Telegram Web Link
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን ጉዳይ

በርካታ ክልሎች የመምህራን ደመወዝ መክፈል ተስኗቸው መምህራን ለከፋ ችግር እየተጋለጡ እንደሚገኙ ቅሬታቸውን በተደጋጋሚ ያቀርባሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፤ "ክልሎች ለመምህራን ተብሎ የተሰጣቸውን በጀት ለተባለው ጉዳይ ባለማዋላቸው እየተፈጠረ ያለ ችግር እንደሆነ" ገልፀዋል፡፡

ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ትምህርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እየተነጋገረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

የመምህራኑ የደመወዝ ይከፈለን ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ በትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረውም ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

በወላይታ ዞን፣ ጋሞ ዞን፣ ሀዲያ ዞን እና ትግራይ ክልል የሚገኙ መምህራን የወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው መቆየቱ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
2017 የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚደረግ አዲስ የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡

የዋጋ ትመናው ጊዜውን ያላገናዘበ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር በቀን እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ የተጠየቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፤ "ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቀን ተተምኖ የሚመደበው ሒሳብ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ሲደረጉ የነበሩ ጥናቶች እና ሲሰሩ የቆዩ ሥራዎች እየተጠናቀቁ" መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

"እስከ ነሐሴ ድረስ ሥራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል" ብለዋል፡፡

@tikvahuniversity
መንግሥት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደመወዝ ላይ ማሻሻል ለማድረግ እየሠራሁ ነው አለ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የዩኒቨርሲቲ መምህራን ደመወዝ ማሻሻያን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት፤ "የዩኒቨርሲቲ መምህራን ደመወዝ አነስተኛ ነው፣ ይህንን ችግር ለመፍታት ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር እየተነጋገርን ነው" ብለዋል፡፡

ከኮሚሽኑ ጋር በመሆን ጥናቶች እየተደረጉ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፤ እስከ ህዳር 2017 ዓ.ም ድረስ ጥናቱ እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል፡፡

ኑሮ የከበዳቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራን ተጓዳኝ የጉልበት ሥራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ፣ የቤት ኪራይ መክፈል የተሳናቸው መምህራን ደግሞ በተማሪዎች ዶርም እያደሩ እንደሆነ ሲዘገብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
#WachemoUniversity

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል።

ዳዊት ሃየሶ (ዶ/ር) ከሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ጀምሮ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተወከሉ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ያሳያል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ታምራት ታገሰ (ዶ/ር) በሙስናና በሃብት ምዝበራ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

ከኦዲት ግኝት ጋር በተያያዘ በዚህ ዓመት ብቻ የወላይታ ሶዶ፣ ጋምቤላ እና ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል_ማስታወሻ የህንድ መንግስት በ2023/24 ለ55 ኢትዮጵያዊያን ነፃ የትምህርት ዕድል ይሰጣል። በህንድ ባህላዊ ግንኙነት ም/ቤት (ICCR) የቀረበው ነፃ የትምህርት ዕድሉ፤ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ድህረ ዶክትሬት የትምህርት ፕሮግራሞች የተካተቱበት ነው። በህንድ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት የሚሰጠው ዕድሉ፤ ከክፍያ ነፃ የትምህርት አገልግሎቶች እና ነፃ የአየር በረራ ትኬት ለአሸናፊዎች…
በ2024 በህንድ ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ከሆኑ 55 ኢትዮጵያዊያን መካከል በመጀመሪያ ዙር 35 ምሁራን በፕሮግራሙ ተቀባይነት አጊኝተው ቪዛ ወስደዋል፡፡

እነዚህ 35 ነፃ የትምህርት ዕድሉ ተጠቃሚዎች፣ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ማስተርስ ዲግሪ እና የዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን በህንድ ይከታተላሉ፡፡

በህንድ ባህላዊ ግንኙነት ም/ቤት (ICCR) የቀረበው ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚዎቹ፤ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ከሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ እንደሆኑ ከህንድ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የነፃ ትምህርት ዕድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑ ቀሪ 20 ምሁራን/ተማሪዎች በሒደት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

በህንድ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት የሚሰጠው ዕድሉ፤ ከክፍያ ነፃ የትምህርት አገልግሎቶች እና ነፃ የአየር በረራ ትኬት ለአሸናፊዎች ያቀርባል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
ለ3ኛ ዙር ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ፕሮግራም የተመዝግባችሁና ለፈተና ያለፋችሁ ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ የሆናችሁ፤ ፈተናው ከሐምሌ 9-12/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) አሳውቋል፡፡ ወደ 3ኛ ዙር ፈተና ያለፋችሁ ስም ዝርዝር በአስተዳደሩ የሳይበር ታለንት ማዕከል የቴሌግራም አድራሻ https://www.tg-me.com/cteinsa በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑ…
ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ባዘጋጀው የ2016 ዓ.ም “ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ” ፕሮግራም ላይ ተመዝግባችሁ ለ3ኛ ዙር ፈተና ያለፋችሁ ነዋሪነታችሁ ከአዲስ አበባ ውጪ በተለያዩ ክልሎች የሆነ እንዲሁም አድራሻ ስትሞሉ አዲስ አበባ ብላችሁ ሞልታችሁ በተለያየ ምክንያት ወደ ክልል የሔዳችሁ፤ ፈተናው የሚሰጠው ሐምሌ 18 እና 19/2016 ዓ.ም ከታች በተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች መሆኑን አሳውቋል።

ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች፦
1. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
2. ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
3. ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ
4. ጅማ ዩኒቨርሲቲ

የፈተና ቀንና ሰዓት፦
- ስማችሁ ከA - L የሚጀምር ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ ከሰዓት 7፡30
- ስማችሁ ከ M-Z የሚጀምር ዓርብ ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፣ ከሰዓት 7፡30

ለፈተና ስትሔዱ መታወቂያ እና ፕሮጀክት የምታቀርቡበት ላፕቶፕ መያዝ እንዳትዘነጉ።

ለ3ኛ ዙር ፈተና ያለፋችሁ ስም ዝርዝራችሁን በINSA የሳይበር ታለንት ማዕከል የቴሌግራም አድራሻ https://www.tg-me.com/cteinsa በመግባት ማየት ትችላላችሁ።

ከተገለፁት ክልሎች ውጪ የምትገኙ እና ለ3ኛ ዙር ያለፋችሁ የፈተና ፕሮግራምና የመፈተኛ ቦታን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ አስተዳደሩ ገልጿል።

@tikvahuniversity
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ሊያደርግ ነው።

የዳግም ምዝገባ ሂደቱን ለማስረዳትና ባለሥልጣኑ በሥራ ላይ ባዋለው የከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ እንዲሁም የአሰራር ስታንዳርድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ያደርጋል።

በዚህም የሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ወይም አንድ ተወካያቸው ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ባለሥልጣኑ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተቋሙ አሳስቧል።

@tikvahuniversity
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የክረምት ነባር የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም የ PGDT ፕሮግራም ሰልጣኞች ምዘገባ ሐምሌ 18 እና 19/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ቲቶሪያል ትምህርት ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ · የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
ቅመም Itel Proን ዛሬውኑ በመግዛት ለ90 ቀናት በ 90 ጊባ የቲክቶክ ጥቅል በሽ በሽ እንበል! አሁኑኑ ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች በማቅናት ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር ቅመም Itel Proን እንግዛ!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#SafaicomEthiopia
#MpesaSafaricom
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና

አኃዛዊ መረጃ፦

52,300 - የሁለተኛ ደረጃ መምህራን
8,070 - የትምህርት ቤት አመራሮች
60,370 - አጠቃላይ ተሳታፊዎች
28 - ስልጠናው የሚሰጥባቸው ተቋማት

► የአሰልጣኞች ስልጠና ከሐምሌ 17-19/2016 ዓ.ም ይሠጣል፡፡

► ሰልጣኝ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች እስከ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም እስከ ቀን 6፡00 በየተመደቡበት ተቋም ይገባሉ፡፡

► ስልጠናው ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ይሰጣል።

► የስልጠናው የማስጀመሪያ መርሐግብር ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ቀን 8፡00 በኦንላይን ይካሔዳል፡፡

► ስልጠናው የሚሰጥባቸው የትምህርት አይነቶች፦ ሒሳብ፣ እንግሊዝኛ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ፊዚክስ፡፡

► የማስተማር ስነዘዴ፣ አይ.ሲ.ቲ. እና የስነ-ልቦናና የማኅበራዊ ድጋፍ ሌሎች የስልጠናው የትኩረት መስኮች ናቸው፡፡

@tikvahuniversity
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ህይወታቸውን ላጡ እንዲሁም ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፡፡ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ይመኛል።

@tikvahuniversity
#AAEB

በአዲስ አበባ በኦንላይን እየተካሔደ የሚገኘው የ2017 ዓ.ም የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምዝገባ ለተጨማሪ 15 ቀናት ተራዝሟል፡፡

በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው በኦንላይን የተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 30/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ለምዝገባው ምንም አይነት ክፍያ እንደማይጠየቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወንድሙ ኡመር ገልፀዋል፡፡

ወላጆች ይህንን ተገንዝበው በተራዘመው ጊዜ ልጆቻቸውን ያለምንም ክፍያ እንዲያስመዘግቡና የመማሪያ መፃሕፍት እዲወስዱ የመከሩት ኃላፊው፤ ከዚህ ተቃራኒ በሆነ አሰራር ለምዝገባው ክፍያ የሚጠይቁ ትምህርት ቤቶች በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

@tikvahuniversity
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች መግቢያ እሑድ ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡ ምዝገባ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡

የምዝገባና የመማሪያ ቦታ፦

➧ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በአባያ ካምፓስ፣
➧ የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች ሳውላ ካምፓስ፣
➧ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ፣ የህግ ትምህርት ቤት እና የስነ-ትምህርትና ስነ-ባህሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዋናው ግቢ፡፡

ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች አቅም ማጎልበቻ ሰልጣኞች መግቢያ ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ የስልጠና ቦታ፦ በጫሞ ካምፓስ፡፡

ሁሉም የክረምት ተማሪዎች እና ሰልጣኞች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተከታታይ መርሐግብር በመጀመርያ ዲግሪ #በፋሽን_ዲዛይን ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

የምዝገባ ጊዜው የሚያበቃው፦
አርብ ሐምሌ 19/ 2016 ዓ.ም

አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የወጣውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መስፈርት ወይም መቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት ተከታታይ ስልጠና ሰልጣኞች ምዝገባ ሐምሌ 24 እና 25/2016 ዓ.ም እንደሚካሔድ አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ በየኮሌጆቻችሁ የሬጅስትራር ቢሮዎች

ለነባር የክረምት የ 'PGDT' ስልጠና ተከታታዮች ስልጠናው የሚሰጥ ሲሆን፤ በ2016 ዓ.ም ክረምት የሚጀመር አዲስ የ 'PGDT' ስልጠና ፕሮግራም እንደማይኖር ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
3,600 በላይ ኮምፒውተሮች በአዲስ አበባ ለሚገኙ 74 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊሰራጩ ነው፡፡

በከተማዋ ለ2017 የትምህርት ዘመን የሚሰራጩ ከ3,600 በላይ ኮምፒውተሮች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወንድሙ ዑመር ለኢዜአ ተናግረዋል።

የትምህርት ቁሳቁሶች ከነሐሴ ወር መጀመሪያ አንስቶ ለተማሪዎች እንደሚከፋፈል ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
2024/10/02 02:44:38
Back to Top
HTML Embed Code: