Telegram Web Link
አምቦ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በዕለቱ የህክምና ዶክተሮች፣ የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ እንዲሁም የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች እንደሚመረቁ ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር እስከ ነሐሴ ወር ድረስ 18.8 ሚሊዮን የመማሪያ መጻሕፍት ወደ አገር ውስጥ በማስገባት፣ ለመጪው የትምህርት ዘመን ለክልሎች ለማሠራጨት ዕቅድ መያዙን አስታወቀ፡፡

እስካሁን 20.7 ሚሊዮን የሁለተኛ ደረጃ የመማሪያ መጻሕፍት ታትመው አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ለክልሎች መሠራጨታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር የመማር ማስተማር ቁጥጥርና ሥርጭት ባለሙያ ዘሪሁን አሰግድ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተከሰተውን የመማሪያ መጻሕፍት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ወጥቶ የነበረውን ጨረታ ባሸነፈው የጃፓን ኩባንያ አማካይነት ኅትመቱ እየተከናወነ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በገጠመው የበጀት ችግር ምክንያት የመማሪያ መጻሕፍት ኅትመት በሁለት ዙሮች መደረጉንና እስከ መጪው ነሐሴ ወር ድረስ ቀሪ 18.8 ሚሊዮን የመማሪያ መጻሕፍት እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከዚህ በፊት ለሦስት ተማሪ አንድ መጻሕፍት ይዳረስ የነበረውን አሠራር፣ ለአንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ እንዲዳረስ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በሀረሪ ክልል ሲሰጥ የነበረው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ተጠናቋል።

5 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል።

ክልል አቀፍ ፈተናው በ29 የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰጥቶ በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሙያ ፍቃድና ምዘና ዳይሬክተር ዙኸራ ሙክታር ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በዕለቱ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች እንደሚመረቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#ExitExam

ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የመውጫ ፈተናው በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች በ51 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል።

ለፈተናው ከተመዘገቡት 169,790 ተማሪዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈተኑ 117,192 ተማሪዎች እንዲሁም 52,598 ተማሪዎች ደግሞ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት የጥራትና ብቃት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ገልፀዋል።

የመውጫ ፈተና ውጤት በቅርቡ እንደሚለቀቅ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ?

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተናቸውን ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ማጠናቀቃቸው ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ትናንት ሰኔ 19/2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡

የፈተናዎቹ ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ኃላፊው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች የፊታችን እሑድ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የገፅ-ለገፅ እና የኦንላይን ትምህርትን ያጣመረ የመማር ማስተማር ስርዓት ለመተግበር የፖሊሲ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከፊንላንድ ሴንትሪያ እና ጃመክ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት በተመረጡ ስድስት ክልሎች በሚገኙ 15 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የትምህርት አሰጣጡን ማዘመን የሚያስችሉ የሙከራ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል፡፡

በቀጣይ ሦስት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ የገፅ-ለገፅ እና የኦንላይን ትምህርትን ያጣመረ የመማር ማስተማር ስርዓት ገቢራዊ ለማድረግ የፖሊሲ ዝግጅት እየተከናወነ እንደሚገኝ በተከናወኑ ተግባራት ላይ በተዘጋጀ መድረክ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታው ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በመላ አገሪቱ ከ1,500 በላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መኖራቸው በመድረኩ ተጠቁሟል። #ኢዜአ

@tikvahuniversity
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሰኔ 25 እና 26/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

የተማሪዎች የምርቃት መርሐግብር ሰኔ 25/2016 ዓ.ም በነቀምቴ ካምፓስ እንዲሁም ሰኔ 26/2016 ዓ.ም በጊምቢ እና በሻምቡ ካምፓሶች እንደሚካሔድ ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#TVTI_Exit_Exam

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተና ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

በኦንላይን ከሚሰጠው ፈተና አስቀድሞ፣ ነገ ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ሞዴል የመውጫ ፈተና ለተፈታኞች እንደሚሰጥ ኢኒስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የመውጫ ፈተና በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም መስጠቱ አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
#AksumUniversity
#MaddaWalabuUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እሑድ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በተመሳሳይ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እሑድ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "ስማርት ካምፓስ ፕሮጀክት" ለመተግበር የሚያስችለውን ስምምነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስማርት መማሪያ ክፍሎች እና የተለያዩ ዘመናዊ አሰራሮችን ለማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ስምምነቱ የትምህርት መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት፣ የቤተ-ሙከራ ፍተሻዎችን በተሻለ ተሞክሮ ለማከናወን፣ የምዘና ፈተናዎችን ለመስጠት የሚያስችል ስማርት የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት እንደሚያካትትም ተገልጿል።

የስድስት ኪሎ ግቢ የመግቢያ በሮች፣ ዋና ዋና የአስተዳደር ህንጻዎችን፣ ሙዚየሙንና ሌሎች ስፍራዎች ላይ የሲሲቲቪ ካሜራ መግጠምና ተዛማጅ የመሰረተ ልማት ግንባታ የሚያካትት መሆኑም ተጠቁሟል።

ስምምነቱ የጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ስፔሻላይድ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም የሚያስችል መሆኑም ተሰምቷል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

ትናንት የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና "የቴክኒክ ችግር" አጋጥሞት እንደነበር ትምህርት ሚኒስቴር አረጋገጠ።

ስለሆነም ፈተናውን በድጋሜ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ፈተናው በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ እና ከሰአት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል ተብሏል።

ለፈተናው ተቀምጣችሁ የነበራችሁ የፋርማሲ ተማሪዎች በየተፈተናችሁበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንድትወስዱ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@tikvahuniversity
በፀጥታ ችግር ምክንያት በአማራ ክልል በ2016 የትመህርት ዘመን ከ2.6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መራቃቸውን መንግሥት ገለፀ፡፡

በክልሉ በተካሔደ የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ላይ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) እንደገለፁት፣ እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ከ3 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶችም ዝግ ሆነው ቆይተዋል፡፡

ትምህርት በጀመሩ ተማሪዎች እና መምህራን ላይም ከፍተኛ ጫናና መዋከብ እንደደረሰ ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡

በርካታ በክልሉ ገጠራማ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት በመቆሙ ወደ ትዳር እየገቡ እንደሆነ ከክልሉ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በቅርቡ የተሰጡትን የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናዎች የፀጥታ ችግር ባለባቸው የክልሉ አካባቢዎች በተለይም በምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች አለመሰጠታቸው ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
2024/09/29 01:21:52
Back to Top
HTML Embed Code: