Telegram Web Link
#ጥንቃቄ🚨

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት የጨቅላ ህፃናት እንዳይጠቀሙት የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት ኖቫርቲስ ፋርማ ሽዌይዝ AG/ Novartis Pharma Schweiz AG በተባለ የገበያ ፍቃድ ባለው የመድኃኒት አምራች ፋብሪካ የሚመረት ነው።

ቴግሬቶል (ካርባማዜፔይን) 100 mg/5ml Oral Suspension (OS) የተሰኘው መድኃኒት አብዛኛውን ጊዜ አጠቃላይ ለሚጥልና ከፊል መንቀጥቀጥ/ management of generalized tonic clonic and partial seizures ለማከም የሚያገለግል ነው።

ይሁን እንጂ የተጠቀሰው መድኃኒት በውስጡ በሚይዘው ፕሮፓይሊን ግላይኮል (propylene glycol) የሚባል ንጥረ-ነገር መጠን ምክንያት ለጨቅላ ሕፃናት ማለትም ከ4 ሳምንታት በታች ለሆኑ ሕፃናት ወይም በሶስት ወራት የመወለድ ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት ሊወስዱት እንደማይመከር ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

ተቋሙ ፥ በዚህ ምርት ውስጥ ከሚገኙት ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው ፕሮፓይሊን ግላይኮል ለምግብ እና ትንባሆ ምርቶች እንዲሁም ለፋርማሲዩቲካል እና መዋቢያዎች በአጠቃላይ በአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (FDA) ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ይታወቃል ብሏል።

ይሁንና በዚህ ምርት ውስጥ ያለው መጠን በዚህ የማሳወቂያ መልዕከት ላይ ከተጠቀሱት ለጨቅላ ሕፃናት እና ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ ከደህንነት ገደብ በላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ነው ያለው።

ስለሆነም ይህንን መድኃኒት በጨቅላ ሕፃናት ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ መጠቀም ጉዳቱ ከጥቅሙ የሚያመዝን በመሆኑ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች መድኃኒቱን ለተጠቀሱት የእድሜ ክልል ከማዘዝ እና ከማከፋፈል እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ህብረተሰቡም መድኃኒቱን እንዳይጠቀም መልዕክት አስተለልፏል።

@tikvahethiopia
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ናቸው የተቀበሏቸዋል።

ሩቶ በአዲስ አበባ ቆይታቸው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በ ' World Without Hunger ' ጉባኤ ላይ ይካፈላሉ።

የሀገራቸው ልጅ እና በሀገራቸው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ወቅት ብርቱ ተፎካካሪያቸው የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ዕጩ ሆነው ይፋ በሚደረጉበት ስነስርዓት ላይ እንደሚገኙ የኬንያ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ናቸው።

ሩቶ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት ደቡብ ሱዳን ጁባ ነበሩ። ጁባ ሄደው የነበረው በሀገሪቱ የሰላም ሂደት ላይ ከፕሬዜዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ለመነጋገር ነው።

ሩቶ ከጁባው ቆያታቸው በኃላ በይፋ የወጣ መረጃ ሳይኖር ምሽት ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል።

የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው።

ሌቪት ፥ ትራምፕ በአሜሪካ ህዝብ ዘንድ አስደናቂ የተባለ ድል ማስመዝገባቸውን ገልጸው " ይህ ድል ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ ' ትዕዛዝ ' እንዲሰጡ ያስችላቸዋል " ብለዋል።

ይህም ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት / በገፍ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ (ማስ ዲፖርቴሽን) እንደሆነ ጠቁመዋል።

አንዳንድ ሚዲያዎች ይህ ሰነድ አልባዎችን በብዛት ከአሜሪካ የማስወጣቱ /ማስ ዲፖርቴሽን/ ተግባር የትራምፕ የመጀመሪያው ቀን ስራ ይሆናል ብለዋል።

ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ሰነድ የሌላቸውን ሰዎችን በሚመለከት " ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ሲሉ ቃል ገብተው ነበር።

አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው።

#TikvahEthiopia
#USA #massdeportation

@tikvahethiopia
ነጻ ትምህርት ☑️

#LG_KOICA_Hope

LG-KOICA Hope የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቲቪቲ መግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተማሪዎች በICT እና Electronics የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን #በነጻ ማስተማር ይፈልጋል።

ኮሌጁ በዚህ ዙር እስከ 150 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የተዘጋጀ ሲሆን የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር የሥራ ዕድል አማራጮችም አካቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውና መስፈርቱን ለሚያማሉ የተመረጡ ተማሪዎች የምግብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎችን የሚሸፍን ይሆናል።

የማመልከቻ ጊዜና ቦታ : ከጥቅምት 11 - ህዳር 06 2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 - 11፡00 ሰዓት ሰሚት ኮንዶሚኒየም 3ኛ በር

ለተጨማሪ መረጃ - 011-6-67-75-64 011-6-66-18-29
ሞኤንኮ ፥ በኢትዮጵያ የቢዋይዲ (BYD) ኤሌክትሪክ እና ሃይብሪድ ተሸከርካሪዎች ይፋዊ አከፋፋይ መሆኑን ገለጸ።

በኢንችኬፕ ኩባንያ ስር የሚተዳደረው ሞኤንኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ ፥ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቴክኖሎጂ ዓለም አቀፍ መሪ ከሆነው ቢዋይዲ (BYD) ጋር በኢትዮጵያ የቢዋይዲ የኤሌክትሪክ እና ሃይብሪድ ተሸከርካሪዎች ዋና አከፋፋይ ለመሆን የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙን ገልጿክ።

በስምምነቱ ሞኤንኮ በኢትዮጵያ በዋናነት የቢዋይዲ (BYD) ተሽከርካሪዎችን የሚያከፋፍል ይሆናል።

ሞኤንኮ ከታህሳስ 2017 ጀምሮ ለአካባቢ አየር ተሰማሚ እና በቴክኖሎጂ የተራቀቁ የቢዋይዲ ተሸከርካሪዎችን ከአስተማማኝ ጥገና ፣ መለዋወጫ እና ዋስትና ጋር እንደሚያቀርብም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

" ይህ ስምምነት ዘላቂና አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን የማስተዋወቅ እና ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል ' ብሏል።

የኢንችኬፕ አፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ፍራንሲስ አግቦንላሆር ፥ " ይህ አጋርነት ለኢትዮጵያ የተሸከርካሪ ኢንዱስትሪ ወሳኝ አስተዋጽዖ ያበረክታል ፤ ይህም የአዳዲስ ፈጠራ መስፋፋት እና ታዳሽ ሀይልን በመጠቀም ዘላቂ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎትን ያፋጥናል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#ጥናት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሥር የሚንቀሳቀሰው የጄኖሳይድ አጣሪ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው አዲስ ጥናት በክልሉ የሚገኙ የሥራ አጦች ቁጥር እጅግ አሻቅቧል።

የአጣሪ ኮሚሽኑ ሰነድ ምን ይላል ?

የነፍስ ወከፍ ገቢ ከጥቅል ክልላዊ ምርት አኳያ (GDP Per Capita) ከጦርነቱ በፊት ነበረ ከተባለበት 845 ዶላር ወደ 10.2 ዶላር አሽቆልቁሏል።

የድህነት ምጣኔ ከ29.6 በመቶ ወደ 91.09 በመቶ አሻቅቧል።

የምግብ ደኅንነት ዋስትናን ማስጠበቅ ምጣኔ ከ74.20 በመቶ ወደ 18.73 በመቶ ወርዷል።

አጠቃላይ በየዓመቱ በአማካይ የሚሰበሰብ ሰብል በፊት ከነበረው 20,633,070 ኩንታል ወደ 5.2 ሚሊዮን ኩንታል ዝቅ ብሏል።

የአትክልት ዋጋ ግሽበት ከ8.5 በመቶ ወደ 179.8 በመቶ ከፍ ብሏል።

ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ሆነው ከቀረቡት መካከል አንዱ የሆነው የሥራ አጦች ምጣኔ ነው። ይህም ከጦርነቱ ጅማሮ በፊት ከነበረበት 17 በመቶ በአሁኑ ወቅት ከፍ ብሎ 74.1 በመቶ ላይ ደርሷል።

ኮሚሽኑ ያቀረበው የጥናት ውጤት የክልሉ ወጣቶች ማኅበር በተናጠል ባደረገው ጥናት ግኝት ላይም ተመላክቷል።

የማኅበሩ የጥናት ውጤት ምን ይላል ?

🔴 የሥራ አጥ ምጣኔው ባለፈው ዓመት ከነበረበት 81 በመቶ በዘንድሮው ዓመት ዝቅ ብሏል።

🔴ባለፈው ዓመት በክልሉ ከነበሩ 10 ወጣቶች ስምንቱ ሥራ አጥ ነበሩ።

🔴 በባለፈው ዓመት ጥናት በክልሉ ከነበሩ አጠቃላይ ወጣቶች 40 በመቶ ያህሉ ቀዬአቸውን ለቀው ሥራ ፍለጋ የመሰደድ ፍላጎት እንዳላቸው ተጠንቷል። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 54 በመቶ ያህሉ ከ29 እስከ 35 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ምርታማ የሚባሉ ወጣቶች ናቸው።

🔴 በያዝነው ዓመት የሥራ አጥ ወጣቶች መጠን በስምንት በመቶ ቢቀንስም ወደ 12 በመቶ የሚጠጉ የክልሉ ወጣቶች የአካል ጉዳትና ጤና እክልን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት ሥራ ለመፈለግም ሆነ ለመሥራት አልቻሉም።

🔴 ከሥራ አጥ ወጣቶች መካከል 23.4 በመቶው በየዕለቱ በሥራ ፍለጋ ላይ ቢሰማሩም በፋይናንስ እጥረት፣ በመሠረተ ልማት አለመሟላት፣ አስተዳደራዊና መዋቅራዊ መሰናክሎችን በመሳሰሉ ዋና ዋና ጉዳዩች ምክንያትነት ሥራ ማግኘት አልቻሉም።

🔴 ከአጠቃላይ የጥናቱ ተሳታፊዎች 52 በመቶው ሥራ የማግኘትም ሆነ የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅማቸው በኢኮኖሚያዊ መደላድሎች አለመሟላት እንደተደናቀፈባቸው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። ወደ 46 በመቶ የሚጠጉት ደግሞ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ የሥራ ፍለጋ ሁኔታቸው ላይ ችግር እየፈጠረ ስለመሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

🔴 ወጣቶች ሌሎች የሥራ ሁኔታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ እንደሆነ ከገለጿቸው ጉዳዩች መካከል፣ የማኅበራዊ አገልግሎቶች አለመሟላት፣ የተለያዩ የጤና እክሎች፣ ማንነት፣ እንዲሁም ፆታና ዕድሜን መሠረት ያደረገ አድልኦና መገለል ተጠቃሽ ናቸው።


አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በኃላፊነት ላይ የሚገኙ አካል በ2016 ዓ.ም. ብቻ በክልሉ 49 ወረዳዎች በተደረገ ጥናት 27,000 ወጣቶች ሥራ ፍለጋ ወደ ውጭ አገሮች ለመሰደድ ቀዬአቸውን ለቀው መውጣታቸውን ቤተሰቦቻቸው መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶች በብዛት እየተሰደዱ ካሉባቸው ሥፍራዎችም የኢሮብ ብሔረሰብ ወረዳዎችና የማዕከላዊ ትግራይ ዞን አካባቢዎች ይገኙበታል።

" በ2016 ዓ.ም. በኢሮብ ወረዳ ብቻ ከተሰበሰበ መረጃ 32 ወጣቶች ወደ ውጭ አገሮች በሕገወጥ መንገድ ሲሰደዱ በረሃ ላይ በተለያዩ መንገዶች ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ተረድተዋል " ብለዋል።

ከክልሉ በተገኘ መረጃ በጂቡቲና በሶማሊያ በኩል ወደ የመን በሕገወጥ መንገድ ለመሰደድ ዜጎች ከ300 እስከ 500 ሺሕ ብር እየከፈሉ ናቸው።

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የመረጃ ምንጭ፣ " ወጣቱ ለስደት ወጥቶ ሕይወቱ ያለፈ ወንድሙን ለቅሶ አርባ ቀን እንኳን ሳያወጣ ነው ተነስቶ ለስደት እየወጣ ያለው "  ብለዋል።

ሴቶች በደላሎቹ እጅግ ተፈላጊ መሆናቸውንና ሴቶችን ለሚያመጡ ወንዶች እስከ ነፃ ጉዞ ድረስ የሚደርስ ድርድር እንደሚያደርጉ ከስደተኞች መስማታቸውንም ተናግረዋል።

ወጣቶች በገፍ እየተሰደዱ ያለበትን ምክንያት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ " የመጀመሪያው የደኅንነት ጉዳይ ነው፣ ደኅንነት እየተሰማቸው አይደለም፡፡ በተለይ በድንበር አካባቢ ያለው ወጣት በአንድ በኩል የኤርትራ ኃይል በየቀኑ ሰውን እያፈሰ ሲወስድ ይመለከታል፡፡ ሕዝቡ በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው። ሌላው የሚሰደደው የሥራ ዕድል ለመፍጠርም ሆነ ሥራ ለማግኘትም ያልቻለ ነው፡፡ በሌላ በኩል ጦርነት እንዳያገረሽ ሥጋት ያለበትም እንዲሁ እየተሰደደ ነው " ብለዋል።

(ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው)

@tikvahethiopia
#Infinix_HOT50_Pro+

አዲሱ የኢንፊኒክስ HOT50 Pro + ጥንቅቅ ብሎ የተሰራው ዲዛይኑ ከአያያዝ ምቹነት አልፎም ለዕይታ ማራኪ ከመሆኑ ባሻገር በሶስት የቀለም አማራጮች ቀርቧል፡፡

@Infinix_Et|@Infinixet

#Infinix #InfinixHOT50Pro+ #WOOOWNewHOT #InfinixHOT50Series
#DStvEthiopia

🔥ዛሬ ምሽት ማን ዩናይትድ ወደ ሜዳ ይመለሳል !
ዩናይተድ የግሪስ ቡድን ፓኦክን በኦልትራፎርድ ስታዲዮም የጋጠማል! በቀጥታ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት በSS Football በ ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ

ዩናይትድ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ይችላል?

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ይከታተሉ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvSelfServiceET
TIKVAH-ETHIOPIA
" አግተዋቸው 300,000 ብር እየጠየቁ ነው " - ቤተሰቦች በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ሰዎች ለሕክምና ብለው በወጡበት በታጣቂዎች መታገታቸውን የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ የታገቱት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ የሕክምና አገልግሎት በመዘጋቱ አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ነቀምት ሄደው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት መሆኑን አመልክተዋል።…
#Update

በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ሰዎች  ለሕክምና ብለው በወጡበት በታጣቂዎች መታገታቸውን የታጋች ቤተሰቦች ከቀናት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

" አግተዋቸው 300,000 ብር እየጠየቁ ነው " ነበር ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ታጋቾቹ እንደተለቀቁ ከቤተረቦቻቸውና ከታጋቾች አንደበት ማረጋገጥ ተችሏል።

ከታጋቾቹ መካከል አንዱ እንደሆኑ የገለጹና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ ፤ " ሰው ተደብድቦብን ለሞት ደረሰና ወደ ነቀምት ሆስፒታል ሪፈር አፅፈን ወደ ነቀምት ተጓዝን። እዛ እስከምንደርስ ምንም ችግር አልደረሰብንም ነበር " ብለዋል።

ሕክምናውን ጨርሰው እየተመለሱ  በነበረበት ወቅት ኣጋቾች ከጫካ ወጥተው መታወቂያ ከጠየቁ በኃላ ማገታቸውን ጠቁመዋል።

" የአማራ ተወላጅ ወደዛ መሄድ ስለማይችል ከእኛ ጋር አንድ የኦሮሞ ተወላጅ አብረን ይዘን ሄደን ነበር። እርሱን 'ና ውረድ ለምን ለአማራ ተወላጅ ብለህ አብረህ የሄድህ? ' ብለው ወደጫካ ወስደው በጣም ደበደቡት፤ አሰቃዩት " ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።

" እኛ ላይ ዛቻ አደረሱብን እንጂ አልደበደቡንም። ከዚያ ገንዘቡ ሲላክ ለቀቁን " ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

ያገታችሁ ማነው በሚን ለቀረበ ጥያቄ  በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሸኔ ታጣቂ መሆኑን ገልጸዋል።

" ሌሊቱን በጫካ ውስጥ ሲያዞሩን ነው ያደሩት የእግር ጉዞ አለው። እኔ ደግሞ ኦፕራሲዮን ነኝ። ያገተን ታጣቂ ‘ መናኸሪያ ላይ መታወቂያ የጠየቃችሁ ፓሊስ የለም ወይ ? ’ አለኝ። አዎ ጠይቆናል አልኩት። ‘ እርሱ ነው እንደመጣችሁ የነገረኝ አለኝ ’። ሌላ የማውቀው ነገር የለም " ሲሉ መልሰዋል።

እኚሁ ታግተው የነበሩ ግለሰብ፣ " እኛ ተሰቃዬንም፤ ገንዘብ ከፈልንም ተለቀናል። ለወደፊት ግን ማንኛውም ሰው መብቱ ተጠብቆ በማንነቱ የሚደርስበት ጉዳት ይቁምልን " ሲሉ ተማጽነዋል።

ታጋቾች ከእገታ እንዲለቀቁ ከወዳጅ ዘመድ እርዳታ ጠይቀው ለአጋቾቹ ገንዘብ እንደላኩ የገለጹልን አንድ ስማቸው እንዲነሳ ያልፈለጉ የታጋች ቤተሰብ ፥ " ወንድሞቻችን ከነቀምት ከህክምና እየተመለሱ ኪረሙ ወረዳ ለመድረስ 5 ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው ታግተው ነበር " ብለዋል።

" ምንድን ነው ችግሩ ? ብለን ስንጠይቅ የተፈለገው 300 ሺሕ ብር ላኩ ተባልን፡፡ ብሩን ላክን " ነው ያሉት።

ለአጋቾቹ በምን መልኩ ነው ገንዘቡን የላካችሁት ? ተብሎ ለቀረበላቸው የቲክቫህ ጥያቄ ፥“በአካውንት እንላክላችሁ አልናቸው 'አይቻልም በእጃችን ነው፣ በአንዲት መኪና ሰዎች ይመጣሉ ለእነርሱ ስጡ ያኔ ሰዎቹን እንለቃለን' አሉ፡፡ ከወረዳው የተላከችው መኪና መጣች 300 ሺሕ ብር ላክን፡፡ ሰዎቹ ተለቀቁ። መኪናይቱ ከወረዳ የመጣች ናት " ብለዋል።

አጋቾቹ  ፥ ከታጋቾቹ ጋር አብሮ የሄደውን ግለሰብ ' ለምን አብረህ ሄድክ? በሚል'እንገለዋለን' በሚል ዛቻ አንለቅም ብለው  ሲያስፈራሩ እንዳይገድሉት ተማፅኖ ሲቀርብ '100 ሺሕ ብር ጨምሩ' በማለታቸው ብሩ ተጨምሮ እርሱም ከእገታ መለቀቁን ጠቁመዋል።

በአሙሩ፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋና በሌሎችም " ቦታዎች ሰዎች ታግተው ብር ተጠይቆባቸው ብሩ ከተላከ በኋም በአጋቾች ተገድለዋል። እኛ ግን እግዚአብሔር ይመስገን ብሩን ከፍለን ተለቀውልናል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ እገታው ከተፈጸመበት ቦታ በቅርብ ርቀት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እንደነበሩ የታጋች ቤተሰብ አስረድተዋል።

ሌላኛው የታጋች ቤተሰብ ደግሞ ፥ " ከዘመድ ወዳጅ አሰባስበን 400 ሺሕ ብር ከፍለን ታጋቾቹ ተለቀዋል፡፡ ሴቶች፣ የሶስት ቀን ሕፃናት ሁሉ ተገድለዋሌ፡፡ ግን እስከ መቼ ድረስ ነው ፍትህ የማይሰጠን? " ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአካባቢውንና የክልሉን የጸጥታ አካላት ምላሽ ለማካተት ጥረት ቢያደርግም ባለስልጣናቱ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል። የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው። ሌቪት ፥ ትራምፕ…
#ዴሞክራሲ #አሜሪካ

" ሕዝቡ የሚመርጠውን እንቀበላለን " - ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን

ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የ2024 የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫን ዶናልድ ትራምፕ ካሸነፉ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር አድርገዋል።

በዚህም ፥ ለተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ ስልክ ደውለው " የእንኳ ደስ ያለዎት !" መልዕክት ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል።

ባይደን ከዲሞክራቷ ዕጩ ካማላ ሀሪስ ጋር እንደተናጋገሩ አስታውቀው " መልካም አጋር እና የሕዝብ አገልጋይ ናት " ብለዋል።

የካማላ የምርጫ ዘመቻን " አነቃቂ " ሲሉ ያሞገሱት ባይደን ምክትል ፕሬዝደንቷ በሥራቸው እንዲኮሩ መክረዋል።

" አንዲት ሀገር ምርጫዋ አንድ ነው። ሕዝቡ የሚመርጠውን እንቀበላለን " ሲሉም ተናግረዋል።

ባይደን " ስናሸንፍ ብቻ አይደለም ሀገራችንን የምንወደው፤ ስንስማማ ብቻ አይደለም ጎረቤታችንን የምንወደው " የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንደሚኖርም አስታውቀዋል።

የምርጫ አስተባባሪዎችም " ምስጋና ይገባቸዋል " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥር 12/2017 በኦፊሴላዊ መንገድ መንበረ-ሥልጣኑን ይረከባሉ።

የ2024 ፕሬዝደንታዊ ምርጫ " ታሪካዊ ነው " ያሉት ባይደን በሚቀጥሉት 74 ቀናት ያልተቋጩ ሥራዎችን ጨርሰው ሥልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ አሳውቀዋል።

" መሸነፍ ያለ ነው። ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ ይቅር የማንለው ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩ የሆነው ለፕሬዝዳንትነት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፎካከሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ሽንፈታቸውን ተቀብለው ለተመራጩ ፕሬዝዳንት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ሃሪስ፥ ለትራምፕ ስልክ ደውለው " እንኳን ደስ አለዎ " ማለታቸው ተዘግቧል።

ሃሪስ ለትራምፕ ስልክ ደውለው የ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን በማሸነፋቸው ውጤቱን መቀበላቸውን የሚያመለክት መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
2024/11/15 16:00:02
Back to Top
HTML Embed Code: