Telegram Web Link
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 15-16/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት የሚጀምረው፦
ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም

የአዲስ የ PGDT ሰልጣኞች ምዝገባ እስከ ሐምሌ 14/2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 15-16/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ትምህርቱ እስከ መስከረም 10/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
42A+ ያሳካው የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ

ደሴ ላንቲደር ይባላል፡፡ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ምጣኔ ሃብት ትምህርት ክፍል ትምህርቱን ተከታትሎ አጠናቋል፡፡ ተማሪ ደሴ እጅግ ከፍተኛ ውጤት 3.99 CGPA እና 42A+ በማምጣት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የዋንጫ እና የላፕቶፕ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ ተማሪ ጥሩወርቅ አታሎ ከአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ከጠቅላላ ሴት ተመራቂ ተማሪዎች ከፍተኛ ሆነውን 3.95 CGPA ውጤት በማምጣት የወርቅ የአንገት ሀብል ሽልማት ተበርክቶላታል።

በሌላ መረጃ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልና የቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ዳኛቸው መሀሪ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት በሜዳሊያ ለተመረቁ ሴት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በቋሚነት የሥራ ዕድል ለመፍጠር ቃል ተገብቶላቸዋል።

ጂንካ ዩኒቨርስቲ ትናንት ሰኔ 27/2016 ዓ.ም 4ኛ ዙር የተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ስርዓት ያካሔደ ሲሆን፤ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 871 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

@tikvahuniversity
#AAU_Commencement

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ስርዓት ነገ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ያካሒዳል።


አጠቃላይ ተመራቂዎች - 5,911
በሦስተኛ ዲግሪ - 337
በሁለተኛ ዲግሪ - 2,837
በቅድመ ምረቃ - 2,737

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዳማ ከተማና አካባቢዋ ለሚገኙ ተማሪዎች ነፃ የክረምት ስልጠና አዘጋጅቷል።

የዩኒቨርሲቲው STEM ማዕከል ከአዳማ ት/ቤቶች ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን አወዳድር ማሰልጠን ይፈልጋል።

ዘንድሮ ከ 7-11ኛ ክፍል ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች እስከ ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም በኦንላይን ብቻ መመዝገብ እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ስልጠናው በተቋሙ STEM ማዕከል ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡

ምዝገባው የሚያበቃው 👇
ሐምሌ 05/2016 ዓ.ም

ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ 👇
https://shorturl.at/aYXAj

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ፈተናው በኦንላይን እንደማይሰጥ የሚገልፁ መረጃዎች "በፍፁም ከእውነት የራቀ ሐሰተኛ" መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ማምሻውን በተቋሙ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆች ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።

በመሆኑም ተማሪዎች ይሄንን ተገንዝበው ዝግጅት ማድረግ እንዲቀጥሉ መክሯል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።

"የኦንላይን ፈተናው ቀርቷል" የሚሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወሩ መረጃዎችን አስመልክተን የጠየቅናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "መረጃዎቹ ሐሰተኛ ናቸው" በማለት መልሰዋል።

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አረጋገጠ።

በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ፈተናው በኦንላይን እንደማይሰጥ የሚገልፁ መረጃዎች "ሐሰተኛ" ናቸው ያለው አገልግሎቱ፤ ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎች ይሄንን ተገንዝበው ዝግጅት ያድርጉ ብሏል።

@tikvahuniversity
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦንላይንም በወረቀትም እንደሚሰጥ የሚገልጸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ አጋርቷል።

' የኦንላይን ፈተናው ቀርቷል ፣ አልቀረም ' ብሎ ውሳኔ የሚሰጠው ማዕከላዊው ትምህርት ሚኒስቴር ብቻ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር አስረግጦ በተደጋጋሚ የኦንላይን ፈተና እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ተማሪዎች ተረጋግታችሁ ለፈተናው ተዘጋጁ።

ተማሪዎችን ውዝግብ ውስጥ የከተተው ምንድነው ?

ባለፉት ቀናት በተለይ አዲስ አበባ በተሰጠው የሙከራ ፈተና ወቅት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ሲስቱም አስቸጋሪ ነበር።

ወላጆችም ሲስተሙ ካስቸገረ " ልጆቻቸው ዩኒቨርሲቲ ገብተው ይፈተናሉ " ተብሎ ከት/ቤት እንደተነገራቸው ለቲክቫህ ተናግረዋል።

በኃላ ግን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ሲስተሙ ተስተካክሎ ዛሬ በተሳካ ሁኔታ የሙከራ ፈተና መፈተናቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ ሁሉም ሳይሆኑ አንዳንድ  ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " ፈተናው በኦንላይን አይሰጥም " በማለት ኮምፒዩተር እንደመለሱላቸው ተማሪዎች ተናግረዋል።

ይህ ግን በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በወረደ ትዕዛዝ እንዳልነበር እራሱ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ ላይ መመልከት ይቻላል።

ለሁሉም ግን ውሳኔ የሚሰጠው ትምህርት ሚኒስቴር ብቻ ነው።

ተማሪዎች ይህን ሀገራዊ የተማሪዎች ጉዳይ መረጃ መከታተል ያለባችሁ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ መሆን አለበት።

ፈተናው መቅረቱን፣ በሌላ መንገድ እንደሚሰጥ ወይም በኦንላይን እንደሚሰጥ የሚያሳውቀው ትምህርት ሚኒስቴር ብቻና ብቻ ነው።

ሚኒስቴሩ " የኦንላይ ፈተና ቀርቷል " የሚለው ሀሰት እንደሆነ በማስገንዘብ ተፈታኞች ለኦንላይን ፈተናው እንዲዘጋጁ አሳስቧል።

ተማሪዎች ተረጋግታችሁ የትምህርት ሚኒስቴርን መመሪያ እና ውሳኔዎች ተከተሉ። አትረበሹ !

@tikvahuniversity
#2024_Commencement

12 የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ያስመርቃሉ፡፡

ዛሬ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የትኞቹ ናቸው?

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
መቱ ዩኒቨርሲቲ
➭  ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ
  ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
  ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
አርሲ ዩኒቨርሲቲ
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት

@tikvahuniversity
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ስርዓትን በሚሌኒየም አዳራሽ በማካሔድ ላይ ይገኛል።

አጠቃላይ ተመራቂዎች - 5,911
በሦስተኛ ዲግሪ - 337
በሁለተኛ ዲግሪ - 2,837
በቅድመ ምረቃ - 2,737

@tikvahuniversity
#ECSU

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,269 ተማሪዎች አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም ብቻ 79 ችግር ፈቺና የፖሊሲ ግብዓት መሆን የሚችሉ ጥናትና ምርምሮችን ማከናወኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ፍቅሬ ደሳለኝ ገልፀዋል።

አጠቃላይ ተመራቂዎች - 2,269
በሦስተኛ ዲግሪ - 27
በሁለተኛ ዲግሪ - 2,120
በቅድመ ምረቃ - 122

@tikvahuniversity
2024/10/06 10:36:03
Back to Top
HTML Embed Code: