#National_Exam
አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል፡፡
በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ፈተና በጠዋቱ መርሐግብር የእንግሊዝኛ ፈተና እየተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት የሒሳብ ትምህርት ፈተና ይሰጣል፡፡
የመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።
@tikvahuniversity

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መሰጠት ጀምሯል፡፡
ሀገር አቀፍ ፈተናው በመዲናዋ በወረቀት እና በኦላይን በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች፦
➭ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ፣ 5 ኪሎ፣ 4 ኪሎ እና ኤፍቢኢ ግቢዎች)
➭ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
➭ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
➭ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
➭ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት
➭ አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት
➭ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ

በታጣቂዎች ከታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 138ቱ ያህል መለቀቃቸው ተሰማ፡፡
በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ እያሉ፣ ከአዲስ አበባ 155 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ገርበ ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል ከተባሉት ተማሪዎች መካከል 138ቱ መለቀቃቸው ተሰምቷል፡፡
138 ተማሪዎች ከአጋቾች የተለቀቁት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ዘመቻ ሲሆን፣ 18 ተማሪዎች አሁንም በታጣቂዎች ታግተው እንደሚገኙ ሪፖርተር ጋዜጣ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
ኢሰመኮ ስለታገቱት ተማሪዎች መረጃና አኃዝ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ማግኘቱንና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡
በሦስት አገር አቋራጭ አውቶቡሶች ውስጥ ተማሪዎችና ሌሎች መንገደኞች እንደነበሩ፣ ታጣቂዎቹ ተማሪዎቹን ከሌሎች መንገደኞች በመለየት እንዳገቷቸው የኢሰመኮ መረጃ ይጠቁማል፡፡
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በጉዞ ላይ እያሉ በተማሪዎቹ ላይ ተፈጠረ ስለተባለው ጉዳይ መረጃ እንደሌለውና ስለዕገታው ከማኅበራዊ ሚዲያ የሰማውን መረጃ ለበላይ አካላት ሪፖርት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ሪፖርተር የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ የጠየቀ ሲሆን፤ ቢሮው ተፈጸመ ስለተባው የዕገታ ወንጀል የደረሰው ሪፖርትም ሆነ መረጃ አለመኖሩን በመግለጽ፣ ድርጊቱ መፈጸሙን እንደማያውቅ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ #ሪፖርተር

የኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ቡድን በሞሮኮ በተካሔደው የሁዋዌ 'ቴክፎርጉድ' ክፍለ አህጉራዊ ውድድር አንደኛ በመሆን አሸነፈ።
የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር / Huawie Seeds for the Future 2024 የቴክኖሎጂ ስልጠና መርሐግብር በሞሮኮ ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 2/2016 ዓ.ም ተካሒዷል። በስልጠናው ከምስራቅ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ የተውጣጡ 17 አገራት ተሳትፈዋል።
ከስምንት ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 10 ተማሪዎች ኢትዮጵያን በመወከል በስልጠናው የተሳተፉ ሲሆን፤ ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል አምስት ተማሪዎችን የያዘው የኢትዮጵያ ቡድን በሁዋዌ 'ቴክፎርጉድ' ክፍለ አህጉራዊ ውድድር አንደኛ በመሆን አሸንፏል፡፡ የሞሮኮ ቡድን ደግሞ በሁለተኝነት አጠናቋል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ቡድኖች በ 2025 ለሚካሔድው ዓለም አቀፍ ፍፃሜ ወደ ቻይና እንደሚያቀኑ ሁዋዌ ኢትዮጵያ ያደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡
የኢትዮጵያ ቡድን እንዲያሸንፍ ያስቻለው ፕሮጀክት “EarlyVet” የተሰኘ ሲሆን፤ የእንስሳት በሽታዎችን አስቀድሞ ለማወቅ የሚረዳ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በሚጠቀም ቴክኖሎጂ ላይ ያተኩራል።

#Update
አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና #በድጋሜ የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች ውጤት ይፋ ተደርጓል፡፡
በድጋሜ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ትምህርታቸውን ለተከታተሉባቸው ተቋማት መላኩን በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ አረጋግጠዋል።
በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ካስፈተኑ 122 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተጨማሪ፣ የ 95 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች የመውጫ ፈተናውን #በድጋሜ እንደወሰዱ ነው ኃላፊው የገለፁት፡፡
የእነዚህ በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት ሲማሩበት ወደነበረው ተቋም መላኩን ገልፀዋል፡፡ ተፈታኞቹ ወደእዛ በመሔድ ማየት ይችላሉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም https://result.ethernet.edu.et/ ላይ በመግባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡
የመውጫ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት ከሳምንት በፊት መለቀቁ ይታወቃል፡፡

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤትን ይፋ አድርጓል።
ተፈታኞች ውጤታቸውን በተከታዩ ሊንክ ማየት ይችላሉ፦ harari6.ministry.et
(ወደሊንኩ ለመግባት በመጀመሪያ የስልክዎን VPN ማጥፋት ይኖርብዎታል።)
በሀረሪ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 17-19/2016 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወሳል።
@tikvahuniversity
ተፈታኞች ውጤታቸውን በተከታዩ ሊንክ ማየት ይችላሉ፦ harari6.ministry.et
(ወደሊንኩ ለመግባት በመጀመሪያ የስልክዎን VPN ማጥፋት ይኖርብዎታል።)
በሀረሪ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 17-19/2016 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወሳል።
@tikvahuniversity
#National_Exam
አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የመጀመሪያ ቀን ፈተናዎች ተሰጥተዋል፡፡
በጠዋቱ መርሐግብር የእንግሊዝኛ ፈተና የተሰጠ ሲሆን፤ ከሰዓት ተፈታኞች የሒሳብ ትምህርት ፈተና ወስደዋል፡፡
ፈተናዎቹ በወረቀት እንዲሁም በኦንላይን ሲሰጡ መዋላቸውን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተመልክቷል።