Telegram Web Link
ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸው ስህተትን መቀነስን ጨምሮ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የበይነ መረብ ፈተና ለስህተት በር አይከፍትም

የበይነ መረብ ፈተና አንድ ጥያቄ ሳይመልሱ ወደ ፈለጉት ጥያቄ በአንድ Click የመሔድ እንዲሁም ተመልሰው መስራት የሚፈልጉትን ጥያቄ Flag በማድረግ ተመልሶ የመስራት ዕድልን ይሰጣል።

ጊዜ ቆጣቢ ነው

በአንድ Click የፈተና ጥያቄን መልስ ለመስጠት ያስችላል። እንዲሁም ምን ያህል ደቂቃ እንደተጠቀሙ ከመፈተኛ ስክሪን ላይ ማየት ስለሚቻል ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል።

የተሻሻለ የመረጃ ቋት አለው

የበይነ መረብ ፈተናዎች በቂ የፈተና መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በማከማቸት ለተፈታኞች አመጣጥኖ ያቀርባል፡፡

የተሰሩ ጥያቄዎችን መልስ በፍጥነት በራሱ ይልካል

በፈተና ወቅት ጥያቄዎቹን ሰርተው ሳያጠናቀቁ የተሰጠው ደቂቃ ካለቀ የሰሩትን በጠቅላላ በራሱ በፍጥነት ይልካል።

ፈጣን ግብረ መልስ ይሰጣል

በበይነ መረብ ፈተናዎች ሲሰጡ ውጤታቸው ከሌላው ጊዜ በተለየ ፈጥኖ የመታወቅ ዕድል ይሰጣል።

ተማሪዎች በቤታቸው እያደሩ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣል

ትምህርት ቤቶች የተደራጀ የኮምፒውተር ቤተሙከራ ካላቸውና የመፈተኛ ክላስተር ለመሆን አስፈላጊውን መስፈርቶች ማሟላታቸው ከተረጋገጠ ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ሆነው እንዲፈተኑ ዕድል ይፈጥራል። #MoE

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ የመሆን ሒደቱን ለማጠናቀቅ በቀጣይ አምስት ዓመታት 60 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ተገለፀ።

ዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት መንገዱን ከጀመረ ስምንት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ የሽግግር ሒደቱ ሁለት ዓመት ይፈጃል ተብሏል።

አሁን ላይ የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት ለሽግግር ሒደቱ ችግር እንደሆነባቸው የሽግግር ሒደቱ እስከሚጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ያሉት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን ለሚሠራቸው ሥራዎች በቀጣይ አምስት ዓመታት 60 ቢሊዮን ብር የሚያስፈልገው ሲሆን፤ ከመንግሥት እና ከተቋሙ ገቢ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 25 ቢሊዮን ሊያገኝ እንደሚችል ገልፀዋል። የ 35 ቢልዮን ብር ክፍተት ሊፈጠር እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

በተመሳሳይ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ፈተናዎቹን ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል ፈተናውን 86,671 ተማሪዎች እንዲሁም የስድስተኛ ክፍል ፈተናውን 86,217 ተማሪዎች እንደሚወስዱ በቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ከተፈቀዱ የፈተና ቁሳቁሶች ውጪ፣ ዲጂታል ሰዓትን ጨምሮ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ይዞ ወደ ፈተና መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና ጊዜን የተመለከቱ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ደርሰዋል፡፡

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የተመለከተው ጊዚያዊ የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና መርግብር፤ ፈተናው ከሰኔ 3-10/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል።

በዚህም የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 3 እስከ 6/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 6-10/2016 ዓ.ም ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል። የፕሮግራም ለውጥ የሚኖር ከሆነ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ብቻ የሚሰጥ ሲሆን፤ ተቋማቱ ስለፈተናው ገለፃ ለተፈታኞች መስጠት መጀመራቸውን ተመልክተናል።

ዘንድሮ 78 ሺህ የሪሚዲያል ተማሪዎች #ከባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ ውጪ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ከታህሳስ ወር ጀምሮ ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡

@tikvahuniversity
በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ከፍለው ለመማር የማይችሉ ተማሪዎች የባንክ ብድር እንዲያገኙ የሚረዳ ሕጋዊ አሠራር እንዲመቻች ተጠየቀ፡፡

በ2015 ዓ.ም. ፀድቆ ወደ ሥራ የገባውና ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የሚያደርገው አዋጅ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከስምንት ወራት በፊት ወደ ሥራ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ተጨማሪ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ራስ ገዝነት ለማሸጋገር ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ምንም እንኳ ተጠያቂነቱ ኖሮ በተወሰነ ደረጃ መንግሥት በገንዘብ የሚደግፋቸውም ቢሆኑም፣ ራሳቸውን በራሳቸው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የፋይናንስ፣ የአስተዳደር፣ የአካዴሚክ፣ የሰው ሃብት እና መሰል ነፃነት አዋጁ ያጎናፅፏቸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ራስ ገዝ ሆኖ ሥራ በጀመረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ከፍለው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ክፍያው በከፍተኛ መጠን እንደጨመረባቸው እየተናገሩ ነው፡፡

ወደፊት ራስ ገዝ የሚሆኑ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሥራ ሲገቡ አሁን ያለው ሁኔታ ጥሩ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ከፍለው እንዳይማሩ ይገድባል የሚል ሥጋት እየተሰማ ነው፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ለተማሪዎች የሚሰጥ ብድር መመቻቸት ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) በተመሳሳይ፤ መንግሥት በውጭው ዓለም የተለመደውን ለተማሪዎች ብድር የሚቀርብበት አሠራር ሊያስብበት ይገባል ብለዋል፡፡

ሙሉውን ያንብቡ 👇
https://www.ethiopianreporter.com/130161/

@tikvahuniversity
#Update

በሰኔ 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ ያመለከታችሁ በምዝገባ ወቅት የተላከላችሁን የቴሌ ብር የክፍያ ማረጋገጫ (Tele Birr Payment Transaction Code) በመጠቀም የመፈተኛ የይለፍ ቃል (Password) https://exam.ethernet.edu.et በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የምትፈተኑ ዕጩ ተመራቂዎች የይለፍ ቃል (Password) የምታገኙት ከምትማሩበት ተቋም ብቻ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Note:

ማንኛውም የድጋሚ (Re-exam) ተፈታኝ በምዝገባ ወቅት ያልተሟሉ መረጃዎችን በሲስተሙ በኩል ማሟላት ይጠበቅበታል። ሁሉም ተፈታኞች ወደፊት በሚገለፀው ፕሮግራም መሰረት የሞዴል ፈተናን መውሰድ ይኖርባቸዋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ዛሬ ያበቃል!

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የተዘጋጀ "ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ" ፕሮግራም (National Cyber Talent Challenge Program) የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በቻሌንጁ ላይ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፤ Cyber Security, Cyber Development, Embedded Systems, and Aerospace የታለንት መስኮች ናቸው፡፡

ምዝገባው ዛሬ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

ለመመዝገብ፦ https://talent.insa.gov.et

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ጥሪ ሊያደርግ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በፀጥታ ችግርና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ ሳያደርግ ቆይቷል።

ረቡዕ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም ውይይት ያደረገው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንዲደረግ መወሰኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከተቋሙ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

በዚህም ከሐምሌ ወር አጋማሽ ጀምሮ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በዩኒቨርሲቲው በመገኘት መከታተል ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ፣ ትምህርት ሚኒስቴር በልዩ ሁኔታ ፈተና እንደሚያዘጋጅላቸውም ታውቋል።

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች የጊዜ ሰሌዳ

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም እንዲሁም የስድስተኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በከተማዋ የስምንተኛ ክፍል ፈተናን 86,671 ተማሪዎች እንዲሁም የስድስተኛ ክፍል ፈተናን 86,217 ተማሪዎች እንደሚወስዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወሳል፡፡

(የፈተናዎቹን የጊዜ ሰሌዳ ከላይ ይመልከቱ፡፡)

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሊመረቅ ነው። ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በግንባታና ግብዓት በማሟላት ሒደት ላይ የቆየው ሆስፒታሉ፤ ሰኔ 01/2016 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መሥጠት ይጀምራል፡፡ ተቋሙ "አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል" በሚል ስያሜ እንዲጠራ መወሰኑም ታውቋል፡፡ ሆስፒታሉ 600 የህሙማን አልጋዎች…
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚመረቅበት ጊዜ ተራዝሟል፡፡

ሆስፒታሉ ነገ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም እንደሚመረቅ ዩኒቨርሲቲው ገልፆ የነበረ ቢሆንም፤ "በሌሎች ክልላዊ የሥራ ጉዳዮች ምክንያት" የምረቃው ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዲታደመ ለተጋበዙ አካላት ይቅርታ የጠየቀው ዩኒቨርሲቲው፤ በቀጣይ የሆስፒታሉ ምረቃ የሚከናወንበትን ጊዜ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ለአምስተኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች የውጪ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሰጥቷል፡፡

ለተከታታይ አራት ቀናት የተሰጠውን የህክምና ተማሪዎች የውጭ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና (External Quality Examination) 152 ተማሪዎች መውሰዳቸው ተገልጿል።

ከሀገር ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች 32 የህክምና ባለሙያዎች በተጋባዥ ፈታኝነት ተገኝተው የመመዘን ሒደቱ ተከናውኗል፡፡

የምዘና ሒደቱ በአራት የህክምና ዘርፎች ማለትም ቀዶ ጥገና፣ ውስጥ ደዌ ህክምና፣ ማህፀንና ፅንስ ህክምና እና በህፃናት ህክምና ዘርፍ መሰጠቱ ተመላክቷል።

@tikvahuniversity
#ይጠንቀቁ

ትምህርት ሚኒስቴር ከእንደዚህ አይነት ሐሰተኛ ማስታወቂያዎች ይጠንቀቁ ብሏል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የትምህርት ሚኒስቴርን ስም የሚጠቅሱና "ሰርተፊኬት የሚያሰጡ ነጻ የኦንላይን ስልጠና " የሚሉ ማስታወቂያዎች ሐሰተኛ መሆኑን አውቃችሁ ጥንቃቄ አድርጉ።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አካዳሚ በቡና ጥራት ቁጥጥር እና ቅምሻ ስልጠና በቀን እና በማት መርሐግብሮች ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል!

የማታ መርሐግብር የመጀመሪያ ባች ተማሪዎች ትምህርት ሰኔ 3/2016 ዓ.ም ይጀምራል።

ስልጠናው ከሦስት እስከ ሦስት ወር ከግማሽ ይሰጣል።

ይመዝገቡ!!

በተከታዩ ሊንክ ይመዝገቡ 👇

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe9XBw_BXSv56zYBUUjdaDypd74CUlIn4NKPci3vZswfcPbrw/viewform?usp=sf_link

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን አስመረቀ፡፡

ኮሌጁ ከፍተኛ ወጪ በማድረግ ያደራጃቸውና ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑ የተለያዩ የህክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስመርቋል።

ከተመረቁት ማዕከላት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፦

➧ የካንሰር ማዕከል ጨረራ ህክምና፣
➧ የፎረንሲክ ህክምናና የስነ-ምረዛ ማዕከል፣
➧ የህዝብ መድኃኒት ቤት፣
➧ የስነ-አዕምሮ ህክምና ማዕከል፣
➧ የጨቅላ ህጻናት ፅኑ የህክምናና ልህቀት ማዕከል።

@tikvahuniversity
በአማራ ክልል የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 4/2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል።

ፈተናዎቹን ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ፈተናዎቹ ታትመው፣ ወደሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች የማጓጓዝ ሥራ መጠናቀቁን የቢሮው ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

184,393 የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ 170,470 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኔ 13 እና 14/2016 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

ተማሪዎቹን ለፈተና ለማብቃት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን አስረድተዋል።

@tikvahuniversity
2024/09/29 13:21:14
Back to Top
HTML Embed Code: