Telegram Web Link
#AdigratUniversity

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በ2014 ዓ.ም ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድባችሁ መማራችሁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በ2013 ዓ.ም ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ስትወጡ ያልጨረሳችሁት የተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶች መኖራቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በመሆኑም ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ስትወጡ ያላጠናቀቃችሁት ትምህርት ያላችሁ ተማሪዎች በዚህ ሴሚስተር እንድታጠናቅቁ ከመጋቢት 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም ባለው ግዜ መመዘገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

@tikvahuniversity
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ መደበኛ እና የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ተቀብሎ ለማስተማር ለመጋቢት 16 እና 17/2016 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም የመማር ማስተማር ሒደትን በድጋሜ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገለፀ።

የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ የጠቆሙት የተቋሙ የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት አብዱልቃድር ከሪም (ዶ/ር) ፤ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት ከ11 ሺህ በላይ ተማሪዎች እያስተማረ ይገኛል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ያጋጠመውን የበጀት እጥረት ተቋቁሞ በቅርቡ 2,035 ተማሪዎች ማስመረቁንም አስታውሰዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በተለይ የምርምር እና የመዋቅር ሪፎርም ሥራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ወደ ተግባር እንደሚገባ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አካሒዷል፡፡

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ሐየሎም ስዩም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጧል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ጸሐፊ ሆነው የተመረጡ ሲሆን ሌሎች ዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚዎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መመረጣቸውም ታውቋል።

አዲሶቹ አመራሮች ኅብረቱን ለቀጣይ ሁለት ዓመታት እንደሚያገለግሉ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በ Post Basic Nursing ለመማር የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ አመልካቾች ምዝገባ መጋቢት 25 እና 26/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

ቦረና ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 44
➤ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ ከዜሮ ዓመት ጀምሮ
➤ የሥራ ቦታ፦ ቦረና ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከዛሬ መጋቢት 18/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት

የማመልከቻ አማራጮች፦

ቦረና ዩኒቨርሲቲ የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት ወይም አዲስ አበባ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ወኪል ቢሮ፣ አራት ኪሎ፣ የቀድሞው የጀርመን ባህል ኢንስቲትዩት ህንፃ ቢሮ ቁ. 15 የማመልከቻ ደብዳቤ፣ ሲቪ እና የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
#የካቲት_12_ሆስፒታል_ሜዲካል_ኮሌጅ

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ Post Basic Neonatal nursing, Post Basic ECCN nursing, Post Basic BSc in Medical Laboratory Science እና Post Basic Comprehensive nursing በመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ስም ዝርዝራችሁ ከጤና ቢሮ የተላከ በሙሉ የፈተና ቀን መጋቢት 25/2016 ዓ.ም መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል፡፡

ምዝገባ፦ መጋቢት 30 እና ሚያዚያ 1/2016 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው፦ ሚያዚያ 2/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለተመደቡ ሬዚደንት ሐኪሞች ዛሬ ሊሰጠው የነበረውን ኦረንቴሽን ወደ መጪው ሰኞ አስተላለልፏል፡፡

ገለፃው ሰኞ መጋቢት 23/2016 ዓ.ም ጠዋት 2፡00 ሰዓት ይሰጣል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ በሀዲያ ዞን፣ በከምባታ ዞን እና በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ለሚገኙና ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወሰዱ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ከሁለቱም ዞኖች ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ 432 መምህራን በ54 ማዕከላት ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ሳምንታት የማጠናከሪያ ትምህርቱን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ የተፈታኝ ተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ለማሳደግ እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡

@tikvahuniversity
8ኛው ሀገር አቀፍ የሕግ ትምህርት ቤቶች አምሳለ-ችሎት ውድድር ዛሬ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መካሔድ ይጀምራል።

በውድድሩ በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለቃል ክርክር ያለፉ 12 የሕግ ትምህርት ቤቶች ይወዳደራሉ።

ተወዳዳሪዎቹ "የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የባህር በር የማግኘት መብትና ዓለም አቀፍ ሕግ" በሚለው ጭብጥ ላይ እንደሚከራከሩ ተገልጿል፡፡

ከመጋቢት 20 እስከ 22/2016 ዓ.ም የሚካሔደው ውድድር በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እና በፍትህ እና ሕግ ኢንስቲትዩት ትብብር ተዘጋጅቷል፡፡

@tikvahuniversity
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ AMS Project Innovation ፈንድ አሸናፊ ሆኗል፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ምህንድስና ሒደት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ሔለን ወልደሚካኤል (ዶ/ር) "Improving Enset Processing and Value Chain for Small-holder Farmers በሚል ርዕስ ባቀረቡት የፈጠራ ሥራ ማሸነፋቸው ተገልጿል፡፡

የተመራማሪዋ ሥራ ከ300 ተወዳዳሪዎች መካከል የመጨረሻ 10 ተሸላሚዎች ውስጥ በመግባቱ፤ ሥራውን ወደማኅበረሰብ ተደራሽ እንዲሆን የሚያግዝ 2.7 ሚሊዮን ብር አሸናፊ ሆኗል፡፡

@tikvahuniversity
2024/11/05 19:01:06
Back to Top
HTML Embed Code: