Telegram Web Link
Tikvah-University
የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ አመራሮች ካውንስል ተመሠረተ። ካውንስሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ዘርፉን ማስተሳሰር የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ የአመራር ካውንስሉ ጥናትና ምርምር በማድረግ ልዩነት መፍጠር የሚችል የሰው ኃይል ማፍራት ኃላፊነት እንደተጣለበት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልፀዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከ2,000 በላይ የቴክኒክና…
ዛሬ ግንቦት 21/2016 ዓ.ም በይፋ የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት አመራሮች ካውንስል ሥራ አስፈፃሚ አመራሮችን መርጧል።

በዚህም መለስ ይግዛው ከጄነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት፣ ተሻለ ዱጉማ ከአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ፕሬዝዳንት እና መልካሙ ባራሳ ከሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጸሐፊ ሆነው ተመርጠዋል።

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር 3ኛ ዙር የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) ሰጥቷል።

በወረቀት የተሰጠውን የ IELTS Academic and IELTS General Training ፈተና 25 አመልካቾች መውሰዳቸው ተገልጿል።

በዩኒቨርሲቲው 4ኛ ዙር ፈተና ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን የአመልካቾች ምዝገባ ተጀምሯል።

@tikvahuniversity
#BookFair

የመጻሕፍት አውደ ርዕይ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተከፍቷል።

አውደ ርዕዩ በዩኒቨርሲቲው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ ሲሆን፤ በርካታ የመጻሕፍት አሳታሚዎች እና አከፋፋዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

አውደ ርዕዩ እስከ ቅዳሜ ግንቦት 24/2016 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

@tikvahuniversity
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የስነ-ጽሁፍ ውድድር ማካሔድ ሊጀመር ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው 'ፈኒ ዶጊሳ' የተሰኘ ዓመታዊ የስነ-ጽሁፍ ውድድር በአማርኛ እና በአፋር አፍ ቋንቋዎች ማካሔድ ሊጀምር መሆኑን አሳውቋል፡፡

በሁለት ዘርፎች ማለትም ግጥም እና መነባንብ የሚከናወነውን ውድድር፤ የተቋሙ ዶ/ር ሬዶ የባህል እና ሀገር በቀል ጥናቶች ማዕከል እንደሚያዘጋጀው ተገልጿል፡፡

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ እንዲሁም የአፋር ክልል ነዋሪዎች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦ ከግንቦት 23-25/2016 ዓ.ም

የመመዝገቢያ አማራጮች፦

የተቋሙ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሠራተኞች በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሸግግር ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች በስልክ ቁ. 0953990560 ላይ ሙሉ ስም፣ የሥራ ዘርፍና ቦታ፣ የምትወዳደሩበትን ዘርፍና ይዘት በማካተት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ወይም በቴሌግራም በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የጤና ሚኒስቴር አዲስ የህክምና ትምህርት ኢንሼቲቭ (NIMEI) 2016 ዕጩ ተወዳዳሪዎች የቃል ፈተና የሚሰጥበትን ቀን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

በከፍተኛ ጥንቃቄ በእጅ የታረመ የፅሁፍ ፈተና ውጤት በዚህ ሳምንት እንደሚጠናቀቀቅ ኮሌጁ አሳውቋል፡፡

የፅሁፍ ፈተና ውጤቱ ከተለጠፈ ከአንድ ሳምንት በኋላ የቃል ፈተናው ሊሰጥ እንደሚችል ኮሌጁ ገልጿል (ከክልል ለሚመጡ ተፈታኞች በቂ ጊዜ ለመስጠት፡፡)

የፈተናው ሒደት ግልፅነት በተሞላበት ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን የጠቆመው ኮሌጁ፤ ተወዳዳሪዎች የሚኖራቸውን ማንኛውም አይነት ቅሬታ የሚያቀርቡበት ዕድል ይመቻቻልም ብሏል፡፡

@tikvahuniversity
በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና #በድጋሜ የምትወስዱ ተፈታኞች ምዝገባ እስከ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በዚህም፦

➧ በሰኔ 2015 ዓ.ም እና በየካቲት 2016 ዓ.ም ተፈትናችሁ የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለምትፈልጉ እንዲሁም

➧ ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት የሕግ መውጫ ፈተና ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያላገኛችሁና አሁን በድጋሜ ለመውሰድ የምትፈልጉና ስም ዝርዝራችሁ ከቀድሞው ዩኒቨርስቲያችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላችሁ አመልካቾች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ምዝገባ እንድታጠናቅቁ ተብሏል፡፡

ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

በሰኔ 2015 ዓ.ም እና በየካቲት 2016 ዓ.ም ተፈተናችሁ የማለፊያ ውጤት ያልመጣላችሁ አሁን በድጋሜ መፈተን ለምትፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባችሁን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር ብቻ የምትፈጽሙ ይሆናል፡፡

ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጣችሁ በድጋሜ ለመፈተን የምትፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራችሁ ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያችሁ መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባችሁን የአገልግሎት ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ ስካን ኮፒ በማድረግ በ [email protected] ኢሜል አድራሻ እንድትልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የተዘጋጀ "ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ" ፕሮግራም (National Cyber Talent Challenge Program)

በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

የታለንት መስኮች፦

➧ Cyber Security
➧ Cyber Development
➧ Embedded Systems
➧ Aerospace

ምዝገባ የሚያበቃው 👇
ግንቦት 30/2016 ዓ.ም

ለበለጠ መረጃ👇
0904311833
0943579970
0904311837


ለመመዝገብ፦ https://talent.insa.gov.et
ይለማመዱ!

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የኦንላይን የመፈተኛ ፕላትፎርም አጠቃቀምን ይለማመዱ!

ፕላትፎርሙን እንዴት መጠቀምና እንዴት ፈተናውን መውሰድ እንደሚቻል ለማሳየት በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተዘጋጀን የአራት ደቂቃ ገላጭ ቪዲዮ በተከታዩ ሊንክ በመግባት ይመልከቱ፡፡ ራስዎን ለፈተናው ያዘጋጁ!

ቪዲዮውን ይመልከቱ 👇
https://www.youtube.com/watch?v=PdAu-FI-Q5M


@tikvahuniversity
በ2016 ዓ.ም የትክክለኛነት ማረጋገጫ ከተሰራላቸው 10,238 የትምህርት ማስረጃዎች 1 ነጥብ 6 በመቶዎቹ ትክክለኛውን መስፈርት #የማያሟሉ ሆነው መገኘታቸውን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለፀ።

ሕገ-ወጥ የትምህርት ማስረጃ የዜጎችን የተወዳዳሪነት አቅም በማሳጣት፣ በተቋማት ላይ ብልሹ አሠራሮች በማስፈን በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ማርታ አድማሱ ተናግረዋል፡፡

ሕገ-ወጥ የትምህርት ማስረጃ የብቃት መመዘኛና የመቁረጫ ነጥብ ያላሟሉ፣ ተዛማጅ ባልሆኑ የትምህርት ዘርፍ እና ፍቃድ በሌለው ኮሌጅ ማስረጃ የሚያገኙ መሆናቸውን ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የትክክለኛነት ማረጋገጫ ከተሰራላቸው 10,238 የትምህርት ማስረጃዎች 1 ነጥብ 6 በመቶዎቹ ትክክለኛውን መስፈርት #የማያሟሉ ሆነው መገኘታቸውን ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡

በፌዴራል እና የክልል መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ላይ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ በትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ የማጣራት ሥራው ሲጠናቀቅ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

@tikvahuniversity
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞችን በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በክልሉ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚወስዱ ከ53 ሺህ በላይ ተማሪዎች የቲቶሪያል ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ጥራት ኤጀንሲ ገልጿል፡፡

በክልሉ በሁለት ኮዶች የሚሰጠው የ2016 ዓ.ም ፈተና፤ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና ዘንድሮ ትምህርታቸውን ተከታትለው የሚፈተኑትንም ያካተተ መሆኑን የኤጀንሲው ዳይሬክተር ታደሰ ካሕሳይ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ከ53 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ ተፈታኞችን በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለመፈተን ከተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ በክልሉ ለሚሰጠው የስምንተኛ ክፍል ፈተና 123 ሺህ ተፈታኞች በሁለት ባች ተከፍለው ከሰኔ 11-13/2016 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ጠቁመዋል፡፡ #ኢፕድ

@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ለማስፈተን ፍላጎት ያለው ማንኛውም የመንግሥትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የተደራጀ የኮምፒውተር ላብራቶሪ ሊኖረው እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በዚህም የትኛውም ትምህርት ቤት፦

1. ዴስክቶፕ ወይም ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች
2. የውስጥ ኔትዎርክ (LAN)
3. የኢንተርኔት መስመር ከበቂ ባንድዊድዝ ጋር (ከመፈተኛ የኮምፒውተር ብዛት አንጻር)
4. የመጠባበቂያ ኃይል (ጄኔሬተር) ማሟላትና ለትምህርት ቢሮዎች ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡

በዚህም በቢሮዎች በኩል መሟላቱ ሲረጋግጥ የፈተና ማዕከል በመሆን ተማሪዎቹን ማስፈተን እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ለፈተና የሚዘጋጁት ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ማሟላት ያለበቸው ዝቅተኛ ስፔስፊኬሽን፦

RAM ------------ 4GB or higher
Storage ---------250GB or higher
Processor Speed ----- 2.5GHZ or higher
Processors ----- Intel Core i3 or higher
OS ----------Windows 10
Browsers ---------Safe Exam Browser and other
Accessories ---------- Keyboards and Mouse for desktop computers.

@tikvahuniversity
#MoE

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን የሚወስዱ ተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀ ማስፈንጠሪያ (URL) ላይ በመግባት እንዲለማመዱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ከስር የተቀመጡት ማስፈንጠሪያዎች ተፈታኝ ተማሪዎች የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው ዕለት ደግሞ መፈተኛ ይሆናሉ።

Note:

እስካሁን Username እና Password ያለገኛችሁ ተፈታኞች፤ ከትምህርት ቤት አስተባባሪዎች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ክላስተር አንድ

አዲስ አበባ፦ https://c2.exam.et
ሲዳማ ክልል፦ https://c2.exam.et
ትግራይ ክልል፦ https://c2.exam.et

ክላስተር ሁለት

ደቡብ ም/ኢ/ክልል፦ https://c3.exam.et
ጋምቤላ ክልል፦ https://c3.exam.et
አማራ ክልል፦ https://c3.exam.et

ክላስተር ሦስት

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፦ https://c4.exam.et
ሀረሪ ክልል፦ https://c4.exam.et
አፋር ክልል፦ https://c4.exam.et
ኦሮሚያ ክልል - 1
• አዳማ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• አጋሮ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• አምቦ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ምስራቅ አርሲ፦ https://c4.exam.et
• ምዕራብ አርሲ፦ https://c4.exam.et
• አሰላ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ባሌ፦ https://c4.exam.et
• ባቱ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ቤሾፍቱ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ቦረና፦ https://c4.exam.et
• ቡሌ ሆራ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ቡኖ በደሌ፦ https://c4.exam.et
• ዶዶላ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ምስራቅ ባሌ፦ https://c4.exam.et
• ምስራቅ ቦረና፦ https://c4.exam.et
• ጉጂ፦ https://c4.exam.et
• ምስራቅ ሐረርጌ፦ https://c4.exam.et
• ምዕራብ ሐረርጌ፦ https://c4.exam.et
• ሆለታ ከተማ፦ https://c4.exam.et
• ሆሮ ጉዱሩ፦ https://c4.exam.et
• ኢሉባቦር፦ https://c4.exam.et

ክላስተር አራት

ድሬዳዋ ከተማ፦ https://c5.exam.et
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2
• ጅማ፦ https://c5.exam.et
• ጅማ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ቄለም ወለጋ፦ https://c5.exam.et
• ማያ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• መቱ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሞጆ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሞያሌ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ነጆ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ነቀምት ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሮቤ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሰንዳፋ በኬ፦ https://c5.exam.et
• ሻኪሶ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሻሸመኔ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሸገር ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ሸኖ ከተማ፦ https://c5.exam.et
• ምስራቅ ሸዋ፦ https://c5.exam.et
• ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ)፦ https://c5.exam.et
• ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፦ https://c5.exam.et
• ምዕራብ ሸዋ፦ https://c5.exam.et
• ምስራቅ ወለጋ፦ https://c5.exam.et
• ምዕራብ ወለጋ፦ https://c5.exam.et
• ምዕራብ ጉጂ፦ https://c5.exam.et
• ወሊሶ ከተማ፦ https://c5.exam.et

@tikvahuniversity
ዘንድሮ በኦንላይን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የይለፍ ቃላቸውን ከየት ማግኘት እንደሚችሉ በተደጋጋሚ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲን እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡

የተፈታኝ ተማሪዎች Username እና Password ከዚህ በፊት ለትምህርት ቢሮዎች መላኩን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በመሆኑም እስካሁን Username እና Password ያላገኛችሁ ተፈታኞች፤ ከትምህርት ቤት አስተባባሪዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለሚጀምረው ዓመታዊ የስነ-ጽሁፍ ውድድር 'ፈኒ ዶጊሳ' የምዝገባ ጊዜን እስከ ነገ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም አራዝሟል፡፡

የመመዝገቢያ አማራጮች፦
የተቋሙ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሠራተኞች በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሸግግር ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች በስልክ ቁ. 0953990560 ላይ ሙሉ ስም፣ የሥራ ዘርፍና ቦታ፣ የምትወዳደሩበትን ዘርፍና ይዘት በማካተት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ወይም በሞባይሉ የቴሌግራም አካውንት በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል አስመርቋል፡፡

ማዕከሉ የሥራ ዕድል ፈጣሪዎች (ስታርታፖች) ስልጠና የሚያገኙበትና ሃሳባቸውን ወደ ንግድ የሚቀይሩበት ይሆናል ተብሏል፡፡

ማዕከሉ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራን እና በድሬዳዋና አካባቢዋ ለሚገኙ ወጣቶች የሃሳብ ማበልፀጊያ ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 14 ስታርታፕ ቢዝነሶችን ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ወደሥራ ለማስገባት እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ፈተና (DELF A1 & DELF A1) ሰኔ 1 እና 2/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

ፈተናው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ትብብር የሚሰጥ ነው፡፡

ፈተናው የሚሰጠው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማራኪ ካምፓስ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አካዳሚ በቡና ጥራት ቁጥጥር እና ቅምሻ ስልጠና በቀን እና በማት መርሐግብሮች ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል!

የማታ መርሐግብር የመጀመሪያ ባች ተማሪዎች ትምህርት ሰኔ 3/2016 ዓ.ም ይጀምራል።

ስልጠናው ከሦስት እስከ ሦስት ወር ከግማሽ ይሰጣል። ክፍያ፦ ብር 45,000

ይመዝገቡ!!

በተከታዩ ሊንክ ይመዝገቡ 👇

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe9XBw_BXSv56zYBUUjdaDypd74CUlIn4NKPci3vZswfcPbrw/viewform?usp=sf_link

@tikvahuniversity
ይለማመዱ!

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የኦንላይን የመፈተኛ ፕላትፎርም አጠቃቀምን ይለማመዱ!

ፕላትፎርሙን እንዴት መጠቀምና እንዴት ፈተናውን መውሰድ እንደሚቻል ለማሳየት በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተዘጋጀን የአራት ደቂቃ ገላጭ ቪዲዮ በተከታዩ ሊንክ በመግባት ይመልከቱ፡፡ ራስዎን ለፈተናው ያዘጋጁ!

ቪዲዮውን ይመልከቱ 👇
https://www.youtube.com/watch?v=PdAu-FI-Q5M


@tikvahuniversity
2024/09/29 23:26:43
Back to Top
HTML Embed Code: