Telegram Web Link
"ትምህርት ለትውልድ" በተባለውና የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት መሰብሰቡን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ባለፈው ዓመት መጨረሻ በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አሰተዳደሮች ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መሰብሰቡን በሚኒስቴሩ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል።

በ2016 ዓ.ም ብቻ በትምህርት ለትውልድ መርሐግብር ከ4 ሺህ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ሥራ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
#ምስላዊ_መረጃ

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁ ይታወሳል፡፡

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስታርት አፕ ማዕከል በቅርቡ ሥራ እንደሚያስጀምር ገልጿል፡፡

መንግሥት የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማስፋፋት የስታርት አፕ ልማትን የሚያጎለብቱ የተለያዩ ፖሊሲዎች እያተዘጋጁ እንደሆነ ይገልጻል፡፡

በቅርቡም የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ወጣቶች ሐሳባቸውን ወደ ተግባር ለማዋል በሚፈልጉበት ወቅት ያለምንም የንግድ ቤት ኪራይ ውል ሥራ መጀመር የሚችሉበትን አዲስ አሠራር መዘርጋቱን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

በተጨማሪም ማንኛውም የውጭ አገር ፈንድ ያገኘ ስታርት አፕ ሙሉ በሙሉ የውጭ ምንዛሪውን ለሚፈልገው ሥራ ማዋል የሚችልበት አሠራር ተግባራዊ መደረጉ ተገልጾ ነበር።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚከፍተው የስታርት አፕ ማዕከል በዘርፉ የተጀመሩ ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር አጋዥ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

@tikvahuniversity
#DambiDolloUniversity

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ዕጩ የቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች #ሞዴል የመውጫ ፈተና መስጠት ጀምሯል፡፡

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14-21/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይወቃል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለዕጩ የቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎቻቸው #ሞዴል የመውጫ ፈተና እንዲሰጡ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ያስገድዳል፡፡

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በኦንላይን ለመስጠት እየተከናወኑ በሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል።

በውውይይቱ የክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተሳትፈዋል።

የመልቀቂያ ፈተናውን በአዲስ አበባ በበይነ መረብ ለመስጠት ከወዲሁ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት የሚያስፈልጉ፦

➭ ኮምፒውተሮች፣
➭ ላፕቶፖች፣
➭ ታብሌቶችና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የግል ትምህርት ቤቶች ለፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ከወዲሁ ማዘጋጀት በመጀመር ፈተናው በታቀደለት መርሐግብር እንዲሰጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል። #አዲስአበባትምህርትቢሮ

@tikvahethiopia
#MoE

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ 25 የክልል ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና በተጨማሪ የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እያደሩ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ተናግረዋል።

የፈተና አሰጣጡን ስኬታማ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ሚኒስትር ድኤታዋ ጠቁመዋል።

የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተገልጿል።

@tikvahuniversity
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ያቋቋመው 'አፋር ታለንት አካዳሚ' የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞቹን ተቀብሏል፡፡

አካዳሚው 103 የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎችን በዚህ ሳምንት መቀበሉን የኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ባለፈው ጥቅምት በሠመራ ዩኒቨርሲቲ እና በአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ትብብር የተቋቋመው አካዳሚው፤ በስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡና ባለልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎችን በመመልመል የሚቀበል መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#DV2025

የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ 2025 አሸናፊዎች ነገ ይፋ ይደረጋሉ።

ለዲቪ 2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

ውጤቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል።

Via @tikvahethiopia
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል IELTS የፈተና ማዕከል የIELTS ፈተና ግንቦት 17/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) መውሰድ ለሚፈልጉ አመልካቾች እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገፅ ላይ በመግባት ኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations

ለፈተናው ዝግጅት የሚያስፈልግዎትን ስልጠና እና ምክር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ!

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለመላ የክርስትና ዕምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን መልካም የትንሳኤ በዓል ይመኛል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙና በዓሉን ከቤተሰቦቻችሁ ርቃችሁ እያከበራችሁ ላላችሁ ተማሪዎች መልካም በዓል እንመኛለን።

@tikvahuniversity
2024/09/30 11:26:06
Back to Top
HTML Embed Code: