Telegram Web Link
#MoE

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚያስመርቋቸው ተማሪዎች የሚሰጡት ዲግሪ የህትመት ሥራ በመንግሥት ሊከናወን ነው፡፡

የዲግሪ ህትመት ሥራው በሀገር ውስጥ እነደሚከናወንና አሰራሩም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ትናንት ባዘጋጀው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

"ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲግሪ በማሳተም ለተማሪዎቻቸው መስጠት አይችሉም" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዲግሪ የሚታተመው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እንደሚሆንና ለዚህም ተቋማቱ ክፍያ ለሚኒስቴሩ እንደሚፈፅሙ ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎቹን ዲግሪ የሚያትመው ተቋማቱ በሚልኩት መረጃ እና የተማሪዎቹ የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ውጤትን መሰረት በማድረግ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡

አሰራሩ ተግባራዊ ሲደረግ በሀገሪቱ የሚታየውን የሐሰተኛ ዲግሪ ህትመት ለማስቆም እንደሚያስችል ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

መንግሥት የ Security Printing ሥራ በሀገር ውስጥ በ2017 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ እንደሚጀምር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

@tikvahUniversity
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስቴም (STEM) ማዕከል ለ2016 ዓ.ም ከ200 በላይ የክረምት ሰልጣኝ ተማሪዎች ቅበላ አድርጓል።

ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ከ7-12ኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም የፈጠራ ፕሮጀክቶች ያሏቸው 30 ተማሪዎችም ወደ ማዕከሉ ገብተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በድምሩ 236 ሰልጣኝ ተማሪዎችን ለአንድ ወር ያህል የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት በማቅረብ እንደሚያሰለጥን ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ የመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰበት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ጥናት ማድረግ ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ስምንት አባላት ያሉት የተመራማሪዎች ቡድን ወደስፍራው በመላክ የአደጋውን መንስኤና ቀጣይ የአደጋ ስጋቶችን ለማወቅ ጥናት እየተደረገ መሆኑ ገልጿል።

ቡድኑ ፈጣንና ሳይንሳዊ ቅኝትና ጥናት በማድረግ፤ በቀጣይ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ የአደጋ ስጋት ቦታዎችን የመለየት ሥራ ያከናውናል ተብሏል።

"ከዚህ በኋላ በአካባቢው መሰል አደጋ ሊኖር ይችላል ወይ?" ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ማግኘት እንዲሁም "የአካባቢውን ነዋሪ እዛው ለማቆየት ወይም ወደሌላ ቦታ ለማዛወር' የሚረዱ ሳይንሳዊ ምክረ ሃሳቦችን ማቅረብ የጥናት ቡድኑ ትኩረት መሆኑ ተገልጿል።

አደጋው ያስከተለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች መለየትና መፍትሔዎችን ማመላከት ሌላኛው የጥናቱ ዓላማ መሆኑን ተጠቁሟል።

ከጂኦሎጂ፣ ከሲቪልና ከጂኦሎጂካል ምኅንድስና፣ ከጂኦግራፊ፣ ከግብርና እና ከሌሎች ዘርፎች የተወጣጡ ተመራማሪዎች፤ የጂአይኤስና ሪሞት ሴንሲንግ መሳሪያዎች በመጠቀም ጥናት እያደረጉ መሆኑ ተመልክቷል።

የቡድኑ የጥናት ውጤት በቅርቡ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ይፋ ይሆናል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ Dereja.com ፣ ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እና ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለዕጩ ምሩቃን የሥራ አውደ ርዕይ አካሒዷል።

አውደ ርዕዩ ተመራቂ ተማሪዎችን ከቀጣሪ ተቋማት እና ባለሃብቶች ጋር ለማገናኘት ያለመ ነበር ተብሏል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#MoE የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚያስመርቋቸው ተማሪዎች የሚሰጡት ዲግሪ የህትመት ሥራ በመንግሥት ሊከናወን ነው፡፡ የዲግሪ ህትመት ሥራው በሀገር ውስጥ እነደሚከናወንና አሰራሩም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ትናንት ባዘጋጀው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ…
ትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የዲግሪ እና የዲፕሎማ ስርተፊኬቶች ከመጪው ዓመት ጀምሮ በአገር ውስጥ ለማሳትም ዝግጅት አጠናቋል።

ይህም በትምህርት ዘርፍ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚታየውን የሐሰተኛ ትምህርት ሰነድ ህትመት ለማስቀረት እንደሚያስችል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሁሉም የትምህርት ተቋማት የተመራቂ ተማሪዎቻቸውን ዝርዝር መረጃ ለትምህርት ሚኒስቴር በመላክና ለዚህም ክፍያ በመፈፀም ለተማሪዎቻቸው የዲግሪ እና የዲፕሎማ ሰርተፊኬቶች የሚያገኙበት አሰራር ከመጪው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

@tikvahuniversity
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሥራቸውን ለማስቀጠል የሚያስችላቸውን ፈቃድ ለማግኘት እስከ ታኅሳስ 30/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደገና ምዝገባ ማከናወን እንዳለባቸው የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።

ዳግም ምዝገባው ያስፈለገው እንደ  ሀገር ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

በዚህም በመንግሥት እና በግል ተቋማት መካከል ያለው የፈቃድ አሰጣጥ የአሰራር ስርዓት ልዩነት እንደሚቀር የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሽፈራው ሽጉጤ ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ወደትምህርታቸው ተመልሰዋል።

ተማሪዎቹ ለሰባት ወራት ከትምህርት ገበታቸው መራቃቸውን በመግለፅ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ አቅርበው ነበር፡፡

የዩኒቨርሲቲው የህዝብና ኮሚዩኒኬሽን ግንኙነት ዳይሬክቶሬት "የክረምት ተማሪዎች እና ልዩ ሰልጣኝ መምህራን ከገቡ በኋላ ለጤና ተማሪዎቹ ጥሪ እንደሚደረግ" ለቲክቫህ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

በዚህም የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎቹ ከሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ እንደሚገኙ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል፡፡

@tikvahuniversity
#National_GAT

የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ የሚካሔደው ከሐምሌ 24/2016 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመሆኑም በ2017 የትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩት መስፈርቶችን በሟሟላት በተጠቀሰው ጊዜ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

ለመመዝገብ 👇
https://NGAT.ethernet.edu.et

@tikvahuniversity
በ2017 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በርቀት መርሐግብሮች በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን መከታተል የምትፈልጉ ተማሪዎች ማመልከት እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በራሱ ፖሊሲና መስፈርት እንዲሁም የምዘናና የክፍያ ስርዓት ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ዝርዝር ማስታወቂያ የሚያወጣ ሲሆን፤ እስከዚያው ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ለመግቢያ ፈተና እንድትዘጋጁ ብሏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት ተጨማሪ መመዘኛዎች በዩኒቨርሲቲው እንደሚሰጥ ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity
#Contractual_Agreement

ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለ2017 ትምህርት ዘመን የአፈጻጸም ውል ስምምነት በመፈራረም ላይ ይገኛል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎችን በመመደብ የሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የ2016 ዓ.ም ቁልፍ ውጤት አመላካቾች (KPIs) አፈጻጸም ላይ ውይይት እያደረገ ነው።

ውይይቱን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት ፊርማ (Contractual Agreement) ለ2017 ትምህርት ዘመን እየተዋዋለ መሆኑም ታውቋል።

@tikvahuniversity
#OromiaEducationBureau

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናዎች ውጤትን ይፋ አድርጓል፡፡

በክልሉ የ8ኛ ክፍል የማለፊያ ነጥብ 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል፡፡ በክልሉ የገጠር አካባቢዎች ለተፈተኑ የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 48፣ ለሴቶች 45 ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 45 እና ለሴቶች 42 እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የ6ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት 👇
https://oromia6.ministry.et/#result

የ8ኛ ክፍል ውጤት ኦንላይን ለማየት 👇
https://oromia.ministry.et/#result

ውጤት በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot

@tikvahuniversity
#ETQRA

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በከተማዋ በሚገኙ 59 ኮሌጆች ላይ ያደረገውን ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ተከትሎ 44 ኮሌጆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል፡፡

በዚህም ባለስልጣኑ "ከፍተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ እና የስትራቴጂ ጥሰት" ፈፅመዋል ያላቸውን 18 ኮሌጆች #አግዷል፡፡ እነርሱም፦

1. ብራይት ኮሌጅ ልደታ ካምፓስ
2. ብራይት ኮሌጅ ጀሞ ካምፓስ
3. ሸገር ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
4. ልቀት ኮሌጅ አራት ኪሎ ካምፓስ
5. ልቀት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
6. ላየን ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
7. ሀርመኒ ኮሌጅ ቂሊንጦ ካምፓስ
8. አልፋ ኮሌጅ ላንቻ ካምፓስ
9. አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ
10. አረና መልቲ ሚዲያ ኮሌጅ
11. ጌጅ ኮሌጅ ሾላ ካምፓስ
12. ሳትኮም ኮሌጅ
13. ኩዊንስ ኮሌጅ አምስት ኪሎ ካምፓስ
14. ሀርመኒ ኮሌጅ ሀና ማርያም ካምፓስ
15. ኩዊንስ ኮሌጅ መድሀኒዓለም ካምፓስ
16. ሀጌ ኮሌጅ
17. ኪያሜድ ኮሌጅ እንቁላል ፋብሪካ ካምፓስ
18. ኩዊንስ ኮሌጅ ዩሀንስ ካምፓስ

የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው ሌሎች 18 ኮሌጆች ደግሞ #የመጨረሻ_የጽሁፍ_ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም፦

1. ግሬት ቡልቡላ ኮሌጅ
2. ቢኤስቲ ኮሌጅ
3. ክቡር ኮሌጅ
4. ፋርማ ኮሌጅ
5. ቅድስት ልደታ ኮሌጅ
6. ኤግል ኮሌጅ
7. አፍሪካ ጤና ኮሌጅ
8. ናሽናል ኮሌጅ
9. ሀርቫርድ ኮሌጅ
10. ሰቨን ስታር ኮሌጅ
11. ራዳ ኮሌጅ
12. ሬፍትቫሊ ኮሌጅ ካራሎ ካምፓስ
13. ኬቢ ኮሌጅ
14. ያጨ ኮሌጅ
15. ኪያሜድ ኮሌጅ 22 ካምፓስ
16. ናይል ሳይድ ኮሌጅ
17. ኪያሜድ ኮሌጅ አየርጤና ካምፓስ
18. ዊልነስ ኮሌጅ

በተመሳሳይ መለስተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው 8 ኮሌጆች #የጽሁፍ_ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም፦

1. ያኔት ኮሌጅ 6 ኪሎ ካምፓስ
2. ዳማት ኮሌጅ ጊዎርጊስ ካምፓስ
3. ያኔት ኮሌጅ ሰፈረ ሰላም ካምፓስ
4. ኤክስፕረስ ኮሌጅ
5. ቅድስት ሃና ኮሌጅ
6. ግራንድ ማርክ ኮሌጅ
7. ኩዊንስ ኮሌጅ ሃና ማሪያም ካምፓስ
8. ሀራምቤ ኮሌጅ ሜክሲኮ ካምፓስ

ተቋማቱ እንደደረሳቸው አስተዳደራዊ እርምጃ መሰረት በአስር ቀናት ውስጥ እርምትና ማስተካከያ በማድረግ በጽሁፍ እና በአካል ሪፖርት ለባለስልጣኑ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/04 15:27:19
Back to Top
HTML Embed Code: