Telegram Web Link
#ይለማመዱ

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና #በኦንላይን የሚወስዱ ከሆነ ፈተናውን የሚወስዱበት አድራሻ ላይ በመግባት መለማመድ ይጀምሩ፡፡

ተፈታኞች ከተደለደላችሁበት ክላስተር ውጪ ሲስትሙን መጠቀም እንደማትችሉ ያስታውሱ፡፡

በተለያዩ ቦታዎች ዘንድሮ የመልቀቂያ ፈተናውን የሚወስዱ የበይነ መረብ ተፈታኞች ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

ፈተናው የሚሰጥባቸው አድራሻዎች፦

👉 https://c2.exam.et
👉
https://c3.exam.et
👉
https://c4.exam.et
👉
https://c5.exam.et
👉
https://c6.exam.et

(ተፈታኞች የሚገኙበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ይገኛል፡፡)

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ፈተና ለውጭ ተመዛኞች (TOEFL iBT) ፈተና ይሰጣል።

በኦንላይን ምዝገባ በማድረግ በመረጡት ቀን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከል ፈተናውን መውሰድ ይችላሉ።

ፈተና የሚሰጥባቸው ቀናት፦

➧ ግንቦት 21/2016 ዓ.ም
➧ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም
➧ ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም
➧ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም
➧ መስከረም 11/2017 ዓ.ም
➧ ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም
➧ ኅዳር 14/2017 ዓ.ም
➧ ታኅሳስ 19/2017 ዓ.ም

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇

https://www.ets.org/toefl/test-takers/ibt/register/how-to-register.html

ለተጨማሪ መረጃ፦

ስልክ ቁ.፦ 0912685860
ኢሜይል፦ [email protected]

@tikvahuniversity
Tikvah-University
በራያ አካባቢ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 850 የሚሆኑ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እንዲያጠናቅቁና ማጠናከሪያ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡ ከራያ አካባቢዎች የተውጣጡት ተማሪዎች ከሐሙስ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መግባት መጀመራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ሰምቷል። በራያ አካባቢዎች ትምህርት ከተቋረጠ…
በአላማጣ ከተማና አካባቢው በተፈጠረው አለመረጋጋት የትምህርት ሒደቱ መስተጓጎሉን ተከትሎ 829 ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመከታተል ወልድያ ዩኒቨርሲቲ መግባታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ከራያ አካባቢዎች የተውጣጡት ተማሪዎች ከግንቦት 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ሲሆን ከትናንት ግንቦት 12/2016 ዓ.ም ጀምሮ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለአንድ ወር የሚሰጥ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲው ከገቡበት ቀን ጀምሮ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ተሟልቶላቸው እየተማሩ ነው ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን አሳወቀ።

በ2016 ዓ/ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ተፈታኞች ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 እስከ 21/2016 መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የአገልግሎት ክፍያ  500.00 ብር በ ' ቴሌ ብር ' ብቻ የሚፈጸም መሆኑ አስገንዝቧል።

#ለመጀመሪያ_ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማቸው በኩል መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎችን በተቋማቸው በኩል እንደሚደርሳቸው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ETA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎቻቸውን መረጃ እስከ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም እንዲያስገቡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል።

ተቋማቱ የተፈታኞቻቸውን መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ቴምፕሌት በመጠቀም መላክ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አስታውሷል።

(የባለሥልጣኑ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የአክሰስ ማይክሮ ስኮላርሺፕ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 38 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተማሪዎቹ ለ360 ሰዓታት በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠውን የእንግሊዝኛ ቋንቋና የአመራር ክህሎት ስልጠና ላለፉት ሁለት ዓመታት ተከታትለው ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ስልጠናው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተሰጠ ነው።

@tikvahuniveristy
#ጥቆማ

ለ Fulbright African Research Scholars Program (FARSP) ያመልክቱ!

የዩኒቨርሲቲ መምህር ነዎት? ምርምርዎትን በዩናይትድ ስቴትስ ማከናወን ይፈልጋሉ?

ዓመታዊው የፉልብራይት አፍሪካ የምርምር ምሁራን ፕሮግራም (FARSP) 2025/26 ለአመልካቾች ክፍት ሆኗል፡፡

የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው 👇
ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም

ለማመልከት 👇
https://apply.iie.org/fvsp2025

ለማንኛውም አይነት ጥያቄ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 👇 [email protected]

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የብዝኃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ተመራማሪዎች ከእንቦጭ አረም የተለያዩ ጌጣጌጦች እና ቁሳቁሶችን ሰርተዋል፡፡

በአርባ ምንጭ ከተማ ዙሪያ የሚገኙት ዓባያ እና ጫሞ ሐይቆች የዚህ መጤ አረም ተጠቂ በመሆናቸው አረሙን ለማጥፋት የዩኒቨርሲቲው የብዝኃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል የተለያዩ ምርምሮችን እየሠራ ነው ተብሏል፡፡

የእንቦጭ አረም የተለያዩ ጌጣጌጦች ለመስራት እንደሚጠቅም እንዲሁም አረሙን ከተለያዩ ዕፅዋት ጋር በማደባለቅ የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ ለማምረት እንደሚቻል በምርምር መረጋገጡን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የእንቦጭ አረም ግንዱ ጠንካራ በመሆኑ ከአረሙ ዘንቢሎች፣ ምንጣፎች፣ ጫማዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶች እና ጌጣጌጦችን መሥራት ተችሏል፡፡

በቀጣይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማኣ አካባቢዋ የሚገኙ ሥራ-አጥ ወጣቶችን በማሠልጠን የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ለማድረግ ይሠራል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ኢኖቬቲቭ፣ ሊተገበር የሚችል እና ተፅዕኖ የሚፈጥር የቢዝነስ ሀሳብ አለዎት? ወጣት ተማሪ ነዎት?

እንግዲያውስ የሥራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶችን የሚያበረታታው Youth Challenge Fund ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ!

መስፈርቶች፦

➧ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➧ የቅድመ ምረቃ ተማሪ ከሆኑ ዕጩ ተመራቂ መሆን ያለብዎት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የማስተርስ እና ፒ.ኤች.ዲ ትምህርትዎን እየተከታተሉ ከሆነም ማመልከት ይችላሉ፡፡

➧ ለግብርና ምርታማነት፣ ዘላቂነት እና እሴት መጨመር አስተዋፅኦ ለሚያደርግ ማንኛውም የትምህርት መስክ የምትማሩ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

እንዴት ማመልከት ይቻላል?

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆኑ [email protected] ላይ ማመልከቻዎን ይላኩ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆኑ
[email protected] ላይ ማመልከቻዎን ይላኩ።

በተጨማሪም [email protected] እና [email protected] ላይ ግልባጭ ያድርጉ፡፡

ምን ድጋፍ ይደረጋል?

አሸናፊ የቢዝነስ ሀሳቦች ከ 5,000 እስከ 20,000 ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም የቢዝነስ ኮቺንግና ክትትል እገዛ ይደረግላቸዋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👉 ሰኔ 1/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 17 እና 18/2016 ዓ.ም ሊያካሒደው የነበረውን 7ኛ ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ አራዝሟል፡፡

ጉባኤው ወደ ግንቦት 24 እና 25/2016 ዓ.ም መቀየሩን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በጉባኤው መራዘም ለሚፈጠረው የትኛውም ጫና ዩኒቨርሲቲው ተሳታፊዎችንና ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች ይቅርታ ጠይቋል፡፡

@tikvahuniversity
#ETA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎቻቸውን መረጃ እስከ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም እንዲያስገቡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል።

ተቋማቱ የተፈታኞቻቸውን መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ቴምፕሌት በመጠቀም መላክ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አስታውሷል።

(የባለሥልጣኑ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ሦስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ.ሲ.ቲ. ፍጻሜ ውድድር ለመሳተፍ ወደ ቻይና አቅንተዋል።

በቅርቡ በቱኒዚያ በተካሔደ የሁዋዌ አይ.ሲ.ቲ. የክፍለ አህጉራዊ ፍፃሜ ውድድር፥ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወቃል።

እነዚህ ተማሪዎች በ8ኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ.ሲ.ቲ. ፍጻሜ ውድድር ለመሳተፍ ቻይና ገብተዋል።

የፍጻሜ ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18/2016 ዓ.ም በቻይና ሼንዘን ከተማ ይካሔዳል።

ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን ወክለው በ7ኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ.ሲ.ቲ. ፍጻሜ ውድድር የተሳተፉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሦስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#Update የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ገለፀ። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው "ሰላም ሰፈር" ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ረቡዕ ከጠዋቱ 2:45 አካባቢ እንደሆነ ፖሊስ አመልክቷል። "በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረ አለመግባባት…
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዋን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ግለሰብ ጀርባዋን በጩቤ ሦስት ቦታ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 1 ፖሊስ ገለፀ።

ተከሳሽ አቶ ዮሐንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰብ የሴት ጓደኛው የነበረችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ላይ ጭካኔ የተሞላበት የግድያ ወንጀል በቀን ግንቦት 9/2016 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 2፡45 አካባቢ መፈፀሙን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

መርማሪ ፖሊስ እና ዐቃቢ ሕግ በጋራ በመሆን ተጠርጣሪው ላይ ክስ መስርተው፣ ምርመራ በማጣራት የወንጀል ድርጊቱን የሚያስረዱ የሰው እና የህክምና ማስረጃዎች በማስደገፍ ለሚመለከተው ፍ/ቤት ልከዋል፡፡

የክስ መዝገቡ የደረሰው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍ/ቤትም መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539 (1ሀ) ስር የተመለከተውን መተላለፉ ካረጋገጠ በኃላ፤ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ በቀን ግንቦት 15/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወንጀለኛውን ያርማል ማህበረሰቡንም ያስተምራል በማለት በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።
#አሶሳዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
2024/09/29 21:31:03
Back to Top
HTML Embed Code: