Telegram Web Link
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የክረምት መርሐግብር ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም የ PGDT ሰልጣኞ የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ሐምሌ 15 እና 16/2016 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አሳውቋል።

በትምህርት ሚኒስቴር ስፖንሰርነት ትምህርታችሁን የምትከታተሉ ሰልጣኞች ከምትሰሩበት መስሪያ ቤት መገጣጠሚያ፥ በተለያዩ ተቋማት ስፖንሰር አድራጊነት ትምህርታችሁን የምትከታተሉ ሰልጣኞች መገጣጠሚያና የክፍያ ደረሰኝ እንዲሁም በግል ትምህርታችሁን የምትከታተሉ ሰልጣኞች አስፈላጊውን የክፍያ ደረሰኝ በመያዝ በአካል በመቅረብ ምዝገባ ለ,ማድረግ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
የ79 ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ

የ12 ልጆች አባት ናቸው፡፡ ተማሪ በዛብህ ጡምዶሎ፡፡ በሀዲያ ዞን በጃቾ መሠናዶ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለው፣ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

እስከ 7ኛ ክፍል ድረስ ተምረው እንደነበርና በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ምክንያት ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን ይጠቅሳሉ። ከዛም በግብርና ሥራ ላይ መሰማራታቸውን ያነሳሉ፡፡

የመማር ፍላጎታቸው ከፍተኛ ስለነበር፣ ያቋረጡትን ትምህርታቸውን ቀጥለው ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

እኚህ አባት የሰው ልጅ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ትምህርት ለመማርና ዕውቀት ለመገብየት ዕድሜ እንደማይገድበው ጥሩ ተምሳሌት ናቸው፡፡ #ዋቸሞዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የክረምት መርሐግብር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ነባር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 18 እና 19/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የቲቶሪያል ትምህርት ከሐምሌ 20/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#National_Exam

የመጀመሪያው ዙር አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከረዕቡ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በወረቀት እና በኦንላይን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

በዛሬው የሦስተኛ ቀን ፈተና፣ በጠዋቱ መርሐግብር የታሪክ ትምህርት ፈተና የተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት የኢኮኖሚክስ ትምህርት ፈተና ይሰጣል፡፡

ሁለተኛው ዙር ፈተና ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

የከተማ አቀፍ ፈተናው የማለፊያ ነጥብ 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ 45 እና ከዚያ በላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219 ተማሪዎች መካከል 67,903 ተማሪዎች (78.9 በመቶ) 50 በመቶና ከዚያ በላይ ማምጣታቸውን በቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ገልፀዋል።

ከስር የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም፣ የመለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል፡፡

ውጤት ለማየት 👇
https://aa.ministry.et/account#/student-result

በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ይፋ የሚደረግ መሆኑን ከቢሮውየተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡ #AAEB

@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ከሚገኙ ተፈታኞች መካከል ጎልማሳ የኃይማኖት አባቶች እና የኃይማኖት መምህራን ይገኙበታል፡፡

@tikvahuniversity
#National_Exam

ላለፉት ሦስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያው ዙር አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከረቡዕ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በወረቀት እና በኦንላይን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

የፈተናው መጠናቀቅን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

ሁለተኛው ዙር ፈተና ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
M-PESA Safaricom appን ካለንበት ከተማ የፈጠነ እያወረድን፣ በነፃው የ 500 ሜ.ባ. ኢንተርኔት ፓኬጅ እንፍታታ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👇
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለአገልግሎታችን ለማንኛውም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
2024/10/05 20:03:11
Back to Top
HTML Embed Code: