Telegram Web Link
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ የ8ኛ ክፍል የማለፊያ ዝቅተኛ ነጥብ 50 በመቶ ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኞች 45 በመቶ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህም በክልሉ 110,772 መደበኛ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ 48,728 ወይም 44 በመቶ ተማሪዎች 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች https://ce.ministry.et/ ላይ የአድሚሽን ቁጥራቸውንና ስማቸውን በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahuniversity
“ በነሐሴ ነበር መመረቅ የነበረብን ግን ት/ቤቱ ኮርሶችን አልጨርስም ስላለ ወደ ጥር ወስዶናል ” - ተመራቂ ተማሪዎች

የ2013 ባች "3,000" የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው “አዲስ ህግ በማውጣት” የመመረቂያ ጊዜያቸውን ሊያራዝምባቸው በመሆኑ ቅሬታ እንዳደረባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የተማሪዎቹ አስተባባሪ ምን አሉ ?

“ ነሐሴ ወር ነበር መመረቅ የነበረብን ግን ት/ቤቱ ኮርሶችን አልጨርስም ስላለ ወደ ጥር ወስዶናል፡፡ አሁን ሪሰርች እየራን ያለን ልጆች ነን፡፡

አዲስ ህግ አወጣ ት/ቤቱ፣ ‘ከ C በታች ያላችሁ ተማሪዎች ኮርሱን ድገሙ’ ብሎ፡፡ እኛም ፒቲሽን አሰባስበን ለት/ቤቱ ይህ ነገር ተገቢ እንዳልሆነ፣ ጊዜ እንደሌለን አስረድተን አስገባን፡፡

ከዚያ ‘የእናንተ በልዩ ሁኔታ ይታያል ተረጋጉ፣ ትምህርታችሁን ቀጥሉ’ ብለውን እየቀጠልን በሳምንቱ ደግሞ ሌላ ማስታወቂያ ወጣ፡፡ በ‘Reexam ተፈተኑ፣ በReexam ፋቁት’ የሚል፡፡ ይህንንም ስንሰማ ፒቲሽን አሰባስበን በድጋሚ ት/ቤቱን ጠይቀን ነበር፡፡

16 ኮርሶች ናቸው የምንወስዳቸው፡፡ ከ16 ኮርሶች 5 ከ‘C’ ማይነስ በታች ያለባቸው ተማሪዎች አሉ፡፡ ት/ቤቱ የሚለው ለእያንዳንዱ ትምህርት 100 ጥያቄዎች ይውጡና ተፈትናችሁ ከ50 በላይ አምጡ ነው፡፡

‘Supportive class ነው ይፈጠራል’ ነው እያለ ያለው፤ ግን አይደለም፡፡ ስለ Supportive class በዝርዝር አስረዱን ስንላቸው ሊነግሩን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ግዴታ ውሰዱ ከተባለ ደግሞ 2018 ዓ/ም ነው የምንመረቀው፡፡ ኮርሱን ጠብቀው ወስደው ነው ይፈተኑ እየተባልን ያለነው፡፡

ት/ቤቱ ደግሞ ስንገባ ህግና ደንብ ሰጥቶን ነበር፡፡ ‘ከቱ (ከ2) በታች ውጤት አታምጡ እና ‘F’ በታች መሆን የለበትም፡፡ ‘F’ ካልሆነ ደግሞ ምንም አይነት ኮርስ አትደግሙም’ ብሎን ነበር፡፡

አምና ጠይቀናቸው ነበር ሁሉንም የትምህርት ቤቱን አካል አስቀምጠን ‘C’ ውጤት ለመፋቅ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? ብለን፤ አሳሳቢ ቦታ ላይ ካልገባችሁ መድገም አይጠበቅባችሁም ብለውናል።

ያኔ ጊዜው በነበረን ወቅት ሳያስደግመን አሁን በመጨረሻው ሰዓት ላይ ድገሙ እያለን ነው፡፡ አሁን ደግሞ እንደ ግቢ የመውጫ ፈታና ብሎ አውጥቶ እየተፈተንን ነው፡፡

እንዲህ አይነት አሰራር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም የለም፡፡ የኛም ትምህርት ቤት ዘንድሮ ‘C’ ያመጡ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ ታዲያ ለኛ ሲሆን ነው እንዴ አዲስ ህግ የሚወጣው? ጠይቀናቸው ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡” የሚል ቅሬታ አቅርቧል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለቀረበበት ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ለቀናት ብንጠብቅም፤ ጉዳዩ " የሚመለከታቸው አካላት ስብሰባ ላይ ናቸው" በመባሉ ለጊዜው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡

በተጨማሪ በተማሪዎቹ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ያሏቸው የአካዳሚክ አካልን ያናገርን ሲሆን፣ በኮሚዩኒኬሽን በኩል ምላሽ እንድንጠይቅ፣ እሳቸው የማይመች ቦታ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ወደ ኮሚዩኒኬሽን የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡ ምላሽ ከሰጡ በቀጣይ ሃሳባቸውን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ከ5,500 በላይ ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል። - ኢሰመኮ

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ባሉ ግጭቶችና ሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ከ5,500 በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራቸውን ከማከናወን ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።

በዚህ ምክንያት በአገሪቱ የዜጎች የትምህርት መብት “በእጅጉ እየተጣሰ” ነው ተብሏል።

በስምንት ክልሎች 5,564 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ በመሆናቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው መስተጓጎላቸውን ኮሚሽኑ አመልክቷል።

ትምህርት ቤቶች በተለያዩ አደጋዎች ምክንያት እየተዘጉ ሲሆን፤ በግጭት ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ደግሞ የጦር ካምፕ ሆነው እያገለገሉ እንደሚገኙ የኢሰመኮ የሴቶች፣ የህጻናት፣ የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋሪያ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በአሁኑ ሰዓት ከአራት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ እንደሆኑ ጠቅሷል።

የትጥቅ ግጭት እየተደረገበት ያለው አማራ ክልል በ2016 ዓ.ም. ከ2.6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን ገልጿል።

ኢሰመኮ አሳሳቢ ሆኗል ባለው የትምህርት መብት አደጋ ላይ መውደቅ እና መፍትሔዎቹ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ባለፈው ሐምሌ ወር መምከሩን ገልጿል።

በምክክሩ የሚመለከታቸው አካላት ለችግሩ ፈጣን እና የተቀናጀ የመፍትሔ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል። #ቢቢሲ

@tikvahuniversity
#ይመዝገቡ
#ዛሬ_ይጠናቀቃል

በ2017 የትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ አድርገዋል?

ምዝገባው ዛሬ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ለመመዝገብ 👇
https://NGAT.ethernet.edu.et

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

► የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
► ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 114
► ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
► የሥራ ቦታ፦ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የማመልከቻ ቦታ፦
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሃብት አስተዳደር ወይም በአዲስ አበባ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ወኪል ቢሮ 4 ኪሎ ብርሃንና ሰላም ህንጻ

ለተጨማሪ መረጃ፦
0588270461 / 0913967604

(እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው ሙሉ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#ተጨማሪ ከጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና (Licensure Exam) ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ መድረሳቸውን ተከትሎ ተጨማሪ ማብራሪያ ጤና ሚኒስቴርን ጠይቀናል፡፡ የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና በዚህ ወር በድጋሜ የሚሰጥ ሲሆን፤ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ የምዝገባ ጥሪ ዛሬ ወይም ነገ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ ሀገረ አቀፍ የመውጫ ፈተና #ያለፉ እና ዲግሪ #ያላቸው ሁሉም…
ጥያቄያችን አልተመለሰም ያሉት የፋርማሲ ተማሪዎች ጥያቄያችው ምንድነው ?

ተማሪዎቹ በቅድሚያ ያነሱት የተፈተኑት ፈተና ከብሉፕሪንይ ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ ነው።

የተመዘገበው ውጤትም በዚህ ምክንያት እንደሆነ ጠቁመዋል።

" ፈተናችን እንደገና ይታይ መብታችን ይከበር " ያሉት ተማሪዎቹ " ኮምፒውተር አይሳሳትም አይበሉን የሰራነውን እናውቃለን " ብለዋል።

ሌላው ተማሪዎቹ ያነሱት ጥያቄ የተባው ቃል አልተከበረም የሚል ነው።

" ጥዋት እና ከሰዓት ሁለት ፈተና ነበር መውሰድ የነበረብን ግን አንዱን ፈተና ሌላ ቀን ትፈተናላችሁ ብለውን በዛው ቀርቷል " ያሉት ተማሪዎቹ " ውጤቱ የተገለጸው በጥዋቱ ብቻ ነው " ብለዋል።

" ትምህርት ሚኒስቴር ቃሉን አክብሮ እንደሌሎች ዲፓርትመንት የከሰአቱም ይፈትነንና አማያከዩ ይያዝልን " ሲሉ ጠይቀዋል።

ውጤታችን ባልተስተካከለበት " በምን መስፈርት coc አትወስዱም አሉን ? " ያሉት ተማሪዎቹ " ሌላም ጊዜ እንደተያዘው የመውጫ ፈተናው የከሰዓቱንም ተፈትነን አማካዩ ይይዛልን " ብለዋል።

ተማሪዎቹ በሌሎች ጥዋትም ከሰዓትም ፈተና በወሰዱ የጤና ዲፓርትመንት አማካይ መያዙን ጠቁመው " ስለዚህ የኛንም እንደዛ ይያዙልን " ሲሉ ጥይቀዋል።

በወቅቱ የፋርማሲ ፈተና ወጥቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመሰጣቱ መሰረዙን በኃላም የጥዋቱን ብቻ ተፈትነው ሌላ ጊዜ የከሰዓቱን ትፈተናላችሁ ተብለው መቅረቱን አመልክተዋል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት መማር ለምትፈልጉ የተዘጋጀ መረጃ፦

ኮሌጁ በሦስት ትምህርት ቤቶች ማለትም በሕክምና ትምህርት ቤት፣ በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት እና በነርሲንግ ትምህርት ቤት ስር በሚገኙ በርካታ የትምህርት ክፍሎች አመልካቾችን በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት መርሐግብር ለማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራም ይቀበላል።

አመልካቾች ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ማግኘት ይጠበቅባችኋል። እንዲሁም የፅሑፍ እና የቃል ፈተና በምታመለክቱበት የትምህርት ክፍል ይሰጣል።

የመመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም

ለማመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ፦
https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement

ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ፣ የሚፈልጉትን የትምህርት ፕሮግራም በመምረጥ Apply የሚለውን በመጫን አስፈላጊ መረጃ በማስገባት ያመልክቱ። የማመልከቻ 400 ብር በCBE በመክፈል ደረሰኙን ያያይዙ። ከዛም የትምህርት ማስረጃዎችን ያያይዙ።

@tikvahuniversity
#ተራዝሟል

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 የትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም መራዘሙን አሳውቋል።

በተራዘመው ጊዜ https://NGAT.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ይመዝገቡ።

@tikvahuniversity
ጤና ሚኒስቴር በዚህ ወር ለሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና ምዝገባ ተጀምሯል፡፡

በተለያዩ የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ ቴምፓራሪ ዲግሪ የተሰጣችሁና የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የጤና ባለሙያዎች የምዘና ፈተናውን መውሰድ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

የብቃት ምዘና ፈተናውን የሚወስዱ አመልካቾች ምዝገባ ከነሐሴ 06-15/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

የመንግሥት እንዲሁም የግል ተቋማት ተመዛኞች http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ብቻ ምዝገባ እንድታደርጉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ምዝገባ ስታደርጉ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ ተብሏል፡፡

ማሳሰቢያ፦

በሰኔ 2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተሰጠውን የፋርማሲ ሙያ የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፋችሁ ተመዛኞች፣ በጤና ሚኒስቴር በኩል የሚሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና መውሰድ የሚጠበቅባችሁ በመሆኑ ከላይ በተጠቀሰው ዌብሳይት ላይ በመግባት ምዝገባ አድርጉ፡፡

ሰኔ 19/2016 ዓ.ም በተሰጠው የመውጫ ፈተና አልፋችሁ ዲግሪ የያዛችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች፣ ይህ የምዝገባ ጊዜ እንደተጠናቀቀ የተግባር ምዘና (OSCE) ምዝገባ የሚጀመር በመሆኑ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
#ተጨማሪ

ጤና ሚኒስቴር በዚህ ወር የብቃት ምዘና ፈተና የሚሰጥባቸው 16 ሙያዎች፦

- Medicine
- Nursing
- Public Health
- Anesthesia
- Pharmacy
- Midwifery
- Dental Medicine
- Medical Laboratory Science
- Medical Radiology Technology
- Environmental Health
- Psychiatric Nursing
- Pediatric & Child Health Nursing
- Emergency & Critical Care Nursing
- Surgical Nursing
- Physiotherapy
- Human Nutrition

Note:

እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/04 05:32:36
Back to Top
HTML Embed Code: