Telegram Web Link
በ2017 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በርቀት መርሐግብሮች በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን መከታተል የምትፈልጉ ተማሪዎች ማመልከት እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በራሱ ፖሊሲና መስፈርት እንዲሁም የምዘናና የክፍያ ስርዓት ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ዝርዝር ማስታወቂያ የሚያወጣ ሲሆን፤ እስከዚያው ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ለመግቢያ ፈተና እንድትዘጋጁ ብሏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት ተጨማሪ መመዘኛዎች በዩኒቨርሲቲው እንደሚሰጥ ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity
#Contractual_Agreement

ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለ2017 ትምህርት ዘመን የአፈጻጸም ውል ስምምነት በመፈራረም ላይ ይገኛል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎችን በመመደብ የሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የ2016 ዓ.ም ቁልፍ ውጤት አመላካቾች (KPIs) አፈጻጸም ላይ ውይይት እያደረገ ነው።

ውይይቱን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት ፊርማ (Contractual Agreement) ለ2017 ትምህርት ዘመን እየተዋዋለ መሆኑም ታውቋል።

@tikvahuniversity
#OromiaEducationBureau

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናዎች ውጤትን ይፋ አድርጓል፡፡

በክልሉ የ8ኛ ክፍል የማለፊያ ነጥብ 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል፡፡ በክልሉ የገጠር አካባቢዎች ለተፈተኑ የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 48፣ ለሴቶች 45 ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 45 እና ለሴቶች 42 እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የ6ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት 👇
https://oromia6.ministry.et/#result

የ8ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት 👇
https://oromia.ministry.et/#result

ውጤት በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot

@tikvahuniversity
#ETQRA

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በከተማዋ በሚገኙ 59 ኮሌጆች ላይ ያደረገውን ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ተከትሎ 44 ኮሌጆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል፡፡

በዚህም ባለስልጣኑ "ከፍተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ እና የስትራቴጂ ጥሰት" ፈፅመዋል ያላቸውን 18 ኮሌጆች #አግዷል፡፡ እነርሱም፦

1. ብራይት ኮሌጅ ልደታ ካምፓስ
2. ብራይት ኮሌጅ ጀሞ ካምፓስ
3. ሸገር ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
4. ልቀት ኮሌጅ አራት ኪሎ ካምፓስ
5. ልቀት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
6. ላየን ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
7. ሀርመኒ ኮሌጅ ቂሊንጦ ካምፓስ
8. አልፋ ኮሌጅ ላንቻ ካምፓስ
9. አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ
10. አረና መልቲ ሚዲያ ኮሌጅ
11. ጌጅ ኮሌጅ ሾላ ካምፓስ
12. ሳትኮም ኮሌጅ
13. ኩዊንስ ኮሌጅ አምስት ኪሎ ካምፓስ
14. ሀርመኒ ኮሌጅ ሀና ማርያም ካምፓስ
15. ኩዊንስ ኮሌጅ መድሀኒዓለም ካምፓስ
16. ሀጌ ኮሌጅ
17. ኪያሜድ ኮሌጅ እንቁላል ፋብሪካ ካምፓስ
18. ኩዊንስ ኮሌጅ ዩሀንስ ካምፓስ

የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው ሌሎች 18 ኮሌጆች ደግሞ #የመጨረሻ_የጽሁፍ_ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም፦

1. ግሬት ቡልቡላ ኮሌጅ
2. ቢኤስቲ ኮሌጅ
3. ክቡር ኮሌጅ
4. ፋርማ ኮሌጅ
5. ቅድስት ልደታ ኮሌጅ
6. ኤግል ኮሌጅ
7. አፍሪካ ጤና ኮሌጅ
8. ናሽናል ኮሌጅ
9. ሀርቫርድ ኮሌጅ
10. ሰቨን ስታር ኮሌጅ
11. ራዳ ኮሌጅ
12. ሬፍትቫሊ ኮሌጅ ካራሎ ካምፓስ
13. ኬቢ ኮሌጅ
14. ያጨ ኮሌጅ
15. ኪያሜድ ኮሌጅ 22 ካምፓስ
16. ናይል ሳይድ ኮሌጅ
17. ኪያሜድ ኮሌጅ አየርጤና ካምፓስ
18. ዊልነስ ኮሌጅ

በተመሳሳይ መለስተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው 8 ኮሌጆች #የጽሁፍ_ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም፦

1. ያኔት ኮሌጅ 6 ኪሎ ካምፓስ
2. ዳማት ኮሌጅ ጊዎርጊስ ካምፓስ
3. ያኔት ኮሌጅ ሰፈረ ሰላም ካምፓስ
4. ኤክስፕረስ ኮሌጅ
5. ቅድስት ሃና ኮሌጅ
6. ግራንድ ማርክ ኮሌጅ
7. ኩዊንስ ኮሌጅ ሃና ማሪያም ካምፓስ
8. ሀራምቤ ኮሌጅ ሜክሲኮ ካምፓስ

ተቋማቱ እንደደረሳቸው አስተዳደራዊ እርምጃ መሰረት በአስር ቀናት ውስጥ እርምትና ማስተካከያ በማድረግ በጽሁፍ እና በአካል ሪፖርት ለባለስልጣኑ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

@tikvahuniversity
🔥 ትኩስ የስፖርት ዜናዎችን በቀላሉ በSMS እናግኝ! 💬

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30001 SMS በመላክ አሁኑኑ Elite ስፖርትን እንቀላቀል ! በቀን 2 ብር ብቻ!

በ Elite ስፖርት በሽ ዜናዎች

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት የማዕረግ ዕድገት ሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ የዶ/ር ቢንያም ጫቅሉ፣ ዶ/ር ቡሻ ታአ እና ዶ/ር ሰፊነው ዓለሙን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት አፅድቋል።

ሙሉ ፕሮፌሰር የሆኑ ምሁራን፦

1. ፕ/ር ቢንያም ጫቅሉ - በዲጂታል ሔልዝ እና ኢምፕሊመንቴሽን ሳይንስ
2. ፕ/ር ቡሻ ታአ - በሶሲዮሎጂ
3. ፕ/ር ሰፊነው ዓለሙ - በቬተሪናሪ ኢፒዲሞሎጂ እና ኢኮኖሚክስ

@tikvahuniversity
የጤና ሙያተኞች የሙያ ብቃት ምዘና ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ከመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ተማሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና ሰኔ 19/2016 ዓ.ም መስጠታቸው ይታወቃል፡፡

በ17 የጤና ሙያዎች የተሰጠውን ፈተና 15 ሺህ የሚጠጉ ተመዛኞች መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

ከምዘናው እርማት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በዚህ ሳምንት ተጠናቀው፤ ውጤቱ በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና-ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና በ28 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተሰጠ ነው፡፡

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራኖች እየተሠጠ የሚገኘው ልዩ የአቅም ማሻሻያ ስልጠናው ዛሬ አራተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል፡፡

ስልጠናው ለትምህርት ቤት አመራሮች ለአስር ቀናት እንዲሁም ለመምህራን ለሃያ ቀናት እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

ምስል፦ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በ12 ብር ብቻ 400 MB የእለታዊ ኢንተርኔት ፓኬጅ በM-PESA ስንገዛ፣  እስከ 50% ነፃ ተጨማሪ ዳታ እንፈስ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
Tikvah-University
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል። በአስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል ፈተና የማለፊያ ነጥብ ለወንድ ተማሪዎች 50%፣ ለሴት ተማሪዎች 47% እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች 45% እንደሆነ ቢሮው አሳውቋል። በዚህም በአስተዳደሩ በ2016 ዓ.ም ለፈተና ከቀመጡ 9,085 ተማሪዎች መካከል 5,673 ተማሪዎች ወይም 62.43 በመቶዎቹ ማለፋቸውን…
የድሬዳዋ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል፡፡

ተማሪዎች ከታች ባለው ሊንክ አማካኝነት መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤት መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡

ውጤት ለመመልከት 👇
https://www.gsix.diresrms.org/View_Result/get_result

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ8,500 በላይ ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል፡፡

ተመራቂዎቹ በፒኤችዲ፣ በማስተርስ እና በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በመደበኛው፣ በክረምት፣ በተከታታይ እና በርቀት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 58 በስፔሻሊቲ እና 4 በሰብ-ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ሐኪሞችም ያስመርቃል፡፡ በተጨማሪም በህክምና አመራርነት 6 ምሩቃንን በሰርትፍኬት ያስመርቃል፡፡

@tikvahuniversity
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የ 'PGDT' የክረምት መርሐግብር አመልካቾች ምዝገባ ከሐምሌ 26 እስከ 28/2016 ዓ.ም እንደሚካሔድ ገልጿል።

ትምህርት ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ያደርጋል። የኢንስቲትዩቱ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ዳግም ተፈታኞች የዛሬ ወር የመውጫ ፈተና መውሰዳቸው ይታወቃል። "ኢንስቲትዩቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመውጫ ፈተናው ላይ እየተወያየ መሆኑንና ውይይቱ ሲጠናቀቅ የተፈታኞች ውጤት እንደሚገለፅ" ነግረናችሁ ነበር። ተቋሙ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የነበረው…
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።

የኢንስቲትዩቱ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ዳግም ተፈታኞች የዛሬ ወር የመውጫ ፈተና መውሰዳቸው ይታወቃል።

ኢንስቲትዩቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመውጫ ፈተናው ላይ ውይይት ሲያደርግ መቆየቱ ለውጤቱ መዘግየት ምክንያት ሆኗል።

አሁን ላይ "ውጤቱ የተለቀቀ ስለሆነ፣ የተቋሙ ሬጅስትራር በመሔድ ማየት እንደሚችሉ" ኢንስቲትዩቱ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግሯል።

@tikvahuniversity
2024/10/02 12:29:18
Back to Top
HTML Embed Code: