Telegram Web Link
#EthiopianAviationUniversity

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የአቪዬሽን የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 800 የሚጠጉ ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በአውሮፕላን አብራሪነት፣ በበረራ መስተንግዶ፣ በማርኬቲንግ እና በአውሮፕላን ጥገና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 787 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከስምንት የአፍሪካ አገራት እና ከአንድ የኤስያ ሀገር የተውጣጡ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ካሴ ይማም ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
#SummerVoluntaryService

20 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ይሳተፋሉ።

የዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ሰላም ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ይካሔዳል።

በንቅናቄው ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ39 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሏል።

በዘንድሮው መርሐግብር በ14 መስኮች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚሰጡ ሲሆን፤ ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ነው የተገለፀው።

የአረንጓዴ አሻራ፣ ትምህርት እና የጤና አገልግሎት ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል ይገኙበታል ተብሏል።

20 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተለያዩ አካባቢዎች በበጎፈቃድ አገልግሎቱ እንደሚሳተፉ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ ተናግረዋል።

ንቅናቄው ረዕቡ ሰኔ 12/2016 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ይጀመራል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ በ2017 የትምህርት ዘመን በተለያዩ ምክንያቶች ምዝገባ እንዳያካሒዱ ዕገዳ የተጣለባቸው 35 ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ በ2017 የትምህርት ዘመን በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸው 41 ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የሚገኙ 35 ትምህርት ቤቶች ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንዳያካሒዱ ዕገዳ ተጣለባቸው።

በከተማዋ የሚገኙ 35 የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንዳያካሒዱ ማገዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሳውቋል።

ትምህርት ቤቶቹ በዋናነት በትምህርት ፖሊሲ ጥሰት፣ በትምህርት ስታንዳርዱ መሰረት ከ75 በመቶ በታች ያመጡ እንዲሁም የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን በአግባቡ አለመጠቀም የታየባቸው በመሆኑ ዕግዱ እንደተጣለባቸው ባለስልጣኑ ገልጿል።

ዕግዱ ከተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል የጊብሰን ትምህርት ቤቶች፣ የቅዱስ ሚካኤል አምስት ትምህርት ቤቶች እና የካ አፖሎ ትምህርት ቤት እንደሚገኙበት የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዳኛው ገብሩ ተናግረዋል።

ዕገዳ በተጣለባቸው ትምህርት ቤቶች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በመኖረያ አቅሪያቢያቸው በሚገኙ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ እንዲስተናግዱ ይደረጋል ብለዋል።

ሌሎች 41 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው መሰረዙን የገለፁት ኃላፊው፤ የ150 ትምህርት ቤቶች ጉዳይ በሒደት ላይ እንደሆነና ወደፊት እንደሚገለፅ ተናግረዋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ተማሪዎችን መዝግበው እንዲያስተምሩ ፈቃድ የተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች 1,332 መሆናቸውን ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity
2024/09/29 05:28:56
Back to Top
HTML Embed Code: