Telegram Web Link
የኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ቡድን በሞሮኮ በተካሔደው የሁዋዌ 'ቴክፎርጉድ' ክፍለ አህጉራዊ ውድድር አንደኛ በመሆን አሸነፈ።

የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር / Huawie Seeds for the Future 2024 የቴክኖሎጂ ስልጠና መርሐግብር በሞሮኮ ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 2/2016 ዓ.ም ተካሒዷል። በስልጠናው ከምስራቅ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ የተውጣጡ 17 አገራት ተሳትፈዋል።

ከስምንት ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 10 ተማሪዎች ኢትዮጵያን በመወከል በስልጠናው የተሳተፉ ሲሆን፤ ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል አምስት ተማሪዎችን የያዘው የኢትዮጵያ ቡድን በሁዋዌ 'ቴክፎርጉድ' ክፍለ አህጉራዊ ውድድር አንደኛ በመሆን አሸንፏል፡፡ የሞሮኮ ቡድን ደግሞ በሁለተኝነት አጠናቋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ቡድኖች በ 2025 ለሚካሔድው ዓለም አቀፍ ፍፃሜ ወደ ቻይና እንደሚያቀኑ ሁዋዌ ኢትዮጵያ ያደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡

የኢትዮጵያ ቡድን እንዲያሸንፍ ያስቻለው ፕሮጀክት “EarlyVet” የተሰኘ ሲሆን፤ የእንስሳት በሽታዎችን አስቀድሞ ለማወቅ የሚረዳ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በሚጠቀም ቴክኖሎጂ ላይ ያተኩራል።

@tikvahuniversity
#Update

አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና #በድጋሜ የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች ውጤት ይፋ ተደርጓል፡፡

በድጋሜ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ትምህርታቸውን ለተከታተሉባቸው ተቋማት መላኩን በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ አረጋግጠዋል።

በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ካስፈተኑ 122 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተጨማሪ፣ የ 95 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች የመውጫ ፈተናውን #በድጋሜ እንደወሰዱ ነው ኃላፊው የገለፁት፡፡

የእነዚህ በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት ሲማሩበት ወደነበረው ተቋም መላኩን ገልፀዋል፡፡ ተፈታኞቹ ወደእዛ በመሔድ ማየት ይችላሉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም https://result.ethernet.edu.et/ ላይ በመግባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት ከሳምንት በፊት መለቀቁ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤትን ይፋ አድርጓል።

ተፈታኞች ውጤታቸውን በተከታዩ ሊንክ ማየት ይችላሉ፦ harari6.ministry.et

(ወደሊንኩ ለመግባት በመጀመሪያ የስልክዎን VPN ማጥፋት ይኖርብዎታል።)

በሀረሪ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 17-19/2016 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#National_Exam

አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የመጀመሪያ ቀን ፈተናዎች ተሰጥተዋል፡፡

በጠዋቱ መርሐግብር የእንግሊዝኛ ፈተና የተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት ተፈታኞች የሒሳብ ትምህርት ፈተና ወስደዋል፡፡

ፈተናዎቹ በወረቀት እንዲሁም በኦንላይን ሲሰጡ መዋላቸውን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተመልክቷል።

የመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
ለመማር ዕድሜ ያልበገራቸው እናት

የ54 ዓመቷ ወ/ሮ አዲስ ተስፋዬ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናቸውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዋ ወ/ሮ አዲስ፤ ከገቢ ረሱ ዞን-አዋሽ አርባ ከተማ አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት ነው ወደ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የሔዱት።

የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና የመንግሥት ሰራተኛ የሆኑት ወ/ሮ አዲስ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናቸውን በሠመራ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ነው።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በደህንነት ካሜራ (CCTV) በመታገዝ እየሰጡ ይገኛሉ።

@tikvahuniversity
2024/10/06 06:30:46
Back to Top
HTML Embed Code: