮግራም አመልካቾች እንዲመዘገቡ ጥሪ አድርጓል።

በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፉ ተማሪዎች ማመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 1ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎቹን እየተቀበለ ነው፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከኖርዌዩ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በSocial Anthropology የማስተርስ ፕሮግራም ለአመልካቾች ክፍት አድርጓል።

ለሁለት ዓመታት ለሚቆየው ፕሮግራም፤ በሶሻል አንትሮፖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውና ብቁ አመልካቾች ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።

በፕሮግራሙ የመጀመሪያ ሴሚስተር ኮርሶች ላይ የኖርዌይ ፕሮፌሰሮች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ለፕሮግራሙ በውድድር የሚመረጡ አምስት አመልካቾች ይፈለጋሉ።

አመልካቾች የአንድ ወር የፊልድ ወጪያቸው በፕሮግራሙ ይሸፈናል። አመልካቾች የኑሮ ወጪ እና የትምህርት ወጪ (ለግል አመልካቾች) እንዲሸፍኑ ይጠበቃል።

መስፈርቶች፦

► የመጀመሪያ ዲግሪ በአንትሮፖሎጂ ወይም በሶሻል አንትሮፖሎጂ ያላት/ያለው
► CGPA 3.00 ወይም B ያላት/ያለው
► በሶሻል አንትሮፖሎጂ ረዳት መምህራን ይበረታታሉ

የተመረጡ አመልካቾች ለፅሁፍ እና የቃል ፈተና እንደሚጠሩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የምዝገባ ጊዜ፦
ከመስከረም 20-27/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ለተጨማሪ መረጃ፦
[email protected] / [email protected]

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 3,271 ተማሪዎች ቅዳሜ መስከረም 25/2017 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 11:20:36
Back to Top
HTML Embed Code: