Telegram Web Link
#ዓለምአቀፍ

የሄይቲው ጠቅላይ ሚኒስትር በ6 ወራቸው ከስልጣናቸው ተባበሩ።

የሄይቲ ጠ/ሚ ጌሪ ኮኒል በ6 ወራቸው ከሥልጣን መባረራቸውን ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው ም/ቤት አስታውቋል።

የምክር ቤቱ ዘጠኝ አባላት የፈረሙት ትዕዛዝ እንደሚያሳየው ከሥልጣን በተባረሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ምትክ ነጋዴ የሆኑትና የቀድሞ የሄይቲ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል የነበሩት አሊክስ ዲዲዬን ሾሟል።

የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ባልደረባ የነበሩት ኮኒል ወደ ሥልጣን የመጡት ሀገሪቱን ከታጠቁ ወሮበሎች እንዲታደጉ ነበር።

ሰውዬው በሄይቲ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ሥልጣን ላይ ይቆያሉ ተብሎ ቢጠበቅም በግማሽ ዓመት ከመንበራቸው ተባረዋል።

ሄይቲ ከአውሮፓውያኑ 2016 በኋላ ምርጫ አካሂዳ አታውቅም።

ሄይቲ በአሁኑ ወቅት ፕሬዝደንትም ሆነ ፓርላማ የላትም።

በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሥልጣን ማንሳት የሚችለው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ብቻ ነው።

ኮኒል ሥልጣን የያዙት ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መጨረሻ ነበር።

እንደ ተመድ መረጃ ፤ በሄይቲ ካለፈው ጥር ጀምሮ በወሮበሎች አመፅ ምክንያት 3600 ሰዎች ሲገደሉ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት መኖሪያቸውን ጥለው ተሰደዋል።

በታጠቁ ወሮበሎች እየታመሰች ያለችው ሄይቲ በዓለማችን እጅግ ደሀ ከሚባሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን እንደ ተመድ መረጃ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ከሀገሪቱ ሕዝብ ግማሽ ያክሉ በቂ ምግብ የለውም።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ከቅጣት በኋላ ካላስተካከሉ የማሸግ እንዲሁም ከዚህ አለፍ ሲል ከዘርፉ እስከማሰናበት እርምጃ ይወሰዳል " - በአ/አ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴሎች እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተጋጆቻቸውን " የተራቆተ " ልብስ የሚያስለብሱ ከሆነ ከ50 ሺህ ብር እስከ #እገዳ የሚደርስ ቅጣት የሚጥል ረቂቅ መዘጋጀቱ ታውቋል። የረቂቁ ስያሜ ፦ " በሆቴል…
#AddisAbaba

የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን  ደንብ መውጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህ ቢሮ አሳውቋል።

ይህ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ የወጣ ነው።

ደንቡ " በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ ነው " ብሏል።

ከደንቡ የአለባበስ ስርአት ውስጥ ለአብነት ፦

ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፤

የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፤

ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ያስቀምጣል፡፡

ቢሮው " ደንብ ቁጥር 178/2017 በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም  በከተማው የሚሰጠው የሆቴል አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ ነው " ብሏል።

ይህ ደንብ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሰማራ ባለሙያ በደንቡ በተደነገገው መሰረት አክብሮ እየሰራ ስለመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ክትትል ይደረጋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር በቅንጅት በመስራት ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደረጋል ነው የተባለው።

መረጃው ከየአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom

💫ከዳር እስከ ዳር አስተማማኙን ኔትወርካችንን እያሰፋን ወደ እናንተ እየቀረብን ነው!🙌👏ከአስተማማኙ ኔትወርካችን ጋር አሁንም በአብሮነት ወደፊት!

አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
TIKVAH-ETHIOPIA
Lecturers Claims and questions -.pdf
🔈#የመምህራንድምጽ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር (ኢመማ) 37ኛ መደበኛ የም/ቤቱን ስብሰባ በአዳማ ባካሔደበት ወቅት ከም/ቤት አባላት ለተለያዩ አካላት ተደራሽ መደረግ ያለባቸው ፦
- የመምህራን የመብት፣
- የጥቅማ ጥቅም
- አጠቃላይ በትምህርት ሥራው ላይ ያሉና መፈታት ያለባቸው ጉዳዮችን አስመልክቶ በስፋት ውይይት ተደርጎ ነበር።

ከም/ቤቱ አባላት ከዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ የተነሱ በርካታ በአሰራር ሊመለሱ የሚገቡ የመልካም አስተዳደርና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ተነስተው ነበር።

በአጭር ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ ምላሽ የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፥ ለአቶ ኮራ ጡሹኔ (በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ) ደብዳቤ ልኳል።

በአጭር ጊዜ ምላሽ የሚሹ የተባሉት ጉዳዮች ምንድናቸው ?

1. የመምህራን የመኖሪያ ቤት ጉዳይ አንዱ ነው።

በ2008 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴርና ኢመማ በጋራ ባዘጋጁት የመምህራን የመኖሪያ ቤት ፓኬጅ በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ፓኬጁ ሥራ ላይ ውሎ በርካታ መምህራን የዚህ ፓኬጅ ተጠቃሚ ተደርገዋል።

ነገር ግን የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከክልሎች ዋና ከተማ አልፈው በዞኖች ጭምር የሚገኙና ከተልዕኮአቸው አንዱ በሆነው በማህበረሰብ አገልግሎት የአካባቢውን ማህበረሰብ እያገለገሉ ያሉ ሆኖ ሳለ ' የፌዴራል ተቋማት ናችሁ ' በሚል የዩኒቨርስቲ መምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ተጠቃሚ ሳይሆኑ እስከ አሁን ቆይተዋል፡፡

ስለሆነም መምህራኑ ጥያቄያቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ስለሆነና በም/ቤቱም በሰፊው የተነሳ ሀሳብ በመሆኑ ከክልልና ከአካባቢ የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ለዩኒቨርስቲ መምህራን ምላሽ እንዲሰጥ ማህበሩ ጠይቋል።

2. በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ በርካታ ዩኒቨርሰቲዎች የማስተማሪያ ሆስፒታል (Teaching Hospitals) አላቸው።

ይሁንና የዩኒቨርስቲ መምህራን በሚያስተምሩበት ተቋም ውስጥ መምህራንም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው የሚታከሙበት በክፍያ ስለሆነ ይህ አሰራር መምህራን በተቋሙ ላይ የባለቤትነት ስሜት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ብቻም ሳይሆን ፍትሃዊነት የጎደለውና የመምህራንንም የሥራ ተነሳሽነት ይቀንሳል፡፡

ስለሆነም የዩኒቨርስቲ መምህራንና ቤተሰቦቻቸው በማስተማሪያ ሆስፒታሎች ውስጥ ነፃ ህክምና የሚያገኙበት መንገድ እንዲመቻች ጠይቋል።

3. ዩኒቨርሰቲዎች በሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ ላይ የሚገኙና አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች የበረሀና የውርጭ አበል ጭምር በሌሎች ሴክተሮች ሠራተኞች የሚከፈልባቸው ሆነው ሳለ ዩኒቨርስቲ መምህራን ግን የበረሀም ይሁን የውርጭ አበል አለመከፈለ ቅሬታ እየፈጠረ ስለሚገኝ መፍትሄ እንዲሰጠው ጠይቋል።

እነዚህ ጥያቄዎች የዩኒቨርስቲ መምህራን በም/ቤቱ ላይ ካነሷቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ የሚሹና ሚኒስትር ዴኤታው በም/ቤቱ ተገኝተው በነበረበት ወቅትም ጥያቄዎቹ የተነሱ ናቸው።

እሳቸውም ጥያቄዎቹ የተነሱበትን አውድ መገንዘባቸውን ማህበሩ በደብዳቤው አመልክቷል።

ስለሆነም አፋጣኝ የሆነ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቋል።

ቀደም ሲልም የቀረቡት የዩኒቨርስቲ መምህራን ጥያቄዎች በተለይ የኑሮ ውድነት እና የጥቅማ ጥቅም እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከማህበሩ ጋር መድረክ ተፈጥሮ መፍትሄ እንዲበጅላቸውም ጥሪውም አቅርቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

" ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ " በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየሰራው ነው " ሲል ገልጿል።

ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ የቁጥጥር ስራው ከዚህ ቀደምም የነበረ ቢሆንም በዘመቻ መልክ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ዘመቻ ሲባል ፦
- ወደ ቫት ስርዓት ውስጥ ያልገቡትን ማስገባት ፣
- ፈቃድ የሌላቸው ፈቃድ እንዲያወጡ ማድረግ፣
- ደረጃቸው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ የማይሰጡትን ደረሰኝ አስፈቅደው እና አሳትመው መጠቀም እንዲጀምሩ ማስቻልን ያካትታል።

የቁጥጥር ስራው በተለይም በገበያ ሞሎች ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ታውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም አንዳንድ ነጋዴዎች እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ " ንብረት ለመውረስ እና ሱቆችንም ለመዝጋት ነው " በሚል ሱቃቸውን ዘግተዋል ንብረትም ወደ ሌላ ቦታ አዙረዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ  በመርካቶ አካባቢ የሚሰሩ ነጋዴዎች  " ከምንም በፊት ያሉትን ችግሮች ማወቅ ይገባል። ቸርቻሪውን ማነጋገር ያስፈልጋል። ችግሮቹን ለመቅረፍ መሰራት አለበት። " ብለዋል።

" ነጋዴው ከአስመጪ እቃ ሲገዛ አስመጪው ከዋጋው በታች ደርሰኝ ይሰጣል አልያም ጭራሽ ላይሰጥም ይችላል ፤ ምንም  አይነት የግዢ ደረሰኝ ባላገኘበት ' ነጋዴው ሱቅ ውስጥ ያለዉን ንብረት እንወርሳለን ' ማለት ትክክል አይደለም " ሲሉ አክለዋል።

" መንግሥት ታች ያለው ነጋዴ ላይ ጣቱን ከመቀሰር አስመጪዎቹን ደረሰኝ እንዲሰጡ ማድረግ እና ቸርቻሪውን ማወያየት ያስፈልጋል " ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አንዳንድ የራሳቸው የገቢዎች ሰዎች ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ቸርቻሪዎችን ማስጨነቅ እንደሚቀናቸው ቃላቸውን የሰጡ አንዳንድ ነጋዴዎች ጠቁመዋል።

ያለ ደረሰኝ ግብይት በሚፈጸምበት ወቅት የገንዘብ ድርድር ሁሉ እንደሚያደርጉና ያሉ ችግሮች ስር የሰደዱ እንደሆኑ ገልጸዋል።

" ከምንም በላይ ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይኖር ከላይ ጀምሮ መስራት እንደሚገባ ነጋዴው በደረሰኝ ከገዛ በደረሠኝ እንደሚሸጥ ከላይ ግን እጃቸው የረዘመ ሰዎች ስላሉ መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ " አመልክተዋል።

ሁኔታዎችን በመጠቀም በህግ ሰበብ ከነጋዴው ገንዘብ የሚቀበሉና ሙስና የሚሰሩ ህገወጥ ተግባራትንም የሚያባብሱ በገቢዎች አካባቢ ያሉ ሰዎች እንዲታረሙ መሰራት እንዳለበት አክለዋል።

ዛሬ በመርካቶ " ያለ ደረሰኝ ለምን ሸጣችሁ " በሚል ንብረት ይዘው የሄዱም እንዳሉ በመጠቆም በዚህ ምክንያት ሱቆች ተዘግተው እንደነበር ጠቁመዋል።

ሌላ አንድ በቲክቫህ ኢትዮጵያ የሃሳብ መለዋወጫ መድረክ ሃሳባቸውን ያካፈሉ ዜጋ ፥ አስመጪዎች እና አምራቾች ለጅምላ ነጋዴ እና ቸርቻሪ ያለደረሰኝ ስለሚሸጡ ያለደረሰኝ የተገዙ እቃዎች እንደሚኖሩ ገልጸዋል።

" ነጋዴዎች እቃዎቻቸው ሳይወዱ ደረሰኝ ስለሌላቸው እንዳንወረስ ብለው ወደ ሌላ ቦታ ያሸሻሉ ሱቅም ለመዝጋት ይገደዳሉ  " ብለዋል።

" ዋናው ስራ መጀመር ያለበት ከአስመጪዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች መሆን አለበት ፤ እነሱን በሚገባ ከተቆጣጠሩ እና እርምጃ ከወሰዱ በኋላ በተዋረድ ጅምላ ነጋዴዎች እና ቸርቻሪዎችን መቆጣጠር ይገባል " ብለዋል።

" የችግሩ ምንጭ ከሆኑት አስመጭዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች ጠበቅ ያለ እርምጃ መወሰድ አለበት " ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

" በዛሬው ዕለት በመርካቶ አካባቢ ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው " የሚል ውዥንብሮች በመፈጠራቸው አንዳንድ ነጋዴዎችን ግርታ ውስጥ መክተቱ ተናግሯል።

ስለ ጉዳዩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽን አነጋግሯል።

ዳይሬክተሩ ምን መለሱ ?

➡️ " ጠዋት ሱቆች ሁሉ ተዘግተዋል " ተብሎ ተወርቶ በአካል ዞሬ አይቻለሁ የተወሰኑ ሱቆች የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተዘጉ የሚመስሉ አሉ ነገር ግን መደበኛ ሥራ ቀጥሏል።

➡️ " በዚህ ደረጃ ተዘግቷል ለማለት እይቻልም ተዘጋ የሚባለው ምን ያህል ሱቅ ሲዘጋ ነው ? አንድ ቤት ሁለት ቤት ተዘግቶ ይሆናል ነገር ግን አብዛኛው እየሰራ ነው።

➡️ ህገ ወጥነትን ማስቀጠል የሚፈልግ አካል  አለ። ሆን ብሎ ' የሆነ ነገር ተሰርቷል፣ ሊሰራ ነው ' የሚል ውዥንብር መፍጠር የሚፈልግ አካል እንዳለ ነው የተረዳሁት።

➡️ ቁጥጥር ሊደረግ ነው በተለይ አስመጪ እና አከፋፋይ ላይ ሲባል ቸርቻሪ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ አሉ፣ በትላንትናው ዕለትም የሚሸሹ ነጋዴዎች ገጥመውናል ያለፍቃድ ይነግዱ የነበሩ ናቸው ብንጠየቅ መልስ የለንም በሚል ስጋት ነው። ሱቃቸውን ቢዘጉም እነሱ ናቸው የሚሆኑት።

➡️ ተዘግቷል የሚለውንም እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል በእርግጥ የተዘጋ ነው ወይስ ነጋዴው በsocial ችግር ሱቃቸውን ዘግተው ስለሌሉ ነው የሚል ጥርጣሬ የሚያጭር ስለሆነ የተዘጉ አይደሉም ወደሚል ድምዳሜ ነው የደረስነው።

➡️ ይርጋ ሃይሌ የገበያ ሞል ላይ ከ15 ቀን በፊት ኮንትሮባንድ ስለነበረ ጎምሩኮች በርብረዋል ደረሰኝ የሌለውን ወርሰዋል ደረሰኝ ያለውን ጥለው ወጥተዋል።

➡️ የገበያ ሞሉ ላይ እቃዎችን መለየት አስቸጋሪ ስለነበር እና ሰዎቹም ተባባሪ ስላልነበሩ ለጊዜው ታሽጎ ነበር። በአሁኑ ሰዓት ሀሉም ተከፍተዋል። የቀረ ካለ በንግድ ቢሮ በኩል ፈቃድ ያልነበረው በመሆኑ በተወሰደ እርምጃ ነው።

➡️ ታሽገው የነበሩ አብዛኛው ሱቆች ተከፍተዋል። እስካሁን ያልተከፈተ ካለ ፈቃድ ስላላወጣ ነው የሚሆነው በተረፈ እቃ የሚወረሰው ኮንትሮባንድ ሲሆን ብቻ ነው።

➡️ ሁሉም ሰው ደረሰኝ ስለማይሰጥ የሚመለከተው ብቻ ነው ደረሰኝ እንዲሰጡ የሚጠበቀው መስጠት የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች ደረሰኝ እየሰጡ ግብይታቸውን ይቀጥሉ።

➡️ " እቃችሁ እየተወረሰ ነው፣ ሊወረስብን ነው" የሚሉ አካላት እቃቸው ምን ስለሆነ ነው የሚወረሰው ? እንደዚህ የሚሉ አካላት ኮንትሮባንድ ስለሆነ ይመስላል።

➡️ ያለደረሰኝ አትግዙ ፣የሚሸጥላችሁን ጠቀሙ እኛ ደግሞ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽምን አካል እንቆጣጠራለን ብለናል የምንከታተላቸውም ለዛ ነው።

➡️ እቃ ለመውረስ የህግ መሰረት ያስፈልጋክ። እቃ የሚወረሰው የታክስ እዳ ማካካሻነት ከተያዘ ብቻ ነው።

➡️ ግብይት ላይ ያለ እቃን የታክስ ማካካሻ ብለን የምንወርስበት ምክንያት የለንም። ክፍተት ያለበትን ነጋዴ ለማወናበድ የሚሮጥ ሌላ ጥላ የሚፈልግ አካል የሚያወራው ወሬ ነው።

➡️ " ያለደረሰኝ አትሽጡ " አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም። ይህም ለነጋዴዎች በደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#LG_KOICA_Hope

LG-KOICA Hope የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቲቪቲ መግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተማሪዎች በICT እና Electronics የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን #በነጻ ማስተማር ይፈልጋል።

ኮሌጁ በዚህ ዙር እስከ 150 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የተዘጋጀ ሲሆን የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር የሥራ ዕድል አማራጮችም አካቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውና መስፈርቱን ለሚያማሉ የተመረጡ ተማሪዎች የምግብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎችን የሚሸፍን ይሆናል።

የማመልከቻ ጊዜና ቦታ : ከጥቅምት 11 - ህዳር 06 2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 - 11፡00 ሰዓት ሰሚት ኮንዶሚኒየም 3ኛ በር

ለተጨማሪ መረጃ - 011-6-67-75-64 011-6-66-18-29
ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ !

ሽው ወደ  ስራ ፣ ሽው ወደ ቤት ፣ ሽው ወደ ጉዳዮ

የጃፓን ድርጁት የሆነው ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ

የታክሲ ሰልፍ እንዲሁም የነዳጅ ወጪ ለመቀነስ እና ለማስቀረት የዘመኑን ምርጥ ቴክኖሎጂ ሊትየም አዮን ባትሪ የተገጠመላቸው ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ከነሙሉ መለዋወጫ አቅርቦሎታል።
•⁠  ⁠በአንድ ጊዜ ቻርጅ እስከ 150ኪሜ መጓዝ የሚችሉ
•⁠  ⁠ለሙሉ ቻርጅ 10ብር ብቻ ሚጠይቁ
•⁠  ⁠⁠150ኪሎ ተሸክመው በሰአት እስከ 60ኪሜ  የሚሄዱ
•⁠  ⁠ለእለት ተለት ጉዞ ቢሉ ፣ አልያም ለዲሊቨሪ ስራ የሚሆኑ

ይሂዱ > ይጎብኙ > ይግዙ!

ለበለጠ መረጃ
📍ሾው ሩም: ጎፋ ገብርኤል
📲 ስልክ: 0938022222
🌐 ethiopia.dodai.co

*TikTok Page*: https://www.tiktok.com/@dodai_et?is_from_webapp=1&sender_device=pc
- *Telegram Page*: https://www.tg-me.com/+z09SxQgb6vsyNzU8
(ኢትዮ ቴሌኮም)

#5ጂ በቢሾፍቱ ተጀመረ!!

ኩባንያችን የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የሆነው የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል አገልግሎት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ ማስጀመሩን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል!

በዛሬው እለት ይፋ ያደረግነው የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ ኩሪፍቱ ወተር ፓርክ፣ በምስራቅ ኢንዱስትሪ ዞን፣ ሰንሻይን፣ ግራር ሜዳ እና የረር የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበር የሚገኙ አካባቢዎች የሚሸፍን ነው፡፡

የአገልግሎቱ ተግባራዊ መሆን እያደገ የመጣውን የደንበኞች ዳታ ፍላጎት ለማስተናገድ ከማስቻሉ ባሻገር ተሞክሮን የሚጨምሩ የዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ የዜጎችን ህይወት ለማዘመን እና ቢዝነስን ለማቀላጠፍ እንዲሁም አዳዲስ የዲጂታል ሥራ እድሎችን በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል፡፡

የ5ጂ አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነት ያለው፣ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን በእጅጉ በመቀነስ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎችን ከማዘመን በተጨማሪ ለሀገራችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ እንደ ግብርና፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት ያሉ ዘርፎችን አሰራር በማቀላጠፍ ተወዳዳሪነትን ይጨምራል፡፡

ክቡራን ደንበኞቻችን የ5ጂ አገልግሎትን ለማግኘት የሚያስችሉ ቀፎዎች በመጠቀም በእጅግ ፈጣኑ ኔትወርክ አስደሳች ተሞክሮ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡

ቀደም ሲል የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎትን በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂግጂጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና እና አርባ ምንጭ ከተሞች ማስጀመራችን ይታወሳል፡፡ 

አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ላይ

ለተጨማሪ: https://bit.ly/48PskNK
#Bishoftu #5G
TIKVAH-ETHIOPIA
#ረቂቅአዋጅ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 ለማሻሻል የወጣው ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል። የተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ? ምን ዋና ዋና ማሻሻያ ተደርጓል ? 🔵 ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን የስራ አመራር ቦርድ አሰያየም እና አወቃቀር ጋር በተያያዘ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። በአዋጁ የተዘረጋው የቦርድ አሰያየምና አወቃቀር የተንዛዛ እና ረጅም ሂደትን…
" በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይት ሳይደረግበት ወደቋሚ ኮሚቴ መመራቱ በጉዳዩ ላይ የሕዝብን ድምፅ በተገቢ ላለማካተቱ ሁነኛ ማሳያ ነው !! " - የጋዜጠኞች የሙያ ማህበር እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች

በሚዲያ ሕጉ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ አሳሳቢ ይዘት ላይ የጋዜጠኞች የሙያ ማህበር እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የጋራ መግለጫ ልከዋል።

በዚህም ፥ " በአስፈፃሚው አካል ተረቅቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ የቀረበው ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ በሥራ ላይ የሚገኘውን የመገናኛ ብዙኃን ሕግ በርካታ አንቀፆች ይዘትና መንፈስ የሚቀይር መሆኑን ተገንዝበናል " ብለዋል።

ረቂቅ ማሻሻያው የአካሄድና የይዘት ግድፈቶች በስፋት የሚስተዋሉበት እንደሆነም አመልክተዋል።

" በረቂቁ ማሻሻያ ላይ ምንም ዓይነት የሕዝብ ውይይቶች ባለመከናወናቸው የሲቪል ማኅበረሰቡን፣ የሚዲያ መያተኞችን እንዲሁም የሌሎች መብቶች ተሟጋቾችንና የማኅበረሰብ ድምፆች እንዳይሰሙ አድርጓል " ሲሉ አክለዋል።

ማሻሻያውን ለማዘጋጀት የተሔደበት መንገድ ግልጽነትና አሳታፊነት የጎደለው ነው ብለውታል።

የረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ገለልተኛ አካል በተሠራ ጥናት ስለመለየቱ የቀረበ ማስረጃም እንደሌለ አንስተዋል።

በሌላ በኩል የረቂቅ አዋጁ የተለያዩ አንቀፆች በሥራ ላይ የሚገኘው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ጥበቃ የሚሰጣችውን ነጻነቶች የሚገድብና የሚዲያ ተቆጣጣሪውን አካል በአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ውስጥ ይከተዋል የሚል ስጋት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ለምሳሌ የነባሩን አዋጅ ፦
አንቀጽ 8 (2) ዋና ዳይሬክተሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለሚሾምበት የሚደነግገው ክፍል፤
አንቀጽ 9 (1 እና 2) የቦርዱ አባላት እጩዎች የሚመለመሉበትና የሚፀድቁበት ሒደት ለሕዝብ ግልጽ መሆን እንዳለበት የሚደነግገው ክፍል፤
አንቀጽ 11 (6) የቦርዱ አባላት ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ወይም ተቀጣሪነት የሚከለከሉበትን ሁኔታ የሚደነግገው ክፍል መሰረዝ ዋና ዋና የይዘት ለውጦች ናቸው ብለዋል።

በተያያዘ በአዲሱ ማሻሻያ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሹመት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መሰጠቱ፤ እንዲሁም በነባሩ አዋጅ ለቦርዱ ተሰጥተው የነበሩት የፈቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት አለማደስ፣ ማገድ፣ መሰረዝ፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት የመሳሰሉት ኃላፊነቶች አሁን ለባለሥልጣኑ መሰጠታቸው ሥልጣንን ጠቅልሎ ለአንድ አካል የመስጠትና በሒደትም ላልተገባ ተፅዕኖ በር የሚከፍት ነው ብለዋል።

በተጨማሪ ከላይ የተጠቀሱት የማሻሻያው አንቀፆች በአንድነት ሲነበቡ የነባሩን አዋጅ አንቀጽ 7 (የባለሥልጣኑን ገለልተኝነትና ነፃነት) ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ረቂቅ አዋጅ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በተያያዘም ረቂቅ አዋጁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚቀርበበት ወቅት ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የምክር ቤት አባላት ጭምር ተቃውሞ ገጥሞት የነበረ ቢሆንም በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይት ሳይደረግበት ወደቋሚ ኮሚቴ መመራቱ በጉዳዩ ላይ የሕዝብን ድምፅ በተገቢ ላለማካተቱ ሁነኛ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።

በመሆኑም ከረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ ሒደት ጋር በተያያዘ በርካታ ጉዳዮች እንደሚያሳስባቸው ገልጸው አስችኳይ መፍትሔ ሊፈለግላቸው እንደሚገባ በአጽንኦት አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
#ትኩረት🚨

" የጤና ተቋሙ ሳይፈርስ ከላይ ያሉ አካላት አስቸኳይ ድጋፍ ቢያደርጉ መልካም ነው "  - ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በክልሉ ተፈጥሮ ከነበረው ጦርነት በፊት ለመድሃኒትና ለላብራቶሪ ግብዓቶች ይመደብለት የነበረው በጀት ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ነበር።

በሆስፒታሉ የመድኃኒት እና የላብራቶሪ መመርመሪያ ግብዓቶች እጥረት ስለማጋጠሙ በተደጋጋሚ ሲነገር ቢቆይም ችግሩን እስካሁን መቅረፍ እንዳልተቻለ ተነግሯል።

በሆስፒታሉ ላይ ላጋጠመው እጥረት ለዩኒቨርሲቲው ይመደብ የነበረው በጀት በግማሽ መቀነሱ እንደምክንያት ይነሳል።

ለሆስፒታሉ ለመድኃኒትና ለላብራቶሪ መመርመሪያ ግብዓቶች አቅርቦት በ2016 በጀት ዓመት ተመድቦለት የነበረው 18.9 ሚሊየን ብር ሲሆን ለ 2017 በጀት ዓመት የተመደበለት ደግሞ 30 ሚሊየን ብር ብቻ ነው።

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይደር ኮምፕረንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስተዳደር እና ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይለስላሴ በርኸ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ሆስፒታሉ በ2016 በጀት ዓመት ከ ኢትዮጵያዊ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በብድር የወሰደው መድኃኒት ከ 60-70 ሚሊየን ብር ይደርሳል ብለዋል።

በብድር የወሰደውን የመድኃኒት ክፍያ ሆስፒታሉ መክፈል ባለመቻሉ 14.3 ሚሊየን ብር ከጤና ሚንስቴር ለመድኃኒት አቅራቢ ድርጅት እንዲከፈል ሆኗል።

ሆስፒታሉ የተወሰነ ክፍያ የከፈለ ቢሆንም ያልተከፈለ ከ 40 ሚሊየን ብር በላይ ክፍያ እዳ ከ 2016 ወደ 2017 በጀት ዓመት የተላለፈበት ሲሆን በዚህ ምክንያት ከዚህ በኋላ ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መድኃኒቶችን በካሽ እንጂ በብድር እንደማያገኝ ተነግሮታል።

ሆስፒታሉ ከውስጥ ገቢው እዳውን መክፈል ለምን ተሳነው ?

ዶ/ር ኃይለስላሴ እንደሚሉት በዓይደር ሆስፒታል የሚታከሙ ታካሚዎች ከ 80-90 በመቶ የነጻ ታካሚዎች ናቸው።

" ከፍለው መታከም የማይችሉ ታካሚዎች የደሃ ደሃ መሆናቸውን ከወረዳቸው ያጽፋሉ ወረዳውም ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በሚገባው ውል መሰረት ጤና ቢሮው ከእኛ ጋር ውል ያስራል ያከምናቸውን ታካሚዎችም በ3 ወር ወይም በ6 ወር ለሆስፒታሉ ይከፍላል" ብለዋል።

ስለዚህ የምናክማቸው ታካሚዎች እነርሱ በቀጥታ ባይከፍሉም ከጤና ቢሮው ክፍያው እንዲፈጸም የሚደረግ በመሆኑ ነጻ ናቸው ማለት አይደለም ብለዋል።

ይሁን እንጂ ሆስፒታሉ በተጠቀሰው መንገድ ሲያክም ቆይቶ ክፍያው እንዲፈጸምለት ለጤና ቢሮው ጥያቄ ቢያቀርብም "በትግራይ የምዕራብ እና የደቡብ አካባቢዎች የሚገኙ አንዳንድ ወረዳዎች በትግራይ ስር ስላልሆኑ እና በርካታ መጠለያ ጣቢያዎች በመኖራቸው እንዲሁም ታካሚዎችም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ በመሆናቸው ከየትም አምጥቼ ገንዘብ መሰብሰብ አልቻልኩም " የሚል ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል።

በዚህም ምክንያት ሆስፒታሉ ከጤና ቢሮው ሊከፈለው የሚገባ በርካታ ሚሊየን ብር ስለቀረበት መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ላይ ያለበትን የ40 ሚሊየን ብር በላይ እዳ መክፈል እንዳልቻለ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በኩልም የማይገኙ እንደ የስነ-ልቦና እና የካንሰር መድሃኒቶች ፣ ካቴተር ፣ ለመስፋት የሚያገለግሉ ስቲቾች (Stitches) እንዲሁም እንደ ማግኒዢየም ሰልፌት ያሉ መድኃኒቶችም መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በአገልግሎቱ በኩል አይገኙም የተባሉትን መድኃኒቶች ለመግዛት ወደ ሌሎች አቅራቢዎች ለግዢ ጨረታ ይወጣል ፤ ከውጭ ሲገዛ በጣም ውድ በመሆኑ ሳቢያ ሆስፒታሉ ለመድኃኒት ካለው ትንሽ በጀት ጋር ተደምሮ ለገንዘብ እጥረት እንዳጋለጠው ጠቁመዋል።

አሁን ካለው የኑሮ ውድነት ጫና ጋር ተደምሮ ከዚህ በፊት ለዓመት ያስገዛ የነበረ ገንዘብ ለሁለት እና ሦስት ወርም አይቆይም ብለዋል።

ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ሆስፒታሉ እዳውን መክፈል እንደተሳነው ገልጸዋል።

" በካሽ ካልሆነ በብድር ይሰጥ የነበረ መድኃኒት ከዚህ በኃላ እንደሌለ ከአገልግሎቱ ተነግሮናል " ብለዋል።

በዚህም ሳቢያ በሆስፒታሉ በተለይም የስነ አዕምሮ ፣ የማደንዘዣ እና ለመስፋት የሚያገለግሉ ግብዓቶች እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ማጋጠሙን ተሰምቷል።

በሆስፒታሉ የማይገኙ መድኃኒቶችን ታካሚዎች ከውጭ በውድ ዋጋ እንዲገዙ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

እንደሆስፒታሉ መረጃ በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የስነ አዕምሮ መድኃኒቶች ፍላጎት እየጨመረ ነው።

ሆስፒታሉ ካለበት የበጀት እጥረት በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የባለሞያዎች ፍልሰት እንዳጋጠመው የተሰማ ሲሆን ከህክምና ት/ቤቱ ብቻ ከ300 በላይ ሐኪሞች መሰደዳቸውን ተናግረዋል።

አብዛኛዎቹ ባለሞያዎች የተሰደዱት ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ነው።

ዶክተር ፥ " አብዛኛው ሃኪም የሄደው ወደ ሶማሊያ፣ ፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ነው ለመኖር አስቸጋሪ ቢሆኑም የሚከፈላቸው ክፍያ ጥሩ ስለሆነ ለመኖር አዳጋች ወደ ሚባሉ ቦታዎች እየተሰደዱ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሆስፒታሉ ለህክምና ባለሞያዎች ያልተከፈለ የ17 ወር ደሞዝ እና የ22 ወር የትርፍ ሰዓት ክፍያ እስካሁን እንዲከፈል አልተደረገም።

በሆስፒታሉ ስላጋጠመው እዳ በቀጣይ ምን ታስቧል ? ለሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ " ምንም እንኳን በጽሁፍ ያቀረብነው ጥይቄ ባይኖርም ጤና ሚኒስቴር ድጋፍ እንዲያደርግልን ወይም የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የእዳ ስረዛ እንዲያደርግልን ለመጠየቅ እያሰብን ነው " ብለዋል።

" ሆስፒታሉ ከሚገኝበት ውስብስብ ችግር ምክንያት የጤና ተቋሙ ሳይፈርስ ከላይ ያሉ አካላት አስቸኳይ ድጋፍ ቢያደርጉ መልካም ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በኩል የማናገኛቸው መድኃኒቶች አሉ ስለሚለው ቅሬታ እና ሆስፒታሉ ስላለበት እዳ ምን ታስቧል ? የሚለውን በሚመለከት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመቀሌ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አለማየሁ ገብረማርያምን አነጋግረናል ምላሻቸው በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2024/11/15 05:49:12
Back to Top
HTML Embed Code: