Telegram Web Link
የመውጫ ፈተና ለወደቁ ተማሪዎች ብቻ የሚሆን ቴምፖራሪ እንደሚዘጋጅ ተገለፀ።

የመውጫ ፈተና ወድቀው በድጋሜ መፈተን ለማይፈልጉ ተማሪዎች፣ ትምህርት ሚኒስቴር ዘንድሮው መፍትሔ እንደሚያስቀምጥ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የመውጫ ፈተና ወድቀው በድጋሜ መፈተን ለማይፈልጉ ተማሪዎች የተማሩትን የሚገልፅ ቴምፖራሪ እንደሚዘጋጅ ጠቁመዋል።

የመውጫ ፈተና የወደቀ ተማሪ እንዴት ዓይነት ቴምፖራሪ እንደሚሰጠው እና ሥራ እየሠራ እንደገና መፈተን እንዲችል ሁኔታዎች ይመቻቻል ብለዋል።

@tikvahuniversity
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በቅርቡ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይመደባሉ።
- ትምህርት ሚኒስቴር

በተስተካከለው የ2017 ዓ.ም የትምህርት ካላንደር መሠረት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ እስካሁን አልተደረገም።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ፤ "ከ12ኛ ክፍል ውጤት ጋር የተያያዙ በርካታ ቅሬታዎች ለተቋሙ በመቅረባቸው ምክንያት" ምደባው መዘግየቱን ገልፀዋል።

ቅሬታዎቹን እየተስተናገዱ እንደነበር የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ተማሪዎቹ በቅርቡ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
የድረ-ገፅ እና የሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።  

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የኮምፒውተርና ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ-ገፆችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️    0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለስቴም ሰልጣኞች በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና አጠናቋል።

ብራይተር ጀነሬሽን ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር ቀተሰጠው ስልጠና፤ ከደብረ ታቦር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተውጣጡ 23 ተማሪዎች መሳተፋቸው ተገልጿል።

ሰልጣኞቹ በ Leadership, Communication Skills, Critical Thinking እና Community Development Project ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎችን መውሰዳቸው ተመላክቷል።

@tikvahuniversity
አርሲ የኒቨርሲቲ መደበኛ ነባር ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ነባር ተማሪዎቹ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም ወደተቋሙ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታቸውን በተቋሙ ከተከታተሉ ተማሪዎች 𝟗𝟔.𝟗 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጿል።

1,507 ተማሪዎች የሪሚዲያል ትምህርታቸውን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው 1,461 ተማሪዎች (𝟗𝟔.𝟗 በመቶ) የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል።

@tikvahuniversity
ቦረና ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል እና አዲስ ለሚመደቡ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።

በ2016 ዓ.ም በቦረና ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ቦረና ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 23 እና 24/2017 ዓ.ም ይከናወናል በማለት ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ምዝገባው ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 11:30:57
Back to Top
HTML Embed Code: