Telegram Web Link
#AAEB

በአዲስ አበባ በኦንላይን እየተካሔደ የሚገኘው የ2017 ዓ.ም የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዝገባ ለተጨማሪ 15 ቀናት ተራዝሟል፡፡

በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው በኦንላይን የተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 30/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ለምዝገባው ምንም አይነት ክፍያ እንደማይጠየቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወንድሙ ኡመር ገልፀዋል፡፡

ወላጆች ይህንን ተገንዝበው በተራዘመው ጊዜ ልጆቻቸውን ያለምንም ክፍያ እንዲያስመዘግቡና የመማሪያ መፃሕፍት እዲወስዱ የመከሩት ኃላፊው፤ ከዚህ ተቃራኒ በሆነ አሰራር ለምዝገባው ክፍያ የሚጠይቁ ትምህርት ቤቶች በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

@tikvahuniversity
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች መግቢያ እሑድ ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡ ምዝገባ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡

የምዝገባና የመማሪያ ቦታ፦

➧ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በአባያ ካምፓስ፣
➧ የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች ሳውላ ካምፓስ፣
➧ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ፣ የህግ ትምህርት ቤት እና የስነ-ትምህርትና ስነ-ባህሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዋናው ግቢ፡፡

ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች አቅም ማጎልበቻ ሰልጣኞች መግቢያ ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ የስልጠና ቦታ፦ በጫሞ ካምፓስ፡፡

ሁሉም የክረምት ተማሪዎች እና ሰልጣኞች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተከታታይ መርሐግብር በመጀመርያ ዲግሪ #በፋሽን_ዲዛይን ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

የምዝገባ ጊዜው የሚያበቃው፦
አርብ ሐምሌ 19/ 2016 ዓ.ም

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የወጣውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መስፈርት ወይም መቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት ተከታታይ ስልጠና ሰልጣኞች ምዝገባ ሐምሌ 24 እና 25/2016 ዓ.ም እንደሚካሔድ አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ በየኮሌጆቻችሁ የሬጅስትራር ቢሮዎች

ለነባር የክረምት የ 'PGDT' ስልጠና ተከታታዮች ስልጠናው የሚሰጥ ሲሆን፤ በ2016 ዓ.ም ክረምት የሚጀመር አዲስ የ 'PGDT' ስልጠና ፕሮግራም እንደማይኖር ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
3,600 በላይ ኮምፒውተሮች በአዲስ አበባ ለሚገኙ 74 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊሰራጩ ነው፡፡

በከተማዋ ለ2017 የትምህርት ዘመን የሚሰራጩ ከ3,600 በላይ ኮምፒውተሮች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወንድሙ ዑመር ለኢዜአ ተናግረዋል።

የትምህርት ቁሳቁሶች ከነሐሴ ወር መጀመሪያ አንስቶ ለተማሪዎች እንደሚከፋፈል ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ዩኒቨርሲቲዎች ለልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት የአቅም ግንባታ ሰልጣኞች ጥሪ እያደረጉ ነው።

ሰልጣኞች ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6፡00 ብቻ ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ይጠበቅባቸዋል።

ሰልጣኞች ወደየተመደባችሁበት ተቋም ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል።

የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም በተመረጡ 28 የስልጠና ማዕከላት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የክረምት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጡ የአሰልጣኞች ስልጠና (ToT) በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።

የአሰልጣኞች ስልጠና ከሐምሌ 17-19/2016 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መርሐግብር ያሳያል።

የአሰልጣኞች ስልጠናው በትምህርት አመራርነት፣ በእንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የትምህርት መስኮች በማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ዳግም ተፈታኞች ሰኔ 24/2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና መውሰዳቸው ይታወቃል።

በርካታ ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ሳይገለፅ ዘገየ ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ አድርሰዋል።

በጉዳዩ ላይ የኢንስቲትዩቱን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ጠይቀናል።

"ኢንስቲትዩቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመውጫ ፈተናው ላይ እየተወያየ መሆኑን" ዳይሬክቶሬቱ ለቲክቫህ ተናግሯል። ምንም እንኳን የመወያያ ጉዳዮቹን ዝርዝር ባይገልፁም።

"የሁለቱ ተቋማት ውይይት በቅርቡ መቋጫ እንደሚያገኝና የተፈታኞች ውጤትም እንደሚገለፅ" ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከኢንስቲትዩቱ ሰምቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለ 2,135 ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና በኦንላይን መስጠቱ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት የ STEM ማጠናከሪያ ትምህርት ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል።

ተማሪዎቹ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡና የተሻለ ውጤት ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
የዲላ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል ለክረምት መርሐግብር ሰልጣኞች ቅበላ አድርጓል።

የሳይንስ ዝንባሌ ያላቸውና ከጌዴኦ ዞን ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 240 ከ7-12ኛ ክፍል ተማሪዎች ስልጠናውን ይወስዳሉ ተብሏል።

ተማሪዎች ለሁለት ወራት በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ፤ የምግብ፣ የህክምና እና የመኝታ አገልግሎት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ማስታወሻ

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ለመከታተል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ጥሪውን ባለፈው ወር ሰኔ 8/2016 ዓ.ም ያደረገ ሲሆን፤ ጥሪው አለመቀየሩን እንድናረጋግጥላቸው በርካታ ተማሪዎች ጠይቀውናል።

ጥሪው #አለመቀየሩን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

ሪፖርት ማድረጊያ ቦታዎች፦

- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በፖሊ ካምፓስ
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ ዓባይ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው
➧አራት ጉርድ ፎቶግራፍ
➧ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ

@tikvahuniversity
ዩኒቨርሲቲዎች ለክረምት ልዩ ሰልጣኝ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ጥሪ እያደረጉ ነው።

ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ሰልጣኞቹ ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6፡00 ብቻ ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ/ተቋም መግባት ይጠበቅባቸዋል።

ሰልጣኞች ወደየተመደባችሁበት ተቋም ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል።

(የደብረ ብርሃን እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
AAU 2017 E.C. Academic Calendar.pdf
1.2 MB
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2024/25 አካዳሚክ ካላንደር
2024/10/04 23:16:21
Back to Top
HTML Embed Code: