Telegram Web Link
#National_Exam

አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የመጀመሪያ ቀን ፈተናዎች ተሰጥተዋል፡፡

በጠዋቱ መርሐግብር የእንግሊዝኛ ፈተና የተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት ተፈታኞች የሒሳብ ትምህርት ፈተና ወስደዋል፡፡

ፈተናዎቹ በወረቀት እንዲሁም በኦንላይን ሲሰጡ መዋላቸውን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተመልክቷል።

የመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
ለመማር ዕድሜ ያልበገራቸው እናት

የ54 ዓመቷ ወ/ሮ አዲስ ተስፋዬ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናቸውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዋ ወ/ሮ አዲስ፤ ከገቢ ረሱ ዞን-አዋሽ አርባ ከተማ አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት ነው ወደ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የሔዱት።

የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና የመንግሥት ሰራተኛ የሆኑት ወ/ሮ አዲስ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናቸውን በሠመራ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ነው።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በደህንነት ካሜራ (CCTV) በመታገዝ እየሰጡ ይገኛሉ።

@tikvahuniversity
የተማሪ ወ/ሮ አታለለች ተመሳሌትነት

ተማሪ ወ/ሮ አታለለች አብርሃም የ11 ልጆች እናት ናቸው። ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ እንደሚሆን ይናገራሉ፡፡ 70 የልጅ ልጆችን እንዲሁም 13 የልጅ ልጅ ልጅ አይተዋል፡፡

ከአብራካቸው የተገኙትን 11 ልጆቻቸውን አስተምረው በልዩ ልዩ ሙያዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስመርቀው በስራ ዓለም እንዲሰማሩ አድርገዋል፡፡

ተማሪ ወ/ሮ አታለለች የወለዷቸውን ልጆች ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ድረስ በማስተማር ታላቅ የእናትነት ሚናቸውን ተወጥተዋል።

ተማሪ ወ/ሮ አታለለች ትውልዳቸው በሲዳማ ክልል ምስራቅ ሲዳማ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ ሲሆን በአሁን ወቅት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡

ትምህርታቸውን ካቋረጡ ከበርካታ ዓመታት በኋላ በ2012 ዓ.ም ካቆሙበት በመጀመር ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ በቅተዋል።

ተማሪ ወ/ሮ አታለለች ትናንት የተጀመረውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በመፈተን ላይ ይገኛሉ። #HawassaUniversity

@tikvahuniversity
"በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች ሌላ ዙር ፈተና ይዘጋጃል።" - ትምህርት ሚኒስቴር

በፀጥታ ችግር ምክንያት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች ሌላ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በመገኘት በሰጡት ማብራሪያ እንደገለፁ፥ የማካካሻ ትምህርት በመስጠት ከተቻለ በ2016 ዓ.ም መጨረሻ ካልሆነም በቀጣዩ የትምህርት ዘመን መጀመሪያ ሌላ ዙር ፈተና እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ድብልቅ በሆነ መልኩ በወረቀት እና በኦንላይን እየተሰጠ መሆኑንጨያነሱት ሚኒስትሩ፤ በቀጣይ መሰረተ ልማቶችን በማሟላትና የኢንተርኔት መቆራረጥ ችግርን በመፍታት የኦንላይን ፈተናው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity
#National_Exam

አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሁለተኛ ቀን ፈተናዎች ዛሬ ይሰጣሉ፡፡

በጠዋቱ መርሐግብር የስኮላስቲክ አፕቲትዩድ ፈተና የሚሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት የጂኦግራፊ ትምህርት ፈተና ይሰጣል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና እስከ ነገ ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ምስል፦ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
2024/10/05 22:50:33
Back to Top
HTML Embed Code: