Telegram Web Link
#ጥቆማ

አዲስ ቻምበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በካፒታል ማርኬት ላይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

ስልጠናው ከመስከረም 7-9/2017 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
0115500934 / 0911194965 / 0911343078 / 0913553393

የኢ-ሜይል አድራሻዎች፦
[email protected]
[email protected]
[email protected]

(የስልጠናው አላማ፣ የተካተቱ ይዘቶች እና የክፍያ መጠን ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#Update

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ.ም 2ኛ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) እና ለድኅረ ምረቃ ትምህርት የማመልከቻ ጊዜን አራዝሟል፡፡

በዚህም የማመልከቻ ግዜው እስከ መስከረም 8/2017 ዓ.ም መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና እና የመግቢያ ፈተና ያለፉ ለትምህርት የማመልከቻ ግዜ ወደፊት እንደሚገለፅ ተቋሙ አስገንዝቧል፡፡

ለመግቢያ ፈተና ለማመልከት 👇
https://portal.aau.edu.et

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትግርኛ ቋንቋ እና የፍልስፍና ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ መስጠት ሊያቆም ነው።

ዩኒቨርሲቲው ከ18 ዓመት በፊት በተቋሙ ስር የተከፈተውን የትግርኛ ቋንቋ እና ስነ ጹሁፍ ትምህርት ክፍል ሊዘጋ ነው።

በፍልስፍና ትምህርት ክፍል በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጠው ትምህርትም፤ ከዚህ ዓመት ጀምሮ እንዲቋረጥ ዩኒቨርስቲው ውሳኔ አሳልፏል።

ዩኒቨርሲቲው ከእዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው፤ የትምህርት ክፍሎቹ ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት አዲስ ተማሪዎችን ባለመቀበላቸው ነው።

በሐምሌ 2015 ዓ.ም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው ተቋሙ፤ በስሩ ያሉ የትምህርት ክፍሎችን በአዲስ መልክ በማደራጀት ላይ ይገኛል።

መልሶ ማደራጀትን በተመለከት ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው ሰነድ፤ “የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎባቸው የሚቀጥሉ”፣ “የሚጣመሩ”፣ “ተዋህደው አዲስ የትምህርት ክፍል የሚመሰርቱ”፣ “የሚጠናከሩ” እና “የሚቋረጡ” የትምህርት አይነቶችን ይዘረዝራል።

እንዲቋረጡ ውሳኔ ከተላለፈባቸው የትምህርት አይነቶች መካከል የትግርኛ ቋንቋ እና ስነ ጹሁፍ ይገኝበታል። የትምህርት ክፍሉ ባለፉት ዓመታት ባጋጠመው የተማሪዎች እጥረት ምክንያት ከዘንድሮው የትምህርት ዘመን ጀምሮ እንዲዘጋ መወሰኑን የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ሀድጉ ተካ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። 

የትምህርት ክፍሉ እንዲዘጋ መወሰኑን ተከትሎ፤ በስሩ የነበሩት አራት መምህራን ወደ ሌሎች ትምህርት ክፍሎች መዘዋወራቸውን ኃላፊው ገልፀዋል።

ከ2011 ዓ.ም ወዲህ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ያልተቀበለው የፍልስፍና ትምህርት ክፍልም እንዲቋረጥ ተወስኗል። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahuniversity
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ምዝገባ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም በምትማሩበት ኮሌጅ ወይም ኢንስቲትዩት ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመቅረብ ምዝገባችሁን እንድትፈጽሙ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

አዲስ ገቢ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም አመልካቾች ምዝገባ የሚፈጸመው የNGAT ፈተና ውጤት ከተለቀቀ በኋላ በሚወጣ ማስታወቂያ መሠረት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የነበራችሁና ምዝገባ የሚከናወነው በ2017 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲው ከሚመደቡ የፍሬሽማን ፕሮግራም ተማሪዎች ጋር መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የመውሊድ በዓል ይመኛል!

እንኳን አደረሳችሁ!

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

@tikvahuniversity
#MoE_Contractual_Agreement

ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለ2017 ትምህርት ዘመን የአፈጻጸም ውል ስምምነት በመፈራረም ላይ ይገኛል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎችን በመመደብ የሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የ2016 ዓ.ም ቁልፍ ውጤት አመላካቾች (KPIs) አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት ፊርማ (Contractual Agreement) ለ2017 ትምህርት ዘመን እየተዋዋለ መሆኑም ታውቋል።

ውሉ ዩኒቨርሲቲዎቹ የትምህርት ጥራትንና አጠቃላይ አፈፃፀም ለመከታተል የሚያስችል መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በ2017 ዓ.ም ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ የሚያደርጋቸው መሆኑን ገልጸዋል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለስድስት ሳምንታት ሲሰጥ የቆየውን የSTEM ስልጠና አጠናቋል።

ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ትምህርቶች ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3፣ በፓይተን ፕሮግራሚንግ፣ የህጻናት የሳይንስ ሙከራ እና ብሩህ ትውልድ ትምህርታቸውን በክረምት ወቅት ሲከታተሉ መቆየታቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የ2017 ትምህርት ዘመን መደበኛ ትምህርት ነገ ሰኞ መስከረም 6/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀመሯል።

በሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች የ2017 ዓ.ም ትምህርት መጀመሩን የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሯ ገልጿል።

@tikvahuniversity
#BoranaUniversity

ቦረና ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም በቦረና ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ቦረና ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 23 እና 24/2017 ዓ.ም ሲሆን መስከረም 27/2017 ዓ.ም ትምህርት ይጀምራል ተብሏል፡፡

አዲስ የተመደባችሁ (ፍሬሽማን) ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ፡-

➧የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ስምንት (8) 3x4 ፎቶግራፍ፣
➧አንሶላ፣ ብርድልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ተጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በመቐለ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ምዝገባ ያድርጉ።

ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸው የቅድመ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች፦

► Computer Science and Engineering
► Electrical and Electronics Engineering
► Information Technology
► Biological and Chemical Engineering
► Material Science and Engineering
► Electronics and Communications Engineering

የቅበላ መስፈርቶች

► የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያለፉ
► የኢንስቲትዩቱ የመግቢያ ፈተና የሚያልፉ
► የ2ኛ ደረጃ/ፕሪፓራቶሪ ትራንስክሪፕት
► በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥባችሁ፦
- 415 ከ 700 (ለወንድ)
- 400 ከ 700 (ለሴት)
- 355 ከ 600 (ለወንድ)
- 345 ከ 600 (ለሴት)

የማመልከቻ አማራጮች
- በኢሜይል 👉 [email protected]
- በቴሌግራም/በዋትስአፕ 👇 +251-914749182

ሙሉ ስማችሁን፣ የ12ኛ ክፍል ውጤት፣ የ12ኛ ክፍል የፈተና ምዝገባ ቁጥር፣ የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱበት ማዕከል፣ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የግል ስልክ ቁጥር እና ትራንስክሪፕት ማያያዝና መግለፅ እንዳትዘነጉ።

ምዝገባ የሚጠናቀቀው 👇
መስከረም 14/2017 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥባቸው ማዕከላት፦

- አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣ አክሱም
- ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ዓዲግራት
- ራያ ዩኒቨርሲቲ፣ ማይጨው
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ
- መቐለ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ መቐለ

@tikvahuniversity
#KotebeUniversityOfEducation

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ነባር መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች እና የቀን የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የ4ኛ ዓመት መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም የቀን የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የድኀረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት መስከረም 20/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

በ2015 ዓ.ም የገቡ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች እና የቀን የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 21/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

በ 2016 ዓ.ም አንደኛ ዓመት የነበሩ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ለዲፓርትመንት ምርጫ ገለፃ መስከረም 20/2017 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎቹ አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።

የ2017 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ምዝገባ መስከረም 10 እና 11/2017 ዓ.ም ይካሔዳል ብሎ የነበረው ዩኒቨርሲቲው፤ "በተቋሙ ውስጥ ያሉ ሰልጣኞች በተያዘው ጊዜ ባለመውጣታቸው ምክንያት ምዝገባው ወደ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መራዘሙ ተገልጿል።

ትምህርት መስከረም 22/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
2024/11/05 23:09:27
Back to Top
HTML Embed Code: