Telegram Web Link
#ጥቆማ

በአፍሪካ ፀጥታ እና ደህንነት ላይ ራዕይ ያለዎት ባለሙያ ነዎት? በመስኩ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት አስበዋል?

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፀጥታ እና ደህንነት ኢንስቲትዩት (IPSS) ልዩ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም የማመልከቻ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

Executive Master’s Degree in Managing Peace and Security in Africa (MPSA) የተባለው ፕሮግራም፤ በፀጥታ እና ደህንነት ዙሪያ የሚሰሩ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ አመራሮችን አቅም ለማጎልበት ግብ ያደረገ ፕሮግራም ነው፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው አመልካቾች በኦንላይን የማመልከቻ ቅፁን መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለማመልከት 👉 https://bit.ly/41FUh5H

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👉 ግንቦት 26/2016 ዓ.ም

ፕሮግራሙ የሚጀምረው 👉 መስከረም 20/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገለፀ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው ይህ የተገለፀው።

በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተሠራው የተቋማት ኦዲት ሪፖርት የ2014 በጀት ዓመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 24 መሥሪያ ቤቶች ውስጥ 13 ተቋማት ላይ አስተደደራዊ ዕርምጃ መወሰዱን ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡

በዚህም የወላይታ ሶዶ፣ ጋምቤላ እና ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን ተናግረዋል።

ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መሠጠቱም ተገልጿል። #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
#ይመዝገቡ

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለወጣቶች በቤት አያያዝ ሙያ (Domestic Work) የአጭር ጊዜ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡

ከዛሬ ግንቦት 18/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሜክሲኮ ገነት ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት መመዝገብ ይቻላል።

ምዝገባው እስከ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፤ ስልጠናው ሰኔ 1/2016 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

የምዝገባ መስፈርቶች፦

➧እድሜ ከ 18 እስከ 35 ዓመት
➧ስምንተኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች
➧ለ21 ቀናት ሳያቆራርጡ መሰልጠን የሚችሉ
➧የብቃት ምዘና ለመመዘንና ለመመዝገቢያ 100 ብር ያስፈልጋል።

@tikvahuniversity
#MoH

በአገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የጤና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ተጠናቋል።

የጤና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና በሃገር አቀፍ ደረጃ ግንቦት 15 እና 16/2016 ዓ.ም በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ተሰጥቷል።

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Health Officer, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Technology, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatrics Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ የጤና ባለሙያዎች በኮምፒውተር በታገዘ የፈተና አሰጣጥ ስርዓት ፈተናውን ወስደዋል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ኢኖቬቲቭ፣ ሊተገበር የሚችል እና ተፅዕኖ የሚፈጥር የቢዝነስ ሀሳብ አለዎት? ወጣት ተማሪ ነዎት?

እንግዲያውስ የሥራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶችን የሚያበረታታው Youth Challenge Fund ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ!

መስፈርቶች፦

➧ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➧ የቅድመ ምረቃ ተማሪ ከሆኑ ዕጩ ተመራቂ መሆን ያለብዎት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የማስተርስ እና ፒ.ኤች.ዲ ትምህርትዎን እየተከታተሉ ከሆነም ማመልከት ይችላሉ፡፡

➧ ለግብርና ምርታማነት፣ ዘላቂነት እና እሴት መጨመር አስተዋፅኦ ለሚያደርግ ማንኛውም የትምህርት መስክ የምትማሩ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

እንዴት ማመልከት ይቻላል?

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆኑ [email protected] ላይ ማመልከቻዎን ይላኩ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆኑ
[email protected] ላይ ማመልከቻዎን ይላኩ።

በተጨማሪም [email protected] እና [email protected] ላይ ግልባጭ ያድርጉ፡፡

ምን ድጋፍ ይደረጋል?

አሸናፊ የቢዝነስ ሀሳቦች ከ 5,000 እስከ 20,000 ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም የቢዝነስ ኮቺንግና ክትትል እገዛ ይደረግላቸዋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👉 ሰኔ 1/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
ስድስት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች በዓለም ላይ ካሉ ሁለት ሺህ "ከፍተኛ ደረጃ" ያላቸው ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ለመካተት ቻሉ።

የዩኒቨርሲቲዎች ዓመታዊ ደረጃ የሚያወጣው Center for World University Rankings (CWUR) የተባለ ተቋም የዩኒቨርሲቲዎችን የ2024 ጀረጃ ይፋ አድርጓል።

ደረጃ ከተሰጣቸው 20,966 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 2,000 ዩኒቨርሲቲዎች ወይም 9 ነጥብ 5 በመቶዎቹ ብቻ "ከፍተኛ" ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በተቋሙ የ2024 ደረጃ መሠረት፦

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ➭ 841
2. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ➭ 1701
3. መቐለ ዩኒቨርሲቲ ➭ 1748
4. ጅማ ዩኒቨርሲቲ ➭ 1767
5. ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ➭ 1886
6. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ➭ 1982ኛ መሆን ችለዋል።

በዘንድሮው ደረጃ ከቀዳሚ አስር ዩኒቨርሲቲዎች፣ ስምንቱ የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው።

ላለፋት 12 ዓመታት ደረጃ ሲያወጣ የቆየው ተቋሙ፤ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡት የትምህርት ጥራት፣ የምርምር ጥራት እና የፋክሊቲ ደረጃ በመሳሰሉት መለኪያዎች ይገመግማል።

መንግሥታት እና ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት እና የምርምር ውጤቶቻቸውን እንዲያሻሽሉ በማማከር የሚታወቀው ተቋሙ፤ የዩኒቨርሲቲዎችን ዓለም አቀፍ ደረጃ ከአላማ፣ ግልፅነት እና ዘላቂነት መርሆች አንፃር ይመድባል።

የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃን ይመልከቱ፦ https://cwur.org/2024.php

@tikvahuniversity
Tikvah-University
ሦስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ.ሲ.ቲ. ፍጻሜ ውድድር ለመሳተፍ ወደ ቻይና አቅንተዋል። በቅርቡ በቱኒዚያ በተካሔደ የሁዋዌ አይ.ሲ.ቲ. የክፍለ አህጉራዊ ፍፃሜ ውድድር፥ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወቃል። እነዚህ ተማሪዎች በ8ኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ.ሲ.ቲ. ፍጻሜ ውድድር ለመሳተፍ ቻይና ገብተዋል። የፍጻሜ ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ…
በቻይና ሼንዘን ከተማ በተካሔደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ.ሲ.ቲ. ፍጻሜ ውድድር የተሳተፉት ሦስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተገኙ ሦስት ተማሪዎች ኢትዮጵያን በመወከል በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ተሳትፈዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎቹ፤ የውድድሩ ሦስተኛውን ሽልማት ከማሌዢያ፣ ሜክሲኮ እና ኬንያ ቡደን ጋር መጋራት መቻላቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሶስት የውድድር ትራኮች (Innovation, Network and Computing) ተካፋፍሎ ተካሒዷል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከዚህ በታች በተገለፀው የትምህርት መስክ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ በመምህርነት በቋሚ ኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ➤ የሥራ መደብ፦ መምህርነት ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 16 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪ ➤ የሥራ ቦታ፦ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ➤ የመመዝገቢያ…
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በ Doctor of Medicine መምህራን አወዳድሮ ለመቅጠር ባለፈው ወር ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን አሟልታችሁ የተመዘገባችሁ ብቻ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግቢ ለፈተና መጠራችሁን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ተፈታኞች ለፈተና ስትሔዱ መታወቂያ መያዝ እና በሰዓቱ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ማንኛውም ተፈታኝ የሞባይል ስልክ ይዞ ወደ ፈተና መግባት አይችልም፡፡

@tikvahuniversity
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በኦንላይን ለሚወስዱ 267 የሠመራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመለማመጃ ፈተና (Mock Exam) ሰጥቷል።

የመለማመጃ ፈተናው ተማሪዎቹ የይለፍ ቃላቸውን በመቀየር በተግባር ለዋናው ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያግዝ መሆኑ ተመላክቷል።

ከተማሪዎቹ ውስጥ 16ቱ በዩኒቨርሲቲው የማጠናከሪያ ትምህርት እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተገልጿል።

የሠመራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን እንዲወስዱ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ የተገለፀ ሲሆን፤ በክልሉ ያሉ ቀሪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በወረቀት ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሏል።

@tikvahuniversity
በትግራይ ክልል 53 ሺህ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ፈተና ሳይወስዱ የቀሩ ተማሪዎች መኖራቸው በ2016 ዓ.ም ለፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን ቁጥር ከፍ እንዳደረገው የክልሉ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ገልጿል።

በዚህም ተፈታኞቹ ኮድ 01 እና ኮድ 07 በሚል በሁለት ተከፍለው ፈተናቸውን እንደሚፈተኑ የኤጀንሲው ዋ/ዳይሬክተር ታደሰ ካህሳይ (ዶ/ር) ለአራዳ ኤፍኤም ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈተና የተሰጠ ቢሆንም ሁሉንም መፈተን ባለመቻሉ አሁን ላይ ቁጥሩ ከፍ እንዲል ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል።

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በትግራይ ክልል ከሐምሌ 02-12/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ከዚህ በፊት መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
ደረጃ "Milk Run" የተሰኘ አገር አቀፍ በዩኒቨርሲቲዎች የሥራ አውደ ርዕይ እና ብሔራዊ የሙያ ቅጥር ኤክስፖ ይፋ አድርጓል።

ኹነቶቹ ተመራቂ ተማሪዎችን ከተለያዩ ቀጣሪ ተቋማት ጋር የሚያገናኙ ናቸው።

በአገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበረው ኢኒሼቲቩ፤ ደረጃ ከማስተርካርድ፣ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።

በዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የሥራ አውደ ርዕይ

በስድስት ክልሎች የሚገኙ 30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተደራሽ ያደርጋል።

ብሔራዊ የሙያ ቅጥር ኤክስፖ

ለተመራቂ ተማሪዎች የቅጥር ዕድል የሚፈጥር ሲሆን 400 ኩባንያዎች እና 20,000 ተማሪዎች ይሳተፉበታል።

በዩኒቨርሲቲዎች የሚደረጉ ጉብኝቶች

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ➧ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ➧ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ➧ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ➧ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ➧ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም

የ "Milk Run" አገር አቀፍ ኢኒሼቲቭ የማጠቃለያ መርሐግብር ጥቅምት 7 እና 8/2017 ዓ.ም በሚሌኒየም አዳራሽ በሚከናወን ብሔራዊ የሙያ ኤክስፖ ይጠናቀቃል። #Dereja

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና በአዲስ አበባ በመሰጠት ላይ ነው።

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ለሚገኙ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

ሞዴል ፈተናው በአግባቡ እንዲሰጥ ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች መመደባቸውን በቢሮው የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ገልፀዋል፡፡

ከተማ አቀፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity
የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ አመራሮች ካውንስል ተመሠረተ።

ካውንስሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ዘርፉን ማስተሳሰር የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የአመራር ካውንስሉ ጥናትና ምርምር በማድረግ ልዩነት መፍጠር የሚችል የሰው ኃይል ማፍራት ኃላፊነት እንደተጣለበት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ2,000 በላይ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት በመንግሥት እና በግል ባለቤትነት ስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ከ100 በላይ የሚሆኑት የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ጠቅሰዋል፡፡ #ENA

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ አመራሮች ካውንስል ተመሠረተ። ካውንስሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ዘርፉን ማስተሳሰር የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ የአመራር ካውንስሉ ጥናትና ምርምር በማድረግ ልዩነት መፍጠር የሚችል የሰው ኃይል ማፍራት ኃላፊነት እንደተጣለበት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልፀዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከ2,000 በላይ የቴክኒክና…
ዛሬ ግንቦት 21/2016 ዓ.ም በይፋ የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት አመራሮች ካውንስል ሥራ አስፈፃሚ አመራሮችን መርጧል።

በዚህም መለስ ይግዛው ከጄነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት፣ ተሻለ ዱጉማ ከአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ፕሬዝዳንት እና መልካሙ ባራሳ ከሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጸሐፊ ሆነው ተመርጠዋል።

@tikvahuniversity
2024/09/29 17:43:20
Back to Top
HTML Embed Code: