Telegram Web Link
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ትምህርት የመግቢያ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች ለዝግጅት የሚረዳ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ሦስቱም ካምፓሶች የመግቢያ ፈተናውን ለመውሰድ በኦንላይን የተመዘገባችሁ አመልካቾች እስከ ነሐሴ 7/2016 ዓ.ም በአካል ወይም በስልክ ቁ. 0921194016 በመመዝገብ ስልጠናውን በሚቀርባችው ካምፓስ ተገኝታችሁ አንድትወስዱ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የሦስቱ ካምፓሶች የስልጠና ፕሮግራም፦

ሻምቡ ካምፓስ ► ከነሐሴ 8-10/2016 ዓ.ም
ነቀምቴ ካምፓስ ► ከነሐሴ 13-15/2016 ዓ.ም
ግምቢ ካምፓስ ► ከነሐሴ 16-18/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ Social Work የፒ.ኤች.ዲ. ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ Social Work ትምህርት ክፍል በመስኩ ሙያቸውን ለማጎልበት ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የፒ.ኤች.ዲ. ትምህርት ፕሮግራም ከፍቷል፡፡

የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሙ በ Social Work ምርምር፣ አመራር እና ፖሊሲ ልማት የላቀ ስልጠና ለሰልጣኞች ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ትምህርት ክፍሉ አመልካቾችን መቀበል የጀመረ ሲሆን ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ 👉 [email protected] ኢሜይል አድራሻን ይጠቀሙ፡፡

@tikvahuniversity
#Update

"ለፋርማሲ ተማሪዎች እንዲሁም የብቃት ምዘና ፈተና በድጋሜ ለሚፈተኑ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው በቅርቡ ይሰጣል፡፡" - ጤና ሚኒስቴር

የፋርማሲ ተማሪዎች ባለፈው ሰኔ ከተሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና (Licensure Exam) ጋር የተያያዙ በርካታ ቅሬታዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና-ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል በጉዳዩ ዙሪያ ተከታዩን መረጃ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰጥተዋል፡፡

ባለፈው ሰኔ የተሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና በተመለከተ ጤና ሚኒስቴር ከፋርማሲ ተማሪዎች ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጉን መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና 200 ጥያቄዎች ያሉት መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፤ የፋርማሲ ተማሪዎች በሰኔ ወር መጨረሻ የወሰዱት ፈተና 100 ጥያቄዎች እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በመሆኑም "የብቃት ምዘና ፈተናው የጤና ሚኒስቴርን መስፈርት ባሟላ መልኩ 200 ጥያቄዎች የያዘ ፈተና በድጋሜ እንዲሰጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መወሰኑን" ተናግረዋል፡፡ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንም ገልፀዋል፡፡

ለፋርማሲ ተማሪዎች እንዲሁም ዲግሪ ይዘው የብቃት ምዘና ፈተናውን በድጋሜ መውሰድ ለሚፈልጉ የጤና ባለሙያዎች በቀጣይ ሁለት ቀናት ውስጥ የምዝገባ ጥሪ ይደረጋል ብለዋል፡፡

እስከ ቀጣይ ዓመት መጠበቅ ሳያስፈልግ የብቃት ምዘና ፈተናው በዚህ ወር እንደሚሰጥ መሪ ስራ አስፈጻሚው ለቲክቫህ አረጋግጠዋል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ 33 የማስተርስ እና ዘጠኝ የፒ.ኤች.ዲ. የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ለመቀበል ምዝገባ እያደረገ መሆኑን አሳውቋል፡፡

(ዩኒቨርሲቲው በ2017 የትምህርት ዘመን በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች የሚሰጣቸው የትምህርት አይነቶች እና አመልካቾች ሊወስዷቸው የሚመከሩ የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ዕድል_ጥቆማ
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ቴክኒካል አሲስታንቶች እና መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

➤ የሥራ መደብ፦ በ12 የትምህርት ክፍሎች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 87
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ
➤ የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

አመልካቾች ምዝገባ ለማድረግ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን በ PDF ፎርማት ይሄ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት በ https://bit.ly/aastujobapplication2024 ላይ በመግባት በምታገኙት ቅፅ መላክ ይሞርባችኋል፡፡

(ዩኒቨርሲቲው ያወጣው ሙሉ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#Update "ለፋርማሲ ተማሪዎች እንዲሁም የብቃት ምዘና ፈተና በድጋሜ ለሚፈተኑ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው በቅርቡ ይሰጣል፡፡" - ጤና ሚኒስቴር የፋርማሲ ተማሪዎች ባለፈው ሰኔ ከተሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና (Licensure Exam) ጋር የተያያዙ በርካታ ቅሬታዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና-ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል በጉዳዩ ዙሪያ…
#ተጨማሪ

ከጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና (Licensure Exam) ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ መድረሳቸውን ተከትሎ ተጨማሪ ማብራሪያ ጤና ሚኒስቴርን ጠይቀናል፡፡

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና በዚህ ወር በድጋሜ የሚሰጥ ሲሆን፤ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ የምዝገባ ጥሪ ዛሬ ወይም ነገ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

ሀገረ አቀፍ የመውጫ ፈተና #ያለፉ እና ዲግሪ #ያላቸው ሁሉም የጤና ባለሙያዎች (በድጋሜ ተፈታኝ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ) ለብቃት ምዘና ፈተናው መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ጤና ሚኒስቴር የሚጠቀመው የብቃት ምዘና ፈተና እርማት አሰራር በዓለም አቀፍ ደረጃ አገራት የሚጠቀሙበት መሆኑን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የገለፁት በሚኒስቴሩ የጤናና ጤና-ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል፤ (Average Result) አማካይ ውጤት የሚባል ነገር አለመኖሩን አስረድተዋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር የባለሙያዎችን የሙያ ብቃት ለመለካት የሚያስችልና በኅብረተሰቡ ላይ ምንም አይነት ጉዳት የማያደርሱ ባለሙያዎችን ለመለየት የሚያስችል 'ዝቅተኛ' የማለፊያ ነጥብ እንደሚቀመጥ ነው ኃላፊው ያብራሩት፡፡

የጤና ሚኒስቴር ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና፣ አካታች የሆኑ 200 ጥያቄዎች ያሉት መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

የብቃት ምዘና ፈተናው ለመውሰድ የጤና ባለሙያዎች ምዝገባ ነበጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡

@tikvahuniversity
ቅናሽ ተገኝቶማ አንምረውም ፤ ዕለታዊውን M-PESA ኢንተርኔት ፓኬጃችንን ገዝተን እስከ 50% ቅናሹን ማጣጣም ነው እንጂ!

የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
#ጥቆማ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ #ነርሲንግና_ሚድዋይፈሪ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአራት የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚፈልግ አሳውቋል፡፡

የማስተርስ ፕሮግራሞች፦
- በ Adult Health Nursing
- በ Surgical Nursing
- በ Pediatrics and Child Health Nursing
- በ Clinical Midwifery

በተመሳሳይ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ #የዓሳ_ሃብትና_ውሃ_ሳይንስ ትምህርት ክፍል በአራት የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚፈልግ አሳውቋል፡፡

የማስተርስ ፕሮግራሞች፦
- MSc in Fisheries and Aquaculture
- MSc in Aquatic and Wetland Ecosystem Management

የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች፦
- PhD in Fisheries and Aquaculture
- PhD in Aquatic and Wetland Ecosystem Management

በፕሮግራሞቹ ለማመልከት ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ማለፍ ያስፈልጋል፡፡ (የተቋማቱ ሙሉ መልዕክት ለከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
2024/10/03 06:23:51
Back to Top
HTML Embed Code: