Telegram Web Link
አኃዛዊ መረጃ፦

አጠቃላይ የተመዘገቡ ► 701,749
ለፈተና የተቀመጡ ► 684,372
በአማራ ክልል ያልተፈተኑ ► 9,152
ፈታኞች ► 20,926
ሱፐርቫይዘሮች ► 3,523
ጣቢያ ኃላፊዎች ► 4,270
የዓይነ ስውራን ተፈታኝ አንባቢዎች ► 377
የመልስ ወረቀት ቆጣሪ ► 211
የፌዴራል ፖሊሶች ► 8,100

በወረቀት የተሰጠው ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች/ካምፓሶች ባሉ 122 የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ተከናውኗል፡፡

የኦንላይን ፈተናው በ46 ካምፓሶች፣ በአንድ ልዩ ማዕከል (አዲስ አበባ፣ አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት) እንዲሁም በ 45 ትምህርት ቤቶች ውስጥ በአጠቃላይ በ92 የመፈተኛ ማዕከላት ተሰጥቷል፡፡

@tikvahuniversity
በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ እና ሕክምና ኮሌጅ ተማሪዎች ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም በተቋሙ ዋና ግቢ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@tikvahuniversity
#TVTI

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚካሔደው ሐምሌ 18 እና 19/2016 ዓ.ም መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል፡፡

በመሆኑም በተገለፁት ቀናት ብቻ በተቋሙ ሬጅስትራር ቢሮ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ተብሏል፡፡

በ2015 ዓ.ም የክረምት ስልጠናችሁን አጠናቃችሁ የመውጫ ፈተና ሳትወስዱ የቀራችሁ የዋናው ግቢ እና የሳተላይት (ባህርዳር፣ ኮምቦልቻ፣ አዲግራት እና ማይጨው) ሰልጣኞች ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም በስልጠና ተቋማቹ በአካል በመገኘት ሪፖርት አንድታደርጉ ኢንስቲትዩቱ እናሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንደሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በከተማዋ በሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው፥ በ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,046 ተማሪዎች መካከል 80,198 ተማሪዎች ወይም 94.3 በመቶዎቹ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል፡፡

ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የመለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡ ወይም ከስር የተቀመጠውን የቴሌግራም ቦት ይጠቀሙ፡፡

ውጤት ለማየት፦ https://aa6.ministry.et/#/result

በቴሌግራም ቦት፦ @emacs_ministry_result_qmt_bot

@tikvahuniversity
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ #የድኅረ_ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ኮርስ ያልጨረሳችሁ ነባር የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ በድኅረ ምረቃ ሬጅስትራር ቢሮ አድርጉ ተብሏል።

ትምህርት ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም የሚጀመር ይሆናል፡፡

የጤናና ሕክምና ሳይንስ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት በሐረር የኮሌጁ ግቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
የመምህራንና ትምህርት አመራሮች ልዩ የክረምት ስልጠና

ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ክረምት ይሰጣል የተባለውን ልዩ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ጊዜ ይፋ አድርጓል።

በዚህም የመምህራንና ትምህርት አመራሮች ልዩ የክረምት ስልጠና ከሐምሌ 22-ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ስልጠናው የሚመራበት የአፈጻጸም መምሪያ ለሁሉም አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል፡፡

በዚህም መሰረት፦

► ሁሉም ሰልጣኝ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6፡00 በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ፡፡

► የትምህርት ቤት አመራሮች ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም እንዲሁም መምህራን ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም ስልጠና አጠናተው ከዩኒቨርሲቲዎቹ ይወጣሉ፡፡

ስለሆነም ሁሉም የትምህርት ቢሮዎች በተጠቀሰው መርሐግብር መሰረት ለሰልጣኝ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ጥሪ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ለክልል/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች በላከው ሰርኩላር አሳስቧል።

@tikvahuniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት ተማሪዎች እና በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ ልዩ ሰልጣኞች ምዝገባ ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የተመለመላችሁ ልዩ ሰልጣኞች ምዝገባ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ብቻ የሚከናወን ሲሆን፤ የነባር የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ትምህርታችሁን በምትከታተሉበት ኮሌጅ/ኢንስቲትዩት ይካሔዳል ተብሏል፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#DebreBerhanUniversity

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ልማት ማዕከል በድጋሜ ለማቋቋም ወስኗል።

ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ "የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠት አቁሟል፣ ትምህርት ክፉሉም ተዘግቷል" የሚሉ በርካታ ትችቶች ሲነሱበት ቆይቷል።

ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ "ከዚህ በፊት የነበረውን የባህል ማዕከል የበለጠ ለማጠናከር የአማርኛ ቋንቋን በማካተት ማዕከል ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል" ብሏል።

በዳሬክቶሬት ደረጃ የሚቋቋመው ማዕከል፥ የአካባቢውን ባህል፣ ታሪክ እና የአማርኛ ቋንቋ ስነ-ፅሁፍ ማስተማርና ማጥናት ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል።

የአማርኛ እና የታሪክ ትምህርት ፕሮግራሞች ለተማሪ ምርጫ ቀርበው፥ በዩኒቨርሲቲው ሌጅስሌሽን ላይ የተቀመጡን ዝቅተኛ የተማሪ ቁጥር ማሟላት የሚችሉ ከሆነ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሰጡ እንደሚደረግ መግለጫው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ IELTS ፈተና ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) ይሰጣሉ፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገፅ ላይ በመግባት ኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations

ለፈተናው ዝግጅት የሚያስፈልግዎትን ስልጠና እና ምክር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን ጉዳይ

በርካታ ክልሎች የመምህራን ደመወዝ መክፈል ተስኗቸው መምህራን ለከፋ ችግር እየተጋለጡ እንደሚገኙ ቅሬታቸውን በተደጋጋሚ ያቀርባሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፤ "ክልሎች ለመምህራን ተብሎ የተሰጣቸውን በጀት ለተባለው ጉዳይ ባለማዋላቸው እየተፈጠረ ያለ ችግር እንደሆነ" ገልፀዋል፡፡

ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ትምህርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እየተነጋገረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

የመምህራኑ የደመወዝ ይከፈለን ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ በትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረውም ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

በወላይታ ዞን፣ ጋሞ ዞን፣ ሀዲያ ዞን እና ትግራይ ክልል የሚገኙ መምህራን የወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው መቆየቱ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
2017 የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚደረግ አዲስ የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡

የዋጋ ትመናው ጊዜውን ያላገናዘበ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር በቀን እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ የተጠየቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፤ "ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቀን ተተምኖ የሚመደበው ሒሳብ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ሲደረጉ የነበሩ ጥናቶች እና ሲሰሩ የቆዩ ሥራዎች እየተጠናቀቁ" መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

"እስከ ነሐሴ ድረስ ሥራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል" ብለዋል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/02 20:40:39
Back to Top
HTML Embed Code: