Telegram Web Link
#MekelleUniversity

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትናንት የተሰጡት የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ እና የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የመውጫ ፈተናዎች ከተዘጋጀው ብሉ ሪንት ውጪ በመሆናቸው ፈተናዎቹ በድጋሜ እንዲሰጡ ተፈታኞቹ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ተወካይ በጉዳዩ ላይ ከተቋሙ አመራሮች ጋር የተወያየ ሲሆን፤ ፈተናዎቹ ከብሉ ፕሪንት ውጪ እንደተዘጋጁ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል፡፡ ይሁን እንጂ ፈተናው በድጋሜ ዛሬ ከሰዓት እንደሚሰጥ ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በተመሳሳይ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም የተሰጠው የ Management የመውጫ ፈተና በተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት መሰረት የተዘጋጀ እንዳልነበር በርካታ ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
#AddisAbabaUniversity

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 29/2016 ዓ.ም በሚሌኒየም አዳራሽ ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
#EducationDiplomacy

መንግሥት የትምህርት ዲፕሎማሲን በማጠናከር
በ2016 ዓ.ም ለ865 የጎረቤት አገራት ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጥቷል።

እነዚህ ተማሪዎች በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

ነጻ የትምህርት ዕድል ካገኙት መካከል የደቡብ ሱዳን፣ የሶማሊላንድ እና የጅቡቲ ተማሪዎች ይገኙበታል።

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
አምቦ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በዕለቱ የህክምና ዶክተሮች፣ የመጀመሪያ፣ የሁለተኛ እንዲሁም የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች እንደሚመረቁ ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር እስከ ነሐሴ ወር ድረስ 18.8 ሚሊዮን የመማሪያ መጻሕፍት ወደ አገር ውስጥ በማስገባት፣ ለመጪው የትምህርት ዘመን ለክልሎች ለማሠራጨት ዕቅድ መያዙን አስታወቀ፡፡

እስካሁን 20.7 ሚሊዮን የሁለተኛ ደረጃ የመማሪያ መጻሕፍት ታትመው አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ለክልሎች መሠራጨታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር የመማር ማስተማር ቁጥጥርና ሥርጭት ባለሙያ ዘሪሁን አሰግድ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተከሰተውን የመማሪያ መጻሕፍት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ወጥቶ የነበረውን ጨረታ ባሸነፈው የጃፓን ኩባንያ አማካይነት ኅትመቱ እየተከናወነ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በገጠመው የበጀት ችግር ምክንያት የመማሪያ መጻሕፍት ኅትመት በሁለት ዙሮች መደረጉንና እስከ መጪው ነሐሴ ወር ድረስ ቀሪ 18.8 ሚሊዮን የመማሪያ መጻሕፍት እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከዚህ በፊት ለሦስት ተማሪ አንድ መጻሕፍት ይዳረስ የነበረውን አሠራር፣ ለአንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ እንዲዳረስ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በሀረሪ ክልል ሲሰጥ የነበረው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ተጠናቋል።

5 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል።

ክልል አቀፍ ፈተናው በ29 የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰጥቶ በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የሙያ ፍቃድና ምዘና ዳይሬክተር ዙኸራ ሙክታር ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በዕለቱ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች እንደሚመረቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#ExitExam

ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የመውጫ ፈተናው በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች በ51 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል።

ለፈተናው ከተመዘገቡት 169,790 ተማሪዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈተኑ 117,192 ተማሪዎች እንዲሁም 52,598 ተማሪዎች ደግሞ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት የጥራትና ብቃት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ገልፀዋል።

የመውጫ ፈተና ውጤት በቅርቡ እንደሚለቀቅ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ?

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተናቸውን ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ማጠናቀቃቸው ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ትናንት ሰኔ 19/2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡

የፈተናዎቹ ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ኃላፊው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች የፊታችን እሑድ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የገፅ-ለገፅ እና የኦንላይን ትምህርትን ያጣመረ የመማር ማስተማር ስርዓት ለመተግበር የፖሊሲ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከፊንላንድ ሴንትሪያ እና ጃመክ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት በተመረጡ ስድስት ክልሎች በሚገኙ 15 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የትምህርት አሰጣጡን ማዘመን የሚያስችሉ የሙከራ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል፡፡

በቀጣይ ሦስት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ የገፅ-ለገፅ እና የኦንላይን ትምህርትን ያጣመረ የመማር ማስተማር ስርዓት ገቢራዊ ለማድረግ የፖሊሲ ዝግጅት እየተከናወነ እንደሚገኝ በተከናወኑ ተግባራት ላይ በተዘጋጀ መድረክ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታው ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በመላ አገሪቱ ከ1,500 በላይ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መኖራቸው በመድረኩ ተጠቁሟል። #ኢዜአ

@tikvahuniversity
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሰኔ 25 እና 26/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

የተማሪዎች የምርቃት መርሐግብር ሰኔ 25/2016 ዓ.ም በነቀምቴ ካምፓስ እንዲሁም ሰኔ 26/2016 ዓ.ም በጊምቢ እና በሻምቡ ካምፓሶች እንደሚካሔድ ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#TVTI_Exit_Exam

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተና ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

በኦንላይን ከሚሰጠው ፈተና አስቀድሞ፣ ነገ ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ሞዴል የመውጫ ፈተና ለተፈታኞች እንደሚሰጥ ኢኒስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የመውጫ ፈተና በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም መስጠቱ አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
#AksumUniversity
#MaddaWalabuUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እሑድ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

በተመሳሳይ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እሑድ ሰኔ 23/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
2024/09/29 21:29:47
Back to Top
HTML Embed Code: