Telegram Web Link
ለሁለት ቀናት በአማራ ክልል ሲሰጥ የቆየው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ።

በክልሉ ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም የተሰጠው የ8ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የቢሮው ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።

ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ ኃላፊዋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአማራ ክልል ዘንድሮ 184,393 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበው እንደነበር ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

በክልሉ በቀጠለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከ180 ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና አለመቀመጣቸው ይታወቃል፡፡

ሰኔ 13 እና 14/2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሰጣል።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የ2016 ዓ.ም ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መጠናቀቁ ተገለጸ።

ፈተናው በከተማዋ በሚገኙ 182 የፈተና ጣቢያዎች ለሁለት ቀናት ተሰጥቶ በሰላም መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል 99 በመቶ የሚሆኑት መፈተናቸውን በቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ተናግረዋል።

ፈተናው በአማርኛ ስርዓተ ትምህርት ለተማሩ ተማሪዎች በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሁም የአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ተማሪዎች በስምንት የትምህርት አይነቶች መሰጠቱን ገልፀዋል።

የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም በመዲናዋ ይሰጣል።

@tikvahuniversity
#AddisAbabaUniversity
#FacultyPromotions

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ በተቋሙ ሴኔት ተገምግሞ የቀረቡለትን የ12 ምሁራን የማዕረግ ዕድገት አፅድቋል፡፡

ምሁራኑ በማስተማር ውጤታማነት፣ ባሳተሟቸው ጥናታዊ ፅሁፎች፣ ለማህበረሰብ ያበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎት እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የነበራቸው የተቋም አስተዳደር ተገምግሞ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።

በዚህም፦

1. ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል - በሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ
2. ፕሮፌሰር አንተነህ በለጠ - በፍርማሴዩቲክስ
3. ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ - በፕላንት ጄኔቲክ
4. ፕሮፌሰር አህመደ ሁሴን - በአናሊቲካል ኬሚስትሪ
5. ፕሮፌሰር ታደሰ እጓለ - በማይክሮባዮሎጂ
6. ፕሮፌሰር ተክለኃይማኖት ኃ/ሥላሴ - በፕላንት ባዮቴክኖሎጂ
7. ፕሮፌሰር ተሸመ ሰንበታ - በኮንደንስድ ማተር ፊዝክስ
8. ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ - በካሪኩለም ጥናት
9. ፕሮፌሰር ሀብቴ ተኪኤ - በሜዲካል ኢንቶሞሎጂ
10. ፕሮፌሰር ቃለአብ ባዬ - በሒዩማን ኒውትሪሽን
11. ፕሮፌሰር ሰለሞን ሙሉጌታ - በአርባን ፕላኒንግ
12. ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ፍሰሀ - በፓሊኦኢንቫይሮሜንታል ጥናት

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ካገኙት መካከል ሁለቱ ሴት ምሁራን ናቸው።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ተራዝሟል!

ኢኖቬቲቭ፣ ሊተገበር የሚችል እና ተፅዕኖ የሚፈጥር የቢዝነስ ሀሳብ አለዎት? ወጣት ተማሪ ነዎት?

እንግዲያውስ የሥራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶችን የሚያበረታታው Youth Challenge Fund ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ!

መስፈርቶች፦

➧ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➧ የቅድመ ምረቃ ተማሪ ከሆኑ ዕጩ ተመራቂ መሆን ያለብዎት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የማስተርስ እና ፒ.ኤች.ዲ ትምህርትዎን እየተከታተሉ ከሆነም ማመልከት ይችላሉ፡፡

➧ ለግብርና ምርታማነት፣ ዘላቂነት እና እሴት መጨመር አስተዋፅኦ ለሚያደርግ ማንኛውም የትምህርት መስክ የምትማሩ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

እንዴት ማመልከት ይቻላል?

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆኑ [email protected] ላይ ማመልከቻዎን ይላኩ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆኑ
[email protected] ላይ ማመልከቻዎን ይላኩ።

በተጨማሪም [email protected] እና [email protected] ላይ ግልባጭ ያድርጉ፡፡

ምን ድጋፍ ይደረጋል?

አሸናፊ የቢዝነስ ሀሳቦች ከ 5,000 እስከ 20,000 ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም የቢዝነስ ኮቺንግና ክትትል እገዛ ይደረግላቸዋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
ቅዳሜ ሰኔ 8/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ "የድኅረ ምረቃ ትምህርት በኢትዮጵያ፤ መስፋፋት፣ የመግቢያ መስፈርት እና የሰልጠና ጥራት” በተሰኘ ርዕስ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

መርሐግብሩ በበላይ ሐጎስ (ዶ/ር) አቅራቢነት በፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማርያም አወያይነት ይካሔዳል።

መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ሐሙስ ሰኔ 20/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት እንደሚካሔድ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ክፍፍል

የፌደራል መንግሥት ለ2017 በጀት ዓመት ከያዘው 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ 39 ቢሊዮን ብር ያህሉ ከመንግሥት ግምጃ ቤት ወጪ ሆኖ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲከፋፈል መድቧል።

ለፓርላማ በቀረበ የበጀት ረቂቅ ሰነድ ላይ እንደሚታየው 13 ዩኒቨርሲቲዎች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦላቸዋል።

ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመንግሥት መደበኛ በጀት 1.9 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ባህርዳር ዩኒቨርስቲ 1.8 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል።

ከመንግሥት ግምጃ ቤት 1.7 ቢሊዮን ብር የሚሰጠው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በክፍፍሉ ሦስተኛውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን የሚያገኝ ይሆናል። ጅማ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በአራተኛ እና በአምስተኛነት ይከተላሉ።

የፌደራል መንግሥት በጀትን የሚያዘጋጀው የገንዘብ ሚኒስቴር፤ ባለፈው ግንቦት ወር መጀመሪያ ባካሄደው የበጀት ስሚ መርሐግብር ዩኒቨርሲቲዎች “በተቀመጠላቸው ጣሪያ መሰረት” የበጀት ዕቅዳቸውን አስተካክለው እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር አይዘነጋም። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

የሪሚዲያል ፕሮግራም የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናቸውን በኦንላይን ሲወስዱ ቆይተዋል።

በሌላ በኩል የሪሚዲያል ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ ቀን ፈተና ዛሬ በኦንላይን በተሰጠ የእንግሊዝኛ ፈተና ተጀምሯል።

@tikvahuniversity
ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ 190 ለሚሆኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ተማሪዎቹ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ስልጠናው ከሰላም ሚኒስቴር እና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ስልጠናውን ተከትሎ ተማሪዎቹ ለአንድ ወር በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚሳተፉ ይሆናል።

@tikvahuniversity
የእርዳታ ጥሪ

ይህ የ18 ዓመት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሙሉጌታ ብርሃኑ ይባላል!

የጥቁር አንበሳ የህክምና ቦርድ "የአጥንት መቅኔህ ደም ማምረት ስላቆመ ወደ ውጭ ሔደህ መታከም አለብህ" ብሎታል።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመፈተን በዝግጅት ላይ የነበረው ተማሪ ሙሉጌታ፥ አሁን ላይ በህይወት እና ሞት መካከል ይገኛል። በሚያሳዝን ሁኔታ በየቀኑ ደም ይሰጠዋል!

ብቸኛ ወንድሙ ዘካርያስ ብርሃኑ ትምህርቱን አቋርጦ ለመድኃኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ለሟሟላት እየጣረ ቢሆንም ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት የእናንተን ድጋፍ ይጠይቃል።

በህይወት ለመቆየት የሚያስፈልገው ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ስለሆነ በፀሎት እያሰባችሁት እባካችሁን ሼር በማድረግ አግዙት🙏

"ለመልካም ሥራ ረፍዶ አያውቅም!"
አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000402392607 - ዘካርያስ ብርሀኑ (ወንድም)
ስልክ ቁ. 0961237095 - ዘካርያስ
ባይሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን ፈተና ዛሬ እየተሰጠ ነው።

የተፈጥሮ ሳይንስ ሪሚዲያል ተማሪዎች የኦንላይን ፈተና ትናንት በተሰጠው የእንግሊዝኛ ፈተና መጀመሩ ይታወቃል።

"በፈተናው ወቅት የኔትወርክ መቆራረጥ እና ፈተናው በሰዓቱ ሳይጀመር በመቅረቱ ተፈታኞች በቂ ጊዜ አለማግኘታቸውን" ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልፀዋል፡፡

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ ችግሮቹ ከታየባቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

በተለይ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ከሰዓት የተሰጠው የእንግሊዝኛ ፈተና በተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ምክንያት ብዙ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ አለመቻላቸው ታውቋል፡፡

"የተፈጠረውን ችግር ትምህርት ሚኒስቴር የሚያውቀው ስለሆነ በቅርቡ ተለዋጭ የፈተና ግዜ ለተፈጥሮ ሳይንስ የእንግሊዘኛ ትምህርት እንደሚወጣ ከስምምነት መደረሱን" ከዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ሰምተናል፡፡

እሑድ ሰኔ 9/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ የነበረው የተፈጥሮ ሳይንስ ሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ወደ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም እንደተዘዋወረ መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የሦስተኛ ቀን ፈተና እየተሰጠ ነው።

ትናንት የነበረው የተፈጥሮ ሳይንስ ሪሚዲያል ተማሪዎች የኦንላይን ፈተናም የቴክኒካል ችግር አጋጥሞት እንደነበር ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል፡፡

መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የኔትወርክ መቆራረጥና ቴክኒካል ችግሮች ከታየባቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

እሑድ ሰኔ 9/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ የነበረው የተፈጥሮ ሳይንስ ሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ወደ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም መዘዋወሩ ይታወቃል።

ምስል፦ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
በርካታ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ ጥያቂያቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

ከመውጫ ፈተና ጋር የተያያዘ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የተመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር ደብዳቤ፤ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያረጋግጣል፡፡

በኦንላይን ለሦስተኛ ጊዜ የሚሰጠው የመውጫ ፈተናው፤ በድጋሜ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞችም ይሰጣል፡፡

ምስል፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል የመውጫ ፈተና

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ለመከታተል ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ሪፖርት ማድረጊያ ቦታዎች፦

➧ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በፖሊ ካምፓስ
➧ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ ዓባይ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው
➧ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ
➧ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ

@tikvahuniversity
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል ይመኛል!

እንኳን ለኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

ኢድ ሙባረክ!! Eid Mubarak!!

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ነገ መሰጠት ይቀጥላል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ዛሬ ያልተሰጠ ሲሆን፤ ፈተናው ነገ ሰኔ 10/2016 ዓ.ም መሰጠት እንደሚቀጥል ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

ሰኞ ሰኔ 10/2016 ዓ.ም የፊዚክስ ትምህርት ፈተና እንዲሁም ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ደግሞ የኬሚስትሪ ፈተና ይሰጣል።

ምስል፦ ቦረና ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
2024/09/29 11:19:53
Back to Top
HTML Embed Code: