Telegram Web Link
የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጡ የአሰልጣኞች ስልጠና (ToT) ዛሬ ተጠናቋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና ከሐምሌ 17/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተሰጥቷል።

የአሰልጣኞች ስልጠናው በትምህርት አመራርነት፣ በእንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የትምህርት መስኮች በማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ትኩረት በማድረግ መሰጠቱ ታውቋል።

የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት ስልጠና የፊታችን ሰኞ ይጀምራል።

ስልጠናው ለትምህርት ቤት አመራሮች ለአስር ቀናት፤ ለመምህራን ለ20 ቀናት ይሰጣል።

ምስል፦ ወሎ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና የፊታችን ሰኞ ይጀምራል።

የአቅም ግንባታ ሰልጣኞቹ ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6፡00 ብቻ ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ይጠበቅባቸዋል።

ስልጠናውን የሚሰጡ የተመረጡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰልጣኞቹ ጥሪ እያደረጉ ነው።

ሰልጣኞች ወደየተመደባችሁበት ተቋም ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ መያዝ ይኖርባችኋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰልጣኞች የምዝገባ ቦታ፦ ፔዳ ግቢ

(ወልድያ፣ ባሕር ዳር እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጥሪ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
በ2015 ዓ.ም ተቋርጦ የነበረው የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክረምት ትምህርት መርሐግብር በዚህ ዓመት መቀጠሉ ይታወቃል።

ባለፉት ዓመታት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዲሁም በፀጥታ ችግር ምክንያት ጫና ውስጥ የቆየው የክረምት ትምህርት ዘንድሮ መሰጠት ጀምሯል።

የ2016 ዓ.ም የክረምት መርሐግብር ትምህርት ከሐምሌ ወር ሁለተኛ ሳምንት ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።

ምስል፦ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ሳምንት ከ1 ሺህ በላይ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ የክረምት መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ IELTS ፈተና ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) ይሰጣሉ፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገፅ ላይ በመግባት ኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations

ለፈተናው ዝግጅት የሚያስፈልግዎትን ስልጠና እና ምክር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል።

በአስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል ፈተና የማለፊያ ነጥብ ለወንድ ተማሪዎች 50%፣ ለሴት ተማሪዎች 47% እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች 45% እንደሆነ ቢሮው አሳውቋል።

በዚህም በአስተዳደሩ በ2016 ዓ.ም ለፈተና ከቀመጡ 9,085 ተማሪዎች መካከል 5,673 ተማሪዎች ወይም 62.43 በመቶዎቹ ማለፋቸውን ቢሮው ገልጿል።

ውጤት ለመመልከት 👇
https://www.geight.diresrms.org/View_Result/get_result

@tikvahuniversity
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና የተመደባችሁ ወደ ተቋሙ መግቢያ ቀን ነገ ሐምሌ 21/2016 ከጠዋት 2፡00-6፡00 በዋናው ሬጅስትራር ሕንጻ መሆኑ ተገልጿል፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች በሚገኙ 18 ካሞፓሶቹ ያስተማራቸውን 9,000 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በጤና፣ በቢዝነስ፣ በማኅበራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መስኮች በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ
#MoE

መንግሥት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን  'ኮደሮችን' ለማሰልጠን ያለመ ኢኒሼቲቭ አስጀምሯል።

ለሦስት ዓመት የሚቆየው ኢኒሼቲቩ፤ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው።

የፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኮርሶች #ከክፍያ_ነፃ ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

የትምህርት ይዘቶቹን በኦንላይን ተምረው የሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው የምስክር ወረቀት ያገኛሉ።

ከ6-7 ሳምንታት በሚፈጀው የኦንላይን ስልጠና ለመሳተፍ እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል የሚያሳይ ቪዲዮ በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ 👇  https://youtu.be/-zSmhhD5qE4

@tikvahuniversity
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለስምንት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት የማዕረግ ዕድገት ሰጥቷል።

ሙሉ ፕሮፌሰር የሆኑ ምሁራን፦

1. ዶ/ር አህመድ ዘይኑዲን ➧ ፕ/ር በፓራሲቶሎጂ ህክምና
2. ዶ/ር ቤይራ ሀይሉ ➧ ፕ/ር በኔማቶሎጂ
3. ዶ/ር ሌሊሳ ሴና - ፕ/ር በኅብረተሰብ ጤና ኢፒዴሚዮሎጂ
4. ዶ/ር ሙባረክ አበራ ➧ ፕ/ር በአዕምሮ ጤና
5. ዶ/ር ሙሉመቤት አበራ ➧ ፕ/ር በኅብረተሰብ ጤና
6. ዶ/ር ስራውድንቅ ፍቅረየሱስ ➧ ፕ/ር በምግብ ሳይንስና ድኅረ-ምርት ቴክኖሎጂ
7. ዶ/ር የትናየት በቀለ ➧ ፕ/ር በምግብ ሳይንስና ቴክኖሎጂ
8. ዶ/ር ዘሪሁን አየነው ➧ ፕ/ር በሰው ሃብት አስተዳደር

@tikvahuniversity
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 27 እና 28/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

በዚህም በ2011 ዓ.ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራቹሁ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ነባር የክረምት ተማሪዎች በተገለፁት ቀናት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

ለምዝገባ ወደ ተቋሙ ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ መያዝ ይኖርባችኋል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የክረምት ስቴም ሰልጣኝ ተማሪዎችን ተቀብሏል።

ዩኒቨርሲቲው 347 አዲስ የክረምት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ (STEM) ሰልጣኞችን ተቀብሏል።

@tikvahuniversity
2024/10/04 19:24:02
Back to Top
HTML Embed Code: